• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው?

April 30, 2014 08:32 am by Editor Leave a Comment

ፍርሃት የማያሰራው ነገር የለም።ኢህአዲግ በከፍተኛ የፍርሃት ማጥ ውስጥ ነው።ሁሉንም ይፈራል።አይዞህ አትፍራ ቢሉትም የሚችል አይመስልም።በሕዝብ ላይ የሰራቸው ሕዝብ የሚያውቃቸው እና የማያውቃቸው ብዙ ድብቅ ስራዎች ስላሉት የመፍራት ደረጃው ከዕለት ወደ ዕለት እየባሰበት እንጂ እየተሻለው አልሄደም። የሚደግፉትም ልያፅናኑት አልቻሉም።ከሚገባው በላይ ፍርሃት ሲያንቀጠቅጠው ሲመለከቱ እነርሱም ይብሱን ፈሩ።ብዙ የስርዓቱ ደጋፊዎች እና በሀብት የደለደሉቱ ሀገር ጥለው እየወጡ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህ ደግሞ ሌላው የፍርሃት ገፅታ ነው።

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሌሎች ሰሞኑን የተያዙት ጋዜጠኞች ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ግን ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር ያሉ በእዚህም መስረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ እየጠቀሱ የሃሳብ የመግለፅ መብታቸውን የተጠቀሙ፣የሚሰሩት በመንግስት መስርያቤቶች የሆነ፣የሚፅፉት አይደለም ምን በልተው ከማን ጋር ውለው እንዳደሩ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሕዝብ የሚያውቃቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው።ከእዚህ በፊት በሃሳብ የሞገቱትን ሁሉ ”ህገ መንግስቱን እና ስርዓቱን ለመናድ የተንቀሳቀሱ” እያለ ሲያስራቸው የነበረው መንግስት ዛሬ እራሱ ህገ መንግስቱን አክብረው ሕግ እየጠቀሱ የፃፉትን በ20 ዎቹ እድሜዎች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ”ሃገርን በውጭ ከሚኖር ድርጅት ጋር ተመሳጥረው ሊያሸብሩ” እያለ ፌዝ አይሉት ቀልድ መሰል ክስ አቅርቦ ማዕከላዊ እስር ቤት አስገባቸው።ምንም አይነት ወንጀል እንደሌለባቸው እራሱ ኢህአዲግ ያውቀዋል።ግፍ መስራት የማይሰለቸው እና በፍርሃት የተዋጠ መሆኑ ግን የእዚህ አይነቱን ተግባር እንዲቀጥልበት አድርጎታል።zone 9

”የፈሪ ዱላው አስር” እንዲሉ የኢህአዲግ አባላት ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ የግብፅ፣የየመንን በቅርቡ ደግሞ የዩክረንን የህዝብ ንቅናቄ እያዩ በሰላም መተኛት አልቻሉም።ያ ቀፎው እንደተነካ ንብ የሚተመው ሕዝብ አንድ ቀን እኛም ላይ ይነሳል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።ለእዚህም ማስረጃው ኢቲቪ ባለፈው ሰሞን ያሳየው የዩክሬንን አመፅ የተመለከተ ፊልም መጥቀሱ ይበቃል።ፍርሃታቸውን ደግሞ እነ ሚሚ ስብሃቱ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ገብቶ እንደሚንዘፈዘፍ ሰው እየተንቀጠቀጡ ሲናገሩ ሕዝብ ታዝቦ ”ወይ ፍርሃት” ብሏል።ግንቦት 20 ስመጣ ጀግና እንደነበሩ ከሃያ ዓመት በፊት የነበሩ አሮጌ ታንኮች ያሳየናል።መለስ ብለው ደግሞ በፈስ ቡክ እና በጡመራ ፈራን ይላሉ።አጀብ ነው።

ኢህአዲግ ፈራሁ ብሎ ያሰራቸው ንፁሃን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው? የወጣቶቹን የስራ መስክ ግልፅነት እና ሙያ ተመልክታችሁ ፍረዱ።ለፈሪዎችም እዘኑላቸው።

1/ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
ለተባበሩት መንግሥታት ዜና አገልግሎት ኢሪን ለረጅም ጊዜ የሰራ የእንግሊዝኛው ‘ፎርቹን’ ጋዜጣ አምደኛ እና ዘጋቢ

2/ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ
አዲስ ጉዳይ መፅሄት ከፍተኛ ኤዲተር

3/ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ
በአካባቢ ጥበቃ የሰለጠነች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በቀድሞው ‘እንቢልታ’ ጋዜጣ ዘጋቢ

4/ በፍቃዱ ኃይሉ
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ብሎገር እና ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ በሙያው የሚሰራ

5/ አቤል ዋበላ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ‘ግራውንድ ቴክኒሻን’

6/ ማህሌት ፋንታሁን
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰራተኛ

7/ አጥናፍ ብርሃኔ
የ25 ዓመት ወጣት በፌስ ቡክ ሃሳቡን የሚገልፅ በብሎጉ ላይ ሃሳቡን የገለፀ

8/ ናትናኤል
የ 26 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ባለሙያ፣’የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር’ አባል

9/ ዘላለም ክብረት
የሕግ ባለሙያ፣ማስተርሱን ከሰራ ገና ሳምንታት የሆነው በአምቦ ዩንቨርስቲ የሕግ ትምህርት መምህር ናቸው።

ምንጭ – ከጦማርያኑ ውስጥ በውጭ ሀገር የሚገኙት እንዳልካቸው እና ሶልያና ለቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሚያዝያ 20/2006 ዓም ከሰጡት መግለጫ የተገኘ።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 21/2006 ዓም

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule