
1) ያልተረጋገጠ መረጃ እያኘክ ትኩረትክን አትጣ። አሁንም ተወርረሃል! በርካታ ወገንህ በጨካኝ ኃይል ስር ነው። እየተዘረፈ፣ እየተጨፈጨፈ ነው። አቋም ያዝ። ጠላት ወርሮኛል ብለህ ተቆጣ! በሰበር ዜና ስሜትህን አታላላ! ሰበር ዜና አንተ እንድትታለን የሚለቀቅ አይደለም። ከሜዳ እንድትዘናጋ የሚሰራ አይደለም። ጠላት ይደንግጥበት፣ አንተ ተጨማሪ የማሸነፍ ወኔ ሰንቀህ ገስገስበት!
2) መጥፎ ነገር ሲኖር ከዚህም ከዛም ላይ አትበሳጭ፣ ተስፋ አትቁረጥ። መፅናት ብቻ ነው የሚያዋጣው። መቼም ቢሆን እናሸንፋለን ብለህ አቋም ያዝ።
3) ሕዝብ በረንዳህ አይደለም። በረንዳህን ብርድ ሲሆን ጥለኸው ትገባለህ። ፀሐይ ሲሆን ወጥተህ ትዘረጋበታለህ አይደል? ሕዝብ እንደዛ አይደለም። በክፉውም በበጎውም አብረኸው ሁን። ሲጠቃ ተስፋ ቆርጠህ፣ ተስፋ እያስቆረጥክ፣ ለጠላት የሚጠቅም ፕሮፖጋንዳ ስታሰራጭ እየዋልክ፣ መለያያ እየፈለክ ከምኔው ድል ሲባል ሮጠህ መምጣት እንደመርህ መያዝ የለበትም። አንድ ተራራ ሲያዝ መቆዘም፣ ተራራ ሲያስለቅቅ አማራው ተራራ የሚል ስነ ልቦና የአማራ አይደለም። ፈፅሞ!
4) የትህነግ ዋና ጠላትነት ትርክቱ ነው። ጦሩ ቢያልቅ፣ ከአማራ ምድር ቢወጣ ጠላትነቱ ይቆያል። ትህነግ ከራሱ በተጨማሪ በርካታ ልቅምቃሚ ጠላት አፍርቶብናል። ጦርነቱ ገና ነው!
5) ድል ሲኖር በሚመጥን መልኩ ዘክረው። የሕዝብህን ስነ ልቦና በሚገነባ፣ ለሰራዊቱ ግስጋሴ በሚመጥን መልክ አሳውቀው። “ሀሰት ነው” ወዘተ እያልክ በንትርክ መልኩ ከወገንህ ላይ መረጃ አጣሪ አትሁን። የጠላትን መረጃ በዜሮ አጣፍተህ ብልጫ ውሰድ እንጅ፣ ወገንህ ለበጎ በሚለጥፈው ስር እየሄድክ የምትነዛነዝ አቅመ ቢስ አትሁን።
6) የራስክን ሕዝብና ሰራዊት አታሸብር። ምንም የፖለቲካ ልዩነት ቢኖርህ በዚህ ወቅት እየመረረህም ቢሆን ከራስ ወገን ጋር ቁም። ጠላት የሁላችሁንም አንገት እንደሚቆርጥ አትርሳ!
ጌታቸው ሽፈራው
Leave a Reply