በቅርቡ በአንድ የኦሮሞ ወገኖች ስብሰባ ላይ አንድ ሰው ኦሮምያ ሰላም የምታገኘው ኢትዮጵያ ስትፈራርስ ነው ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት አለ ተብሎ ሲራገብ እያየን ነው። እኔ በግሌ የዚህን ሰው ተልእኮ ለመረዳት ቅንጣት ጊዜ አልወሰደብኝም። ከራሱ ከወያኔ በቀጥታ መልእክት እየተቀበለ የሚሰራ የወያኔ ተቀጣሪ ነው ወይም እያጃጃሉ በስልት የሚጠቀሙበት ሰው ነው። አለቀ።
ይህንን ለማለት ያስቻለኝ ነገር እንደሚታወቀው ይህ መንግስት ገና ሲመሰረት ጀምሮ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለው መሳሪያ ህዝባዊ ድጋፍ አይደለም። በዚህ ጎጠኛ የፓለቲካ አስተሳሰቡና በሙስና ድር በተፈጠረ ሥርዓት ምን ጊዜም ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ አያስብም። ይህንን መንግስት በሚገባ ያውቃል። ይህን ስርዓት እድሜ ይቀጥልለታል ተብሎ የሚታሰበው ስልት ቅራኔ ነው። ለዚህም ነው መንግስት ከህገ መንግስቱም በላይ አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚያራግበው። ምክንያቱ ቅራኔዎችን እየፈጠረ በዚያ ቅራኔ መሃል ነው ስርዓቱ ህልው የሚያገኘው። በኢትዮጵያ ውስጥ ቅራኔ ሲፈልጉ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የመደብ ቅራኔን ማንሳት ስለማይችሉ ቅራኔውን የመሰረቱት በአለፈ የሃገሪቱ መጥፎ ትዝታዎዥ (past bad memories) ላይ ነው። ያለፈውን የታሪክ ትውስታ በነባራዊው እውነት ላይ እየጨማመሩና እያራገቡ ሲያስፈልግም እንደ አኖሌ አይነት ሃውልት እያቆሙ ቅራኔን ማራገብ ነው። በዚህ ጊዜ ፓለቲካው በብሄር ላይ ስለቆመ ያለፈ የታሪክ ግድፈት ለቅራኔ መሰረት ሲሆን ያን ያለፈ ችግር ወደ አንድ ብሄር በማላከክ ቅራኔው ሲራገብ አቅጣጫው በቀጥታ ወደ ብሄር ግጭት ይሄዳል።
በዚህ መሰረት ወያኔዎች ቅራኔውን ሲያራግቡ በተለይ ሁለቱ ብዙ የሰው ሃይል ያላቸው አማራና ኦሮሞ ቅራኔ ውስጥ ይገባሉ የሚል ስልት ይዘው ነው። የታሪክ ቅራኔው በብሄር ፓለቲካ ከባቢ ውስጥ ሲግል ይህ ቅራኔ በቀጥታ ወደ ብሄር ግጭት ይዞራልና ነው። ይሄ ስልት የወያኔ የስልጣን መሰረት ተደርጎ የሚወሰድ ነው። በሌላ በኩል ያለው ቅራኔ ደግሞ መድብለ ፓርቲውን የአንድነት ሃይልና የብሄር ሃይል በመፍጠር እነዚህን ሃይላት ማናቆር በየብሄሩ አክራሪ ብሄርተኞችን በማፍራት ከአንድነት ሃይሉ ጋር እንዲናቆሩ ማድረግና የየብሄሩ አክራሪ ሃይላት እርስ በርስ እንዲነቃቀፉ ማድረግ ነው። እነዚህ ሃይላት በቀላሉ ስለማይገናኙ ይህ የፓለቲካ ቅራኔ የስልጣን መሰረቴ ነው ብሎ ህወሃት ኢህአዴግ በጣም ያምናል። ቅራኔዎች በብሄርና በመድብለ ፓርቲው አካባቢ ሲበዛ ከእኔ ላይ ገለል ይላሉ ነው ስልቱ።
መንግስትን ህዝባዊ መሰረት የሚያጎናፅፈው ተመራጭ የፓለቲካ አስተሳሰብ ባይኖረንም ግን ቅራኔ መብዛቱ አንድን ጠባብ ቡድን በኢኮኖሚው ዘርፍ እስክንለውጥ ድረስና የበላይነቱን እስክናቆናጥጥ ጊዜ ይሰጠናል ብለው የስርአቱ ዋናዎች በሃይል ያምናሉ።
ታዲያ ይህ ስልት ባለፉት አመታት የተጠቀሙበት ቢሆንም በቅርቡ የተነሳው ህዝባዊ ንቅናቄ የዚህን መንግስት የስልጣን መሰረት የሆነውን የብሄር ቅራኔ መቀመቅ እያወረደው ነው። አማራውና ኦሮሞው ማዶ ለማዶ እየሆኑ ደምህ ደሜ ጉዳትህ ጉዳቴ ነው እያለ አስገራሚ ህብረት ሲያሳዩ መንግስት እጅግ ደንግጧል። ለምን ካልን ከፍ ሲል ያልነው ስርዓቱ በቅራኔዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ህዝቡ እነዚህን መሰረቶች መናድ ስለጀመረ ነው። ስለዚህ ይህ ህዝባዊ ድጋፍ የሌለውና ቅራኔዎች ላይ ተንጠልጥሎ ያለ መንግስት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሊወያይ የሚችለው ነገር ይህን ቅራኔ እንዴት እናድስ? የስልጣናችን መሰረት እየተናደ ነውና እንዴት እንደገና ቅራኔውን እናራግብ የሚል ነው። ያለ ጥርጥር በቅርቡ በኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ስብሰባ ላይ ያንን ከሃዲ ቀስቅሰው ኢትዮጵያን እናፈርሳለን በል ሲሉ ያ ሰው ይህንን ሲል ቀበል ብለው መነጋገሪያ እንዲሆን አደረጉ። አንዳንድ የዋሆች ወያኔን ትተው ወይኔ የሚፈልገውን ቅራኔ ወዲያው ያዙለት። ወያኔ ይህ ቅራኔ ሲነሳ እፎይ እላለሁ አስቀየስኩ (divert አደረኩ) ይላል።
የሚገርመው አንዳንድ የዋሆች ሰውየው የሚናገረውን መንፈስ እንኳን ላይመረምሩ ይችላሉ። እርግጥ ነው ባለፉት ጊዚያት ወያኔዎች ያልሆኑ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች ሪፈረንደም ያስፈልጋል ይሉ ነበር። ይህ ሰው የሚለው እኮ ኦሮምያ ሰላም ትሆን ዘንድ ኢትዮጵያ መፈራረስ አለባት መበታተን አለባት ነው። ይህንቃል በማየት ብቻ ንግግሩ የሆነ ሃይል ከሁዋላው እንዳለ ያሳያል። በመገንጠል የሚያምኑም እንዲህ አይናገሩም። ቃሎቹ ራሳቸው ለሶሻል ሚዲያ ዋና ጉዳይ እንዲሆኑ በወያኔ የተቀመሙ ናቸው። ይህንን መገምገም አለብን። በሌላ በኩል ይህ ሰው ሲናገር ጭብጨባ ነበር። የወያኔን ስልት ከ25 አመት በሁዋላ ያልተረዳ ካለ ያሳዝናል። በየመድረኩ ህዝብ የማይወደውን ነገር መናገር ሲሹ በስብሰባው መሃል እዚያና እዚያ ፈንጠር እያሉ ጥግ እየያዙ ካድሬዎች ይቀመጡና ጭብጨባና ፉጨቱን ያግሉታል። ይሄ ብዙ ጊዜ የሚያደርጉት ነገር ነው። በአጠቃላይ ይህ ኮንፈረንስ ብዙ የኦሮሞ ልጆች በሃቅ ለሃገራቸው መላ ለመሻት የኦሮሞን ህዝብ ትግል ለመደገፍ የተነሱ ሰዎች እንዳሉበት ሁሉ ወያኔም ጥሩ መድረክ ያገኘበት ጉባኤ ነበር።
ስብሰባው ዴሞክራሲያዊ መሆን እንዳለበት አምናለሁ ነገር ግን እንዲህ አይነት አገር አፈርሳለሁ የሚል ወንበዴ ሲነሳ ይሄንን ሰው አውጥቶ መጣል እንጂ ዝም ማለት አይገባም። ወያኔዎች ውጭ አገር ሲመጡና ስብሰባ ሲጠሩ ለምን ስብሰባቸውን አክቲቪስቶች ይበጠብጣሉ? አገር እያፈረሳችሁ ነው በሚል አይደለም? እንዲህ አይነቱ የወያኔ ቅጥረኛ በአንድ ስብሰባ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ሲል እንዴት ዝም ይባላል?። አንድ መዘንጋት የሌለብን ነገር በሚመጣው ህዳር ወር ላይ በሚኖረው ስብሰባ ላይ እንዲሁ ኢትዮጵያ ትፍረስ የሚሉና የሚያጨበጭቡ ካድሬዎች መዘጋጀታቸውን እንጠብቅ። አዘጋጆቹም ሃሳብ በነፃነት እንዲንሸራሸር ማድረጉን ሳይዘነጉ ለፍተው ያዘጋጁትን መድረክ የወያኔ መፈንጫ እንዳያደርጉ መጠንቀቅ አለባቸው። ሌላው መሰረታዊ ነገር መታወቅ ያለበት ዲያስፓራው ያለው ሚና ሃገር ቤት ያለውን ትግል መደገፍ ነው።
ህዝቡ ህብረትና ትብብርን ሲያሳይ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚል ሃይል ከመጣ ከወያኔ ሌላ ከቶ ማን ይሆናል። ዲያስፓራው ይህንን ህብረት ማየትና በገንዘቡ በዲፕሎማሲው መደገፍ እንጂ የህዝቡን ትግል ለማናጋት ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝም። በተረፈ እነዚህ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚሉ ሃይላት ከወያኔም በላይ የምንዋጋቸው መሆናቸው መታወቅ አለበት። በስንት የኦሮሞ ጀግኖች ደምና አጥንት የተገነባችን አገር በአባቶች መቃብር ላይ ቆሞ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ የሚል ሃይል የኦሮሞ ልጆችን መሳደብ ነው። ሁላችንን መሳደብ ነው። ከዚህ በተረፈ የወያኔን ስልቶች ሁል ጊዜም አንዘንጋ። ለምን ዝንጉ እንሆናለን?። እነሱ እኮ ስራቸውን እየሰሩ ነው። አንድ ጊዜ የጉዳይ ማስቀየሻ ስልታቸውን ካወቅን በሁዋላ እንደገና መታለል የለብንም። የቅራኔ መሰረቶቻቸውን በህብረት መስበራችንን መቀጠል አለብን። እነሱ በየጊዜው እያጠኑ የሚሰሩልንን የማስቀየሻ ጉዳዮች ስናብጠለጥል እነሱ ጊዜ አገኙ ማለት ነው።
ለወያኔ መንግስት ውሎ ማደር ወሳኝ ነው። ራእይ የላቸውም። ነገር ግን ትግሎች በዘገዩ ቁጥር የጀመሩት ቢዝነስ ይዳብራል ከሚል ነው። ተቃዋሚውን ህዝቡን ትግሉን ማዘግየት ዋና የስልጣን ዘመን ማራዘመያ መሳሪያዎች ናቸውና ኢትዮጵያውያን በህብረት በፍጥነት ትግላችንን እንቀጥል። አሁን የተቋቋመው ኮማንድ ፓስት በውጭ አገር በሚኖረው ትግል ላይ የሚኖረው ሴራ እንደዚህ አይነት ድራማዎችን እየሰሩ ሃይልን ህብረትን መበተን ነው። ይህንን አንዘንጋ። የኦሮሞ ወገኖችም የሚመጣው ስብሰባችሁ የተሳካ እንዲሆን እመኛለሁ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
geletawzeleke@gmail.com
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
lusif says
I heard the speech of that particular individual. I watched the huge clapping of hands from the audiences. In the first place the speech was nonsense. ” we do not want the palace. We late others take it. We will go to the bush and live there. ” Those sentences were part of his speech.
I could be wrong, but I might guess that the meeting was boring. The individual unexpected surprise speech might have created sudden euphoria. After a boring meeting, when a joking guy appears and say something even nonsense, the excitement of the audiences would become uncontrollable. Most of when we get bored, we feel asleep. when the person next to clap his hand you suddenly do the same thing without knowing what was going on. I am sorry, I have done it so many times. I take the whole mood that way.
One thing we should not forget is that, among the organizers and audiences there were great minds = true sons and daughters of Ethiopia, whose heart is bleeding like those brave and fearless Ethiopian youth currently fighting against tyranny.
በለው! says
»> ከሁሉ አስቀድሞ በዓለም ላይ አላግባብ ተበትነው ስለሀገራቸው ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፡ሠላም፡አንድነት፡የግለሰቦች ሰበዓዊ ደህንነት፡የብሔሮች አብሮ መኖር ፡በጋራ ሠርቶ በጋራ ማደግና መበልፀግን ለሚሹ፡ ለሚሰሩ! ለሚታገሉ!ለሚታሠሩ! ለሚሰደዱ! ለሚፈናቀሉ!የሕይወት መስዋዕትነት የሚከፍሉ ሁሉ ብርታተና ጥንካሬን አግኝተው ከፋፋይና ገንጣይን ድል አድርገው በሕግ የበላይነት ሁሉን ዜጋ በዕውቀትና የሙያ ችሎታው ተመርጦ የሚሰራና የሚያሰራ እንጂ ብዘርና ቋንቋ ተመርጦ የሚሰረስር ሳይሆን፡ ተንገዋሎ ወደኋላ የማይገፋበትሥርዓት ተመሥርቶ የህወአት/ኢህአዴግን የሚያስንቅ ሕዝባዊ ድል ተቀናጅተው የትውልዱ መልካም ምሳሌ ይሆኑ ዘንድ ምኞቴ ነው።”
» በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያ…ትውልድ፡ ይህ… ትውልድ የሰራው ጀብዱ ተብሎ ሲፈረጅ በቅርቡ የሚወሳው የኢትዮጵያ ሙሰሊሞች የመብት ጥያቄ የሁለት ዓመቱ ጨዋነት የተሞላበት የሰላማዊ ሠልፍ ግዜ የኩሩ ሕዝብ ታሪክ ሲንፀባረቅ ኢህአዴግ አሸባሪነቱን አስመስክሯል በዚህ ምግባሩንም በዓለም ታዛቢ ፊት ተዘርሯል። » ሌላው በዲሞክራሲና የሕዝብ መብት ጥያቄን አንግቦ የተነሳው የኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣት በጥናት ቆሞ ግንባሩን ሰጥቶ ገበሬው ሲፈናቀል ተገቢው ካሳ!፡ የልማት ተጠቃሚነት ይገባኛል ጥያቄ ምንም እንኳ ድምፁ ” በአትድረሱብን፡ ልዩ ነን፡ ባሕላችን፡ ቋንቋችንን ሃይማኖታችንን እንዳትበክሉ ” በሚሉ የምሁር ደናቁርት በግንጠላ አራጋቢ ፅንፈኛ የተበከለ ቅላጼ ቢሰረቅም ልብ እየገዛ ከክልል(ጋጣ)በወጣ አመለካከት የሌላውን ወገኑን ደምህ ደሜ ነው ማለቱ ብሔርና ብሔርተኝነት ገብቶት ነበር። በዚሁ አንድነት ቪዥን ላይ እንኳን “መዋለድ የጥቂቶች የግለሰቦች የቤተሰብ እንጂ የትልቁ ኦሮሞ ጉዳይ አደለም”ብለው በትንሽ መነጽር ረዳት ፕሮፍ ሁሴን ሐሰን ከኦሮሞ ተዋልጃለሁ የሚሉትን ከማጣጣል አልፈው ጥለውታል።
>>>”ጉድ ላይሰማ ስብሰባ አይጠራም!”ከሌላው ኅብረተሰብ ጋር አብሮ ለመሥራትም ይሁን እርስ በራስ በተለያየ ሐሳብና ግብ ከመጠላለፍ የዓላማ አቋም እንያዝ የሚሉ መሐል ዘመም የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎች ተሰብስበው ሌላውን ለማሰባሰብ ያደረጉት ጥረት ለሌላውም ደጋፊና ተደጋፊ ባልከፋ የኦሮሞን ልጅ ጣር ያበዛበት 43 ዓመት የሐሳብ መዋዥቅና ቀፂበ ተስፋ ነው። ለህወአት/ኢህአዴግም 25 ዓመት መደንቆር ያሰለፋቸው የደጋፊ ተደጋፊዎች ጭብጫቦ ነው። የመጀመሪያው ስብሰባ በለንደን ዋኖቹ የጫካ ሰዎች ብቅ አሉ” ዓላማና ምርጫችን ኢትዮጵያን ማፈረስ በፍርስራሹ ላይ ኦሮሚያ የምሥራቅ አፍሪካ ሃያል ሀገር መገንባትነው፡ ምንይልክ ቤተ መንግስት የምትገቡ ሂዱ በኋላ በጉርብትና ወይንም አብሮ ለመኖር እንደራደራለን!።” ጭብጨባው ቀለጠ በለው! እዚህ ጋ ከተናገረው ያስተጋባው ያሳዝናል የበለጠ አክራሪና ጽንፈኛ ነው። …(ሀ)አጫብጫቢው (ለ) “ተጨበጨበ ማለት ተስማማ ማለት አይደለም…”ሃገር ገንጣይ ኦሮሞ ሳይሆን ወያኔ ነው…(ህወአት፡ኦነግ፡ሻዕብያ፡ኦብነግ)ምንና ምን ናቸው? ልዩ ዘር አንድ ዓላማ(ራዕይ)የጋራ ጠላታቸው አማራ! ኦርቶዶክስ! ኢትዮጵያ!!…”ኢትዮጵያ የሚለው ትክክለኛ ቦታ ኦሮሚያ ነው ከ11 ሚሊዮን በላይ ልዩ ልዩ ብሄሮች ይኖሩበታል።(በአሜሪካ 11ሚሊየን የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን ማለት ነው ይህ በታኝና አፍራሹ ዶ/ር ብጤ የኦሮሞ ዶናል.ትራፕ መሆኑ ነው? ወይ ማስፈራራት!?
** ከዚህ በፊት “ዘጠና ዘጠኝ ሙስሊም ባለበት ክልል ማንም ክሪስቲያን ደፍሮ አይናገርም ቀና ቢል አንገቱን በሜንጫ ነው የምንለው” ላለው ጀዋር መሐመድ የኢሳት አማሮች ፖለቲካ ተንታኝና አስተማሪ መቼም አይገባቸውም እንዳለው ታዋቂው አበበ ገላው “ጃዋር አፉ አዳልጦት ነው ብሎ አማርኛን በአማርኛ ለመተርጎም ሲሯሯጥ ሌላው አክቲቭ አብርሃ ደስታ ደግሞ “ድረስ ተብዬ ነው ጀዋር በጣም የማደንቀው ፖለቲከኛ ነው ሐሳብና ፍላጎቱን እጋራለሁ”አለን። አብሮ እየተላፉ ትግል ለመላላጥ በሉ!።
*** ወጣም ወረደ! ገና ይወጣል ተብሎ የሚገመትና የሚጠበቅ የሚታለም!ቢኖር ባለፉት ሳምንት ለኢትዮጵያ አንገቴን! ትበተናላችሁ እንጂ ኢትዮጵያ አትበታተንም! ኦሮሞዎችም ሆኑ ከሌላ ብሔር የተገኙ የኦሮሞ ዘሮች ሁሉ ሕመምና ድንጋጤያቸው ልብ የሚሰብር ቢሆንም በአንዲት ቅድስት ሀገረ ኢትዮጵያ ያላቸው ጽናትና ኩራት ግን “ነብር ዥንጉርጉርነቱም ኢትዮጵያዊም ኢትዮጵያዊነቱን አይቀይርም!”የሚለው ከበቂ በላይ ተመስክሯል አኩሪ ገድል ነው። ዙሪያውን ቁጣቸው የገነፈለ የደቡብ፡ የምሥራቅ፡ የምዕራብ፡የሰሜን፡የመሐል የውጭ ሀገር ነዋሪዎችና ተወላጆች ሁሉ ጠንክሩ!አንድነት ኅይል ነው!! ህወአት ከዚህ ብዙ ሊማር ሊነቃ ይገባል።ጠያቂ ብቻ ሳይሆን ሥልጣን ነጣቂ በሀገሩ የማይደራደር ነቄ ትውልድ ተፈጥሯልና “በአካባቢው ሁሉ ቀፎ ሠቅላችሁ አይተንባችሁ ጉጉት አድሮብን ተማሩ ነው ያልናችሁ” ሲግባቡ ማልቀስ የለም መፈንደቅ ማጨብጨብ እንጂ በለው!በቸር ይግጠመን
>.>