• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአረቢያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ሽያጭ ተጠያቂው ማነው?

December 27, 2012 10:46 am by Editor 4 Comments

ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል። ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት ነው፡፡

የወገኖቻችን እንግልት የሚጀምረው አገራቸው ላይ ነው፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያንም በዜጎቻችን ላይ ክብራቸውን ጭምር የሚነካ ተግባር የሚፈጽሙ አሉ፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በደላላዎች እየተደለሉ ከየቀያቸው እየተፈናቀሉ ዜጎቻችን ለጉዳት እየተዳረጉ ነው፡፡ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ እንደሆነና ወርቅ ተነጥፎ እንደሚጠብቃቸው በመስበክ ወጎኖቻችንን እያስጨረሱ ነው፡፡ ከእነዚህ ደላሎች በስተጀርባ የመንግስት እጅ አለበት መንግሥት ዜጎችን ከመጠበቅና ካለበት ኃላፊነት አንጻር እሱም ተጠያቂ ነው፡፡ ዕድሜያቸው እንዳልሞላ እየታወቀ ከ13-15 ዓመትን ልጅን 23-26 ዓመት በማለት በማጣራትና አይቶም መገመት ሲቻል ፓስፖርት ይሰጧቸዋል፤ የሚያስደነግጥ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ሳዑዲና ኩዌት ለመሄድ የሚመጡት መጻፍ፣ ማንበብ የማይችሉና መታወቂያና ፓስፖርት መሆኑን መለየት የማይችሉ ናቸው፡፡ ፓስፖርት እስከሚያወጡና የሕክምና ምርመራ እስከሚደረግላቸው ድረስ ብዙ ችግሮችን ያሳልፋሉ ሁሉም ነገር ተሳክቶላቸው እስከሚሄዱ ድረስ የደላሎቹ የወሲብ መፈጸሚያ ይሆናሉ፡፡ የጤና ምርመራ ሲደረግላቸውም የHIV ተጠቂ ሆነው ይገኛሉ፤ ውጤታቸው ሲነገራቸው እንደ ውርደት ስለሚቆጥሩት ተመልሰው ወደቀያቸው መግባትን ይተዉና ራሳቸውን በመሸጥ ለመተዳደር ይሞክራሉ፡፡ በሽታውንም ያስተላልፋሉ ላልተፈለገ እርግዝና ለአደንዛዥ ዕፆች ተጋላጭ እየሆኑ ነው፡፡

የጤና ምርመራ ውጤቱን አግኝተው ከተጓዙ በኋላ በተቀባይ አገሮችም ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ እዚያ ሲመረመሩ ብቁ አይደላችሁም ተብለው እንዲመለሱ ይገደዳሉ ወይም የት እንዳሉና ማን እንደቀጠራቸው፣ ስንት ቤተሰብ ያለበት ቤት እንደሚገቡ በስንት እንደተቀጠሩ፣ ቀጣሪዎች ለሕገወጦች ከፍለናል የሚሉት ገንዘብ ስንት እንደሆነና ከሄዱ ከስንት ጊዜ በኋላ ደመወዛቸውን እንደሚያገኙ አያውቁትም፡፡ ዱባይ ከደረሱ በኋላ ወደ አፍጋኒስታንና ኢራን ሳይቀር ለቤት ሠራተኝነት ያግዟቸዋል፡፡ ወይም ዱባይ አየር መንገድ ደርሰው የሚቀበላቸው ሰው ባለማግኘት አየር ማረፊያው አካባቢ ሜዳ ላይ ለመዋልና ለማደር፣ ለምኖ ለመብላትም የተገደዱ በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች ወዴት እንደሚሄዱና ለምን እንደሚሄዱ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ መንግሥት ራሱ ማወቅ ነበረበት፡፡ የዜጎቹን መብት የሚያስከብር መንግስት የለንም በዚህ የተነሳ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች በሕገወጥ መንገድ እየወጡ ነው፡፡ የሚደርስባቸውን አደጋ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡

የዚህ ምክንያት ብዙ ነው፡፡ አንዱና ዋነኛው ቁጥጥሩና ክትትሉ በአግባቡ አለመቃኘቱ ነው፡፡ ዜጎች በየትኛውም ቦታ የመዘዋወር ሕገመንግሥታዊ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን በተለይ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚደረገው ጉዞ ለሥራ መሆኑን መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ጉዞው በህጋዊ መንገድ መሆን ሲገባው፣ በተለያየ መንገድ የሚመጣላቸውን ቪዛ ሕጋዊ ሳያስደርጉና ሳይመዘገቡ ዝም ብለው ነው የሚሄዱት፡፡ ይኽ ደግሞ በውጭ አገር ያሉ ሕገወጦች ቪዛዎችን እያወጡ ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ እዚህ ያሉት ሕገወጦች ተቀብለውና በሕገወጥ መንገድ ለመለመሏቸው ዜጎች ይሰጣሉ፡፡ በዚህ መካከል ሕገወጦቹ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ የኩዌት ኤምባሲ ከሚሠሩ የበታች ሠራተኞች ጋር በሚደረግ የምስጢር ግንኙነት ሕጋዊ ሥርዓቱን በሚቃረን መልኩ እየተሠራ ነው፡፡ በመሆኑም ሕጋዊዎቹ ኤጀንሲዎች ሥራቸው እየተዳከመ ነው፡፡ መንግስት አለ በሚባልበት አገር ሕግ እየተጣሰ በሕጋዊ መንገድ በሚላከው ቪዛ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ እየሄዱ ነው፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ የኢትዮጵያ ቆንስላዎች ወደ ሳዑዲ የሚላኩ ሠራተኞች ስለሚያገኙት ደመወዝ መወሰን የሚችሉት እነሱ እንደሆኑና እጅግ በወረደ ደመወዝ እንደሚያስቀጥሩ መረጃ አለ፡፡ በኩዌት በሳዑዲ ዓረቢያና  ጅዳ  የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሰው ኃይልን በርካሽ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያው እያስነገረ ነው፡፡ ተልዕኮአቸውና ኃላፊነታቸው ግን አይደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ የሚሳተፉ የኤምባሲ ሠራተኞች አሉ፡፡ በኩዌት አካባቢም ከአሠሪዎቻቸው ሸሽተው ከለላ ለማግኝት ወደ ኤምባሲ ለመጠለል ስሄዱ ኤምባሲው ውስጥ ባሉ ሰራተኞች አማካይነት ለሌላ አሠሪ አሳልፈው እንደሚሸጧቸው ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡ ይህንን ጉዳይ ለማስቆም የተንቀሳቀሱትን ወገን ወዳድ ዜጎች በመንግስት ባለስልጣናት ታፍነዋል፡፡

በአሁኑም ጊዜ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በቀን ከአንድ ሺሕ እስከ አንድ ሺሕ አምስት መቶ ይሄዳሉ፡፡ ተቀባይ አገሮች ከሌሎች ሠራተኛ አቅራቢ አገሮች ጋር ያላቸው ግንኙነት ጥሩ ስላልሆነ ፊታቸውን መሪና መንግስት ወደ ሌላት ኢትዮጵያ አዙረዋል ምክንያቱም ሌሎች አገሮች የዜጎቻቸውን መብት እያስከበሩ ስለሚልኩ በአሁኑ ጊዜ ብዙ አገሮች ወደ መንግስት አልባዋ ኢትዮጵያ ትኩረት እያደረጉ ነው፡፡

ለምሳሌ ፊሊፒንን ብንወስድ በዱባይ የሚገኘው ኤምባሲያቸው ጉዟቸውን ሳያፀድቅ አገራቸውን ለቀው አይወጡም፡፡ የአገራቸው መንግሥትም ማንኛውም የቤት ሠራተኛ ሆኖ የሚሄድ ዜጋው ከ450 ዶላር በታች ተከፋይ ሆኖ እንዳይጓዝ በሕግ ደንግጓል፡፡ ችሎታና የትምህርት ደረጃቸውን በሚመለከት የሚሞሉት የቅጥር ፎርም ትክክለኛና እውነተኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ለሚያጋጥሟቸው አስከፊ ችግሮች፣ ለሚደርስባቸው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣና የጉልበት ብዝበዛ መነሻ የሴቶቹ የአገሩን ባህልና አኗኗር ዘይቤ አለማወቅና ለሥራቸው የሚያስፈልጋቸውን ሥልጠና አለማግኘት ነው፡፡ እንደ ልብስ ማጠቢያ ወይም ምግብ ማብሰያ ባሉ ማሽኖች ግራ ይጋባሉ፡፡ ስለሚቀጠሩበት ቤት ሁኔታ፣ የቤተሰብ ብዛት ሌላም ሌላም አንድም የሚያውቁት ነገር ሳይኖር ከአገር ይወጣሉ፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚታየው ወደ አረብ አገሮች በመሔድ ላይ ያሉት ለአዲስ አበባ እንኳ እንግዳ የሆኑ ከገጠር አካባቢ የሚመጡ ልጆች ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የሚቀጥራቸው እንዲገኝ ሲባል የኢትዮጵያውያኑ የቅጥር ፎርም ችሎታቸው ምንም ይሁን ምን ሁሉንም ዘመናዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ማሽን መጠቀም እንደሚችሉ፤ ማንኛውንም ሥራ ለመሥራትም ብቃት እንዳላቸው ተደርጎ ይሞላል፡፡ ይህን ከፍተኛ ቁጥር የተመለከቱ ዱባይ ውስጥ የሚገኙ ህንድና ፓኪስታናዊ ደላሎች አማርኛ ለምደው ሥራቸውን እያቀላጠፉ ኢትዮጵያውያኑ በወር የሚከፈላቸው 135 ዶላር ሲሆን፣ ኤጀንሲዎች አንዲት ኢትዮጵያዊትን በማስቀጠር የሚያገኙት 500 አልያም 550 ዶላር ነው፡፡ በተቃራኒው አንዲት ፈሊፒን የቤት ሠራተኛን በማስቀጠር ኤጀንሲዎች ከ2700 ዶላር በላይ ያገኛሉ፡፡ ‹‹አንዲት ፊሊፒን ለሚቀጥር ኢትዮጵያዊ ይመረቅለታል›› የሚሉ ማስታወቂያዎች በተለያዩ የሥራ ማስታወቂያ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ላይ መመልከትም የተለመደ ሆኖአል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    December 27, 2012 11:44 am at 11:44 am

    Woyane ethnic fascists are systematically destroying Ethiopia and Ethiopians. I am sure the victims of this are Amharas, Oromos and other ethnic groups not the golden Tigrians. The solution is to unite and get rid of these home grown fascists to shorten the suffering of the Ethiopian people. The home grown fascists told us already 21 years ago that their main goal is to disintegrate Ethiopia and build greater Tigrai. But some hodams and those who are blinded by ethnic love could not understand this or they do not want to accept this and tell us about the roads and buildings. Italian fascists were also good in building roads and bridges. FREEDOM FIRST.

    Reply
  2. Anteneh says

    December 27, 2012 01:50 pm at 1:50 pm

    Geta hoy ye Ethiopia sewochen ante tebekelen.Amen Amen Amen!!!

    Reply
  3. nezar dage says

    December 31, 2012 02:42 am at 2:42 am

    betam yaszenall.

    Reply
  4. nezar dage says

    December 31, 2012 02:57 am at 2:57 am

    በመካከለኛው ምስራቅ አውን ያለንበት ሁኔታ እጅግ የከበደ እና ከመቼውም በተለየ መልኩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ነው ፡፡ ከላይ እንደተገለጸውም ያለውን የአብዛኛው ስደተኛ ችግር ተዳሶአል ፡፡ በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲ ከፍተኛ የሰው ሀይል እየገባባቸው ካሉት የ ኩዌት እና የሳውድ አረቢያ አገሮች ላይ ያለወን የሚመለከታቸው አካላት የአፈጻጸም ችግር እና ድክመት እረሱ መመልከቱ የመንግስት በጉዳዩ ዴንታቢስነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ፡፡
    በመካከለኛው ምስራቅ መኖር እጅግ ከባድ እና አሳፋሪ እየሆነ በመጣበት በዚህን ሰሀት ፣ ብሎም ከዚ በፊት ለአመታት ሲሰቃይ እና ህይወቱን ሲያጣ ለነበረ ዜጋ ፣ በተለያዩ ዘግናኝ የአረብ እስር ቤቶች እየማቀቁ ላሉ እስረኞች ምንም አይነት መፍትሔ ሳይመጣ እባካችው ሌላም ዜጋ አለን እና ወሰዱ እየተባለ እየተለመነ ባለበት ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት ለዘላቂ መፍትሄ ከመሰራት ይልቅ እርካሽ የሰው ሀይል ውሰዱ እያሉ የአረብ ባለሰልጣናቶችን መለመን ሌላኛው ትልቅ ህመም ነው ፡፡
    ያለውን ችግር ብዘረዝረው ማብቂያ የለውም ፡፡ እኔ ግን አንድ ፍራቻ አለኝ በዚው ከቀጠለ እውነት የሚሆን ፍራቻ ፡፡ ዛሬ ፓስፖርት እያወጣ እየተሰደደ ያለ የአረብ አገር ዜጋ ነው ያለው ፡፡ ነገ ደሞ እራሳቸው አረቦቹ አገራችን ድረስ ዘው ብለው ገብተው እንደ ባሪያ ሰርሃት እያፈኑ ዜጎቻችንን ቢወስዱ የማን ያለ ይባላል ፡፡ ምክንያቱም አገሩ ኢትዮጵያ ነው ማንም ለማንም የማያስብበት ፡፡ አውንም በዜጎቻችን ላይ እየተደረገ ያለው ተግባር ከዛ አይለይም ዜጎች አገራቸው ድረስ ሰለሚሄዱላቸው እንጂ ፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
Copyright © 2026 · Goolgule