የአባይን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የጁንታው ቅጥረኛ ኃይል መደምሰሱ የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።
የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮሎኔል ሰይፈ ኢንጊ ቅጥረኛው ቡድን የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ የሞከረ ቢሆንም መቋቋም ተስኖት ተበታትኗል ሲሉ ተናግረዋል።
ጠላት አሳቻ ስአት ጠብቆ አካባቢውን ለማተራመስ ቢንቀሳቀስም የጠላትን እንቅስቃሴ ከመነሻው በንቃት ሲከታተሉ የነበሩት የመከላከያ ሰራዊታችን ክፍሎች ተቀናጅተው እርምጃ ወስደውበታል ብለዋል ።
የጠላት ኃይል በጀግናው ሰራዊት የበላይነት ተወስዶበት ሀምሳ የሽብር መልዕክተኞች ሲደመሰሱ ፣ከሰባ በላይ መቁሰላቸውን አስተባባሪው ገልፀዋል ።የተረፈው ኃይል ደግሞ አግሬ አውጪኝ በማለት መፈርጠጡንም ተናግረዋል።
የጥፋት ሃይሉ ሲጠቀምባቸው እና ለእኩይ ስራው ሲያዘጋጃቸው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች ፣ ፈንጂዎች የወደሙ ሲሆን የተቀሩት በጀግናው ሰራዊት በቁጥጥር ስር ገብተዋል ።
በአሁኑ ስአት በአካባቢው ጀግናው የመከላከያ ኃይሉ ፣ እግረኛና ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች እንዲሁም የክልል ልዩ ኃይሎች አስፈላጊውን ዝግጁነት በማረጋገጥ ግዳጃቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮሎኔል ሰይፈ ኢንጊ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለከታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply