
ከዚህ በፊት ስናደርግ የነበረውን የግጥም ጫወታ በበርካታ ምክንያቶችና ለመቀጠል ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለn:: በተቻለን ሁሉ እንደገና ለመጀር እየሞከርን በመሆኑ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በአጫጭር ግጥሞች ታላላቅ መልክቶችን የምታስተላልፈውን የብሌን ከበደን ግጥም ለዛሬው አቅርበናል – ግጥሙን ያገኘነው ከብሌን ፌስቡክ ገጽ ላይ ነው:: እስቲ እናንተም የፌስቡክ ውሎዋችሁን ስንኝ ቁዋጥሩበት::
ምን ይባላል!
ውሎና አዳሬን እዚህ ተወዝቼ
ሰፈሬን መንደሬን ቀዬዬን ዘንግቼ
ከጠለቀው ባህር `ከፌስ ቡክ `ገብቼ
ጥቂት ሞጫጭሬ ብዙ እውቀት አጊኝቼ
ሀሳብን ደግፌ ካልመሰለኝ ትቼ
አሁንም እዛው ነኝ መስኮቴን ከፍቼ ።
አንድ ጊዜ በላኘ ቶኘ አንድ ጊዜ በስልኬ
አይኖቼን ተክዬ እዛው ተላክኬ
ቀንና ሌት ሳልመርጥ ስገባ ስወጣ
ያ ደሞ ምን አለ ይሄ ምን አመጣ
ያቺ ምን ለጠፈች ይቺ ምን አውጥታ
ምን አዲስ ተገኘ ደሞ ምን አመጣ
ስደሰት ስናደድ ስበሳጭ ስቆጣ
ይሄ ቀን አለፈ ደሞ ሌላ መጣ
ወይ ጣጣ!
Temechitognal
ካድሬ እየተባልኩኝ የምሰደብበት ፣
ጥሩ ትፅፍለህ አይዞህ እንዳትደክም በርታ ምባልበት፣
አስተማሪም ቢኖር እረባሽ ተማሪ አንድ ማይጠፋበት ፣
የሰፈር ኮልኮሌ የሚከበርበት ፣
ፌስቡክ ጌታ ሆነ እኛ ሎሌዉ ሆነን ፣
አንዱ አመስግኖ ሌላዉ ሲዘልፈን፣
አሻፈረኝ ብለን ነፃ ካልወጣን ፣
ቸጉቬራም ሞቷል ከፌስቡክ ሰዳቢ ስይገላግለን ፣
(አሁን የፃፍኮት ስለሆነች እናንተዉ አርሞት።)
—————————–
እባክሽን ተነሽ መወዘት ለእሳት ነው
መስኮትሽን ከፍተሽ በርሽን ከዘጋሽው
ብዙ እናዳያመልጥሽ ከሚመላለሰው
አጥርሽን አስከብሪ መስኮት አማላይ ነው።
ያቀረቀረ ዕድሜ ቀጥል ጸላይ መስሏቸው
ስንቶች ተታለዋል ካለው ላይ ተሰርቀው
ነቃ በይ! ቀና! ለሁሉም ግዜ አለው ለሁሉ መጠን
ባለፈው ተናዶ ያለን አስመልጦ ሌላ ቀን ከማደን።
————————-
በለው!