• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጎሠኛነት በባዶ ሜዳ!

November 19, 2016 03:51 am by Editor 6 Comments

በተለያዩ የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የሚደረገው ውይይትና ክርክር እንደተጠናቀቀ ተቆጥሮ የአማራና የኦሮሞ ጎሠኛነት ትልቁ አንገብጋቢ ጉዳይ እየሆነ ነው፤ (ስለ ኢትዮጵያ ለማያውቅ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ከጠሩና ከጸዱ አማራና ኦሮሞዎች በቀር በአገሪቱ ውስጥ ሌላ ሰው ያለ አይመስልም!)

ጎሠኛነት ጉዳያችን ያልሆነው ኢትዮጵያውያን የዳር ተመልካች መሆኑ እየሰለቸን ነው፤ ምንም እንኳን አማራና ኦሮሞ የተባሉት ጎሣዎች በብዛት ከሁሉም ቢበልጡም ከሰማንያ በላይ የሚሆኑ ጎሣዎች እንደሌሉና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቃል እንደሌላቸው ተደርጎ የሚጎነጎነው የሚስዮናውያንና የስለላ ድርጅቶች ታሪክ ለኢትዮጵያውያን ባዕድ ነው፡፡

ሌላው የሚያስደንቀውና ዓይን ያወጣው ነገር እነዚህ ኢትዮጵያን በጠዋቱ ለመቃረጥ እየተነታረኩ ያሉ በአማራና በኦሮሞ ጎሣዎች ስም መድረኩን የያዙት ሰዎች በውጭ አገር የሚኖሩ፣ እነሱ ሌሎች መንግሥታትን የሙጢኝ ብለው ከወላጆቻቸው ባህልና ታሪክ ጋር ማንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው፣ ልጆቻቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው የውጭ አገር ሰዎች ናቸው፡፡ የሚናገሩትና የሚሰብኩት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ላለነው፣ አገራችን ያፈራችውን ግፍና መከራ እየተቀበልን ለምንኖረው የነሱ ንትርክ፣ ውይይትና ክርክር ትርጉም የለውም፡፡ እዚያው በያገራቸው እየተነታረኩ ዕድሜያቸውን ጨርሰው መቀበሪያ ይፈልጉ፤ ሲመች ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ሳይመች የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው፤ ሲመች የአንዱ ጎሣ አባል ናቸው፣ ሳይመች ሌላ ናቸው፤ እነሱ በምጽዋት እየኖሩ እዚህ በአገሩ ጦሙን እያደረ ስቃዩን የሚበላውን በጎሠኛነት መርዝ ናላውን ሊያዞሩት ይጥራሉ፡፡

የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሣ ለያይተው የሞተ ታሪክ እያስነሡ ከአሥራ አምስት ሺህና ከሃያ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት አዛኝ ቅቤ አንጓች እየሆኑ ተነሥ-አለንልህ! እያሉ በአጉል ቀረርቶ ጉሮሮአቸው እስቲነቃ የሚጮሁ ሰዎች ቆም ብለው ቢያስቡ እኛና እነሱ ያለንበትን የአካል ርቀት ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰበም በመንፈስም እጅግ መራራቃችንን በመገንዘብ አደብ መግዛት ይችሉ ነበሩ፡፡ የሥልጣን ጥም ያቅበዘበዛቸው ሰዎች የሚያስነሡት አቧራ በኢትዮጵያ የዘለቄታ መሠረታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር እንዳይችሉ፣ እንዳይደማመጡና እንዳይተያዩ እያደረገ ነው፡፡

አገር-ቤት ያለነውን አላዋቂ ሞኞች ለማሳመን ስደተኞች በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን እያለሙ ያድራሉ፤ እኛ የምንኖረውን እንንገራችሁ ይሉናል፤ እኛ የምናስበውን እንምራችሁ ይሉናል፤ እኛ የሚሰማንን እንግለጽላችሁ ይሉናል፤ በአጭሩ እኛን የእነሱ አሻንጉሊቶች አድርገውናል፤ የእኛን መታፈን ከእነሱ ስድነት ጋር እያወዳደሩ፣ የእኛን የኑሮ ደሀነት ከእነሱ ምቾት ጋር እያስተያዩ፣ የእነሱን ቀረርቶ ከእኛ ዋይታ ጋር እያመዛዘኑ ያላግጡብናል፤ ይመጻደቁብናል፤ በስደት ቅዠት ያገኙትን ማንነት በእኛ ላይ ሊጭኑ ይዳዳቸዋል፡፡

ወላጆቹም እሱም የተወለደበትን አገር ትቶ በሰው አገር ስደተኛ የሆነ፣ የራሱን አገር መንግሥት መመሥረት አቀቶት የሌላ አገር መንግሥትን የሙጢኝ ያለ፣ ማንነቱን ለምቾትና ለሆዱ የለወጠ፣ የተወለደበትንና ያደገበትን ሃይማኖት በብስኩትና በሻይ የቀየረ፣ ተጨንቆና ተጠቦ በማሰብ ከውስጡ ከራሱ ምንም ሳይወጣው ሌሎች ያሸከሙትን ጭነት ብቻ እያሳየ ተምሬለሁ የሚል፣ የመድረሻ-ቢስነቱ እውነት የፈጠረበትን የመንፈስ ክሳት በጭነቱ ለማድለብ በከንቱ የሚጥርና የሚሻክራን ስደት ለማለስለስ በሚያዳልጥ መንገድ ላይ መገላበጡ አያስደንቅም፤ እያዳለጠው ሲንከባለል የተነሣበትን ሲረሳና ታሪኩን ሲስት ሌሎች እሱ የካዳቸው ወንድሞቹና እኅቶቹ ከፊቱ በኩራት ቆመው የገባህበት ማጥ ውስጥ አንገባም ይሉታል፡፡

የአሊን፣ የጎበናን፣ የባልቻን፣ የሀብተ ጊዮርጊስን፣… ወገንነት ክዶና ንቆ ራቁቱን የቆመ፣ እንደ እንስሳት ትውልድ ከዜሮ ለመጀመር በደመ-ነፍስ የሚንቀሳቀስ! ድንቁርናን እውቀት እያስመሰለ ሞኞችን የሚያታልል፣ ወዳጅ-ዘመድን ከጠላት ለመለየት የሚያስችለውን የተፈጥሮ ችሎታ የተነፈገ፣ አባቱን ሲወድ እናቱን የሚጠላ፣ እናቱን ሲወድ አባቱን የሚጠላ፣ ከወንድሙና ከእኅቱ ጋር የማይዛመድ ባሕር ላይ እንደወደቀ ቅጠል የነፋስ መጫወቻ ሆኖ የሚያሳዝን የማይታዘንለት ፍጡር፣ በጥገኛነት የገባበትን ማኅበረሰብ ማሰልቸቱ የማይገባው የኋሊት እየገሰገሰ ከፊት ቀድሞ ለመገኘት የሚመኝ የምኞት እስረኛ ነው፡፡

አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራልያ በጥገኛነት ታዝሎ፣ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ከኢትዮጵያ ስለመገንጠል ይለፈልፋል! ተገንጥሎ የወጣ ከምን ይገነጠላል? ልዩ የነጻነት ታሪክ ባስተላለፉለት አባቶቹና እናቶቹ እየኮራ፣ በጎደለው እያፈረ፣ የአምባ-ገነኖችን ዱላ እየተቋቋመ በአገሩ ህልውና የወደፊት ተስፋውን እየወደቀና እየተነሣ የሚገነባው ኢትዮጵያዊ በፍርፋሪ የጠገቡ ጥገኞችን የሰለለ ጥሪ አዳምጦ የአባቶቹን ቤት አያፈርስም፤ አሳዳሪዎች ሲያኮርፉና ፍርፋሪው ሲቀንስ፣ ጊዜ ሲከፋና ጥቃት ሲደራረብ የወገን ድምጽ ይናፍቃል፤ ኩራት ራት የሚሆንበት ዘመን ይናፍቃል፡፡

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ኅዳር/2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Wogene says

    November 19, 2016 03:59 am at 3:59 am

    Brilliant! Thank you, Prof. Mesfin.

    I do hope that those shameless fanatic so-called Amaras and Oromos will give heed to your advice and simply be satisfied with being Ethiopian. They should recognize the fact that persuing a policy of ethnicism/tribalism such as the case of Jewar Mohamed is the same as the current policy of TPLF. Shame on them!!

    Reply
  2. Sam-Dan says

    November 19, 2016 05:13 am at 5:13 am

    Pro. Mesfen, Let me ask you some questions, in your own word you have denied the existence of the Amhara people in Ethiopia, why today you are concerned regarding the organisation of The Amhara people? Do you think the Amhara people should do nothing until they vanished from the face of the earth by their deadly enemies? Even though the Amhara people are organised in order to defend themselves, they never deny their Ethiopian identity and never abandon their love for Ethiopia. To my surprise, you tried to assimilate the hero Amhara people who stand for the unity Ethiopia with the extremist Oromos who seek the destruction of Ethiopia. Do you think, is this a fair comparison for the people of Amhara who love their mother land – Ethiopia? How you dare to insult millions Ethiopian diaspora and tried to deny their Ethiopian identity? These diaspora Ethiopians who are doing their best for the freedom of Ethiopian people are exposing the evil deed of weyanie to the world and contributing their part in the struggle against the weyanie junta. You have told us your origin is enticho – Tigray, is that the reason why yod don’t care about the systematic genocide of the Amhara people caring out by weyanie? From now on you need to now that the Amhara people have awaked about the hidden agenda of the enemy and have determined to organise and defend themselves. No conspiracy will stop the Amahara people from organising and self defending, eventually struggling for the unity of Ethiopia.

    God bless Ethiopia

    Reply
  3. Tazabi says

    November 19, 2016 09:04 am at 9:04 am

    What is new about ethnic Ethiopian politics now Professor? What is really bugging you inside. I will answer this later.
    We have been under ethnic federation Woyane has created the past 25 years where all the ruling EPRDF parties are operating under ethnic banner in addition to many registered ethnic parties that competed for elections in Ethiopia. We also have ethnic parties that do not have legal status by Woyane regime where some have been around for over 40 years, to name a few ethnicities, Afar, Annuack, Benshengul, Gambela, Ogaden, Oromo, Sidama, Tigray.
    Now coming on why is it bothering the Professor to write this article, the only key ethnic parties added recently are the Amhara opposition parties that do not have a legal ground to operate under Woyane. Professor Mesfin has already expressed his families came from Enticho Adwa on his recent interview with VOA. If this is true, my question to the Professor is; Why are you troubled that the Amharas are organized? How long can the Amhara be victims and perish without having a group that defends it. We all know that the TPLF created Amahara party has been infiltrated by the TPLF and most of their key leaders are not Amharas.
    To give you a background on why the first Amhara civic party “Moresh Wogene” started; it is because of the killings and displacement of Amharas in Bench Maji Zone that is under Ethiopian Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region (SNNPR). Ato Shiferaw Sheguate who was the leader of the region got the blessing of Meles Zenawi at the time for his actions. We all remember Meles Zenawi the ruthless speech that gave the blessing accusing the Amhara peasants at the parliament at the time. It also did not stop there, it continued in Benshengul region where a major genocide has been made on the Amhara peasants. Similarly, the notable Dr. Asrat has created AAPO to represent the voiceless Amharas after the genocide of Amharas in various regions of Ethiopia.
    Saying the above, it is my belief and hope that all ethnic parties will eventually assemble under the Ethiopian banner to create several Ethiopian parties in the near future. Ethnic federation will be abolished for better regional administration federation. The previous provinces of the Haile Selassie and the Derg administration are good place to start with some timely arrangement.

    Reply
  4. ተስፋዬ says

    November 19, 2016 07:43 pm at 7:43 pm

    በጣም ተማርን ከሚሉ፣ በሠለጠነው ዓለም በብኃነት ኮሽታ ሳይሰማ ሰዎች ሁሉ የተፈጥሮ ነጻነታቸውንና የማንነታቸው መገለጫ የሆነው ባሕልና ቋንቋ እንደፈለጉ በሚያገልጡበት አገር ተቀምጠው፤ ዓይናቸው እያየ፣ ጆሮአቸው እየሰማ፣ እውነታውን እየተነፈሱት፣እያጣጣሙት ያሉት እነርሱ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ካልፈረሰች እኛ ሰላም አናገኝም፤ እምቢ ካሉ አፈራርሰናት እንሄዳለን የሚለውን የሚናገሩ መሪዎች እውነት የእውቀት ፍላጮች፣ የሥልጣኔ ማሳያዎች ናቸው ብሎ መገመት እፍረት ነው፡፡ እኔ ሰዎቹ ጆሮ እስከሚያደነቁር ከሚናገሩለት ወገን ነው የተወለድኩት፤ ግን እነዚህን ሂትለር እብደቱ ሲጀመረው ያደረገውን ምልክት እያሳዩኝ እነዚህን እንደዜጋም ሆነ እንደ አሳቢ ሰው ለመቁጠር እቸገራለሁ፡፡

    Reply
  5. Tesfa says

    November 21, 2016 03:19 am at 3:19 am

    የሃገራችን ሁኔታ ስብጥሩ በየቀኑ እየጨመረ ውሉን አግኝቶ ቋጠሮውን ምፍታት አለመቻሉ የብዙሃን ችግር ለመሆኑ ምሥክር አያሻም። ሃገር በዘርና በጎሳ ተከፍላ ሃገር መሆን እንደማይቻልም ያለፈና የቅርብ ቀን ታሪክ ይመሰክራል። ሆኖም ግን ወያኔ ለእኔ ብቻ ብሎ ራሱን ለ 25 ዓመታት አለቃ በማድረግ ሃገሪቱን ወደ ህብር አመራር አለማራመድ ዛሬ በውጭና በሃገር ውስጥ ላለው ግርግር ምክንያት ነው። በተለይም በአማራው ህዝብ ላይ ያለው ጥላቻ ሰው በየወገኑ እንዲሰለፍ ግድ ሆኖበታል። መነቀፍ ያለበት ወያኔና ኢትዮጵያን አፍርሰን ሃገር እንመሰርታለን የሚሉ የጠባብ ብሄርተኛ በሽተኞ እንጂ ዘርና ወገኑ በወያኔ ጥይት ሲረግፍ እሳትን በእሳት ለመከላከል የሚሞክሩ ሃገር ወዳድ የብሄር ስብስቦች መሆን የለባቸውም። ሃገሩን የሚወድ፤ ሰላምን የሚሻ፤ ተገኘ የሚባልልትም እድገት እንዳይንኮታኮት የጠነከርን ነገር ማርገብ የሚችለው መንግሥት ነበር። ወያኔ ግን መንግስትም አይደለም። መንግስትም የለም። ሁሉ የፈለገውን አስሮ፤ አፍኖ፤ ገድሎ፤ ዘርፎ የሚኖርባት መንግሥት አልባ ሃገር ለመሆኑዋ በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚፈጸመው በደል ያመለክታል። በዚህ ግፍ የተነሳ ሰዎች በዘርና በጎሳ በመሰባሰብ ከወያኔ ጋር ግብግብ ቢገጥሙ የሚያስገርም አይሆንም።
    ለህዝብ እንቆረቆራለን የሚሉ የተማሩና ከገዥው ትውልድ ሥፍራ ያልሆኑ በየምክንያቱ እንደሚመነጠሩ እናውቃለን። በቅርቡ በቢሮዋ ውስጥ ሞታ ተገኘች ተብሎ አፈር የተመለሰባት የባህዳርዋ የፓርላማ ተወካይ የቅርብ ጊዜ ሰለባቸው ናት። ታዲያ ፕሮፌስር መስፍን ከሃይለሥላሴ እስከ ወያኔ ግዛት እድሜ ካስተማራቸው ተነስተው አፍር የተመለሳቸውን እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ያሉት በወያኔ ሞት የተፈረደባቸው በአማራ ህዝብ ላይ የሚሰራውን በደል መቃወማቸውና የሞትን ጽዋ መቀበላቸው ዘርኛ አያረጋቸውም። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህዝብ ገንዘብ ከባንክ የሚሰረቅበት፤ የቡና ማከማቻ ተሰብሮ ወያኔ በአቀነባበረው የስርቆት ዘመቻ ለዓለም ገቢያ የሚቅርብበትና ትርፉ ለወያኔ ቆንጮዎች የሚከፋፈልበት ሥድ ያሰራር ዘዴ የሰፈነባት ሃገር ናት። ስርዓት አልባ ሃገር ናት።
    ታዲያ በውጭም ሆነ በውስጥ ሰው በወያኔ ላይ ቢያመጽ የሚያስገርም አይሆንም። በዘርም ሆነ በጎሳ ሰው ቢሰለፍ አሰላለፉ ሃገርን እስከመገንጠል እስካለሆነ ድረስ ችግር የለውም። በመሰረቱ ሃገር እንዲፈራርስ ድልድይ የሰራው ወያኔ ነው። በጠበንጃ አፈሙዝ የጸደቀው ህገመንግሥት መገንጠልን ይፈቅዳል። ቋንቋን ሁሉ ደባልቆ ሰው እንዳይግባባ በየዘርህ ብሎ ክልል ያበጀው ወያኔ ነው። ጎሰኝነት በባዶ ሜዳ የጀመረው ወያኔ ነው። በርቱ፤ በቋንቋ ተደራጁ እያለ የህዝባችንን ሃበሳ ያበዛው። ዛሬ በሃገራችን ውስጥ ብሄራዊ የሆነ የቋንቋ አጠቃቀም ባለመኖሩ በፍርድ ቤት፤ በት/ቤት በመንገድና በሆቴሎች አስተርጉዋሚ ያሻል። እንደ ቀድሞዋ ደቡብ አፍሪካ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የተዋቀረችው በክልል ነው። ከለለ ማለት አገደ ማለት ነው። ገና ከጅምሩ ወያኔ ዘርኛና ሃገር አፍራሽ ለመሆኑ በተባበሩት መንግሥታት ፊት የኤርትራን መገንጠል ተቀበሉልኝ ብሎ ሲማጸን ያየ ሁሉ ለሃገር የማይገደው ወልጋዳ የጠባብ ብሄርተኞች ጥርቅም እንደሆነ ያሳያል። ስለሆነም ፕሮፌሴሩ ትኩረታቸው በወያኔ መሰሪ አሰራር ላይ ቢሆን የበለጠ ፍሬአማ ያደርገዋል። በውጭ በጎጥና በጎሳ ራሱን አሰባስቦ የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚሻ ሁሉ የቀን እንቅልፍ እንጂ እውንነት አይኖረውም። 99 መርፌ አንድ ማረሻ አይወጣውና! ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራው እንቅልፍ አይነሳኝም። አይሆንምና!!

    Reply
  6. Wogene says

    November 22, 2016 05:19 am at 5:19 am

    ዘረኞች ሁሉ; ኦሮሞ ነኝ ባዩ; በተለይ ጀዋር መሐመድ; ቆም ብላችሁ የዶር. መስፍንን መልእክት በጥንቃቄ ተመልከቱ! የትግራይን ጸያፍ ዘረኛነት በናንተ አሳፋሪ የኦሮሞና የአማራ ጎጠኝነት እየመነዘራችሁ መሆኑ ይግባችሁ:: ነገ ሳይሆን ማፈር የነበረባችሁ ዛሬ ነው; ሕሊናና አንጎል አለን ካላችሁ:: በሐምበርገር የጠረቃውን ሆዳችሁን እያስቀደማችሁ; ደሀውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር እየከፋፈላችሁ ባታጫርሱት አይሻልም ወይ? እባካችሁ ትንሽ እንኳ አስቡ; አሰላስሉ! እነጀዋርን የምትደግፉ ሁሉ እባካችሁ ጥቂት አስቡ:: እርግፍ አድርጋችሁ ልትጠሏቸው የሚገባቸው ፍጡሮች ናቸውና!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule