• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከ21 ዓመት በኋላ ህወሓት ተነፈሰ!!

September 16, 2012 01:57 pm by Editor 9 Comments

የመከላከያውንና የደህንነቱን የስልጣን ርካብ ከቀድሞው ይልቅ ቆንጥጦ ለመያዝ እየተረባረበ ያለው ህወሓት በግልጽ ከሚታየው የፖለቲካ አመራር ወንበሩ ተነሳ። ለ21 ዓመታት የድርጅት፣ የጠ/ሚኒስትርነትና ቁልፍ የስልጣን መደቦችን ተቆጣጥሮ የኖረው ህወሓት ሁለቱን ግዙፍ ወንበሮች ለማስጠበቅ በድርጅትና በጎንዮሽ ትስስር ያካሄደው ዘመቻ አልተሳካለትም።

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አቶ መለስን የሚተካ መሪ መሰየም አለመቻሉን አቶ በረከት ስምኦን ያሳበቁበት ህወሓት በቀጣዩ ምርጫም ወንበሩን እንደማያገኘው አቶ በረከት በግልጽ ተናግረዋል። ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ ሁለቱ አዲስ ተሿሚዎች በስልጣናቸው እንደሚቀጥሉ በይፋ ተናግረዋል።

የኢህአዴግን የአመራር ወንበር ላለማጣት ያደረገው ሙከራ በየድርጅቶቹ በተካሄደ የተናጠል ስብሰባ ተሞክሮ ሊሳካ እንዳልቻለ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። በስም ተጠቅሰው ኢህአዴግን እንዲመሩ የቀረቡትን የህወሃት ሰዎች አንቀበልም ያሉት አባል ድርጅቶች በተቃራኒ በቀጣዩ የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ መተካካቱ በተዋጽዖ የተመጣጠነ እንዲሆን የሚያሳስብ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል። ከአቻ ድርጅቶቹ በተጨማሪ አሜሪካ ያስተላለፈችው መመሪያም ተጽዕኖ መፍጠሩ ተገምቷል።

ለዚህ ይመስላል አቶ በረከትና አቶ ሬድዋን ሁሴን በሂልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ላይ “አቶ ኃይለማርያም የራሳቸውን ካቢኔ የመመስረት ሙሉ መብት አላቸው” በማለት አቶ በረከት የቀድሞው ካቢኔ ሊፈርስ ወይም ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚችል አመላክተዋል።

የህወሓት/ኢህአዴግን አካሄድ በመገመትና በመተንተን የሚታወቁት ረዳት ፕሮፌሰር መድኔ ታደሰ ሴፕቴምበር 14 ለአሜሪካ ሬድዮ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል በሰጡት ማብራሪያ አሁን ተፈጠረው አጋጣሚ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ለውጥ ማስከተሉ አይቀሬ መሆኑን አስረድተዋል። አያይዘውም መለስ በሌሉበት ሁኔታ የቁጥጥር አስተዳደር ማራመድ እንማይቻልም አመልክተዋል። ከቁጥጥር ይልቅ ወደ መመካከርና አብዛኞችን ወደሚያሳትፍ አመራር እንደሚለወጥ ተናግረዋል።

ተተኪ ሊቀመንበር ለመሰየም ሲሳብና ሲጎተት የከረመው ኢህአዴግ ራሱ ካወጀው የአቶ መለስ ህልፈት ከሃያ ስድስት ቀናት በኋላ አስቀድሞ በስፋት የተተነበየውን ሹመት ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል አድርጎ ሰይሟል። አቶ ኃይለማርያም “ምደባው የመስዋዕትነት ነው” ሲሉ ለመንበራቸው ያላቸውን ቁርጠኛነት ለጓዶቻቸው አረጋግጠዋል። ህወሓትን ወክለው አቶ ስዩም መስፍን ለምርጫ ቢወዳደሩም ድምጽ በማጣታቸው ሳይመረጡ ቀርተዋል።

ብቸኛው የመረጃ ምንጭ ኢቲቪ መስከረም 4 ቀን 2005 ዓ ም በምሽቱ ሶስት ሰዓት የዜና እወጃው ቀንጭቦ ባቀረበው ምስል አቶ ኃይለማርያምና ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንን በኢህአዴግ ምክር ቤት የአመራር ወንበራቸው ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ታይተዋል። አቶ ኃይለማርያም ይህን ጊዜ ነበር “ምድባው ለመስዋዐትነት ነው፤ ምደባው ህዝብ ከኢህአዴግ የሚጠብቀውን  በሙሉ ለመፈጸም ነው፤ ምደባው በሙሉ በኢህአዴግ ምክር ቤት አባላትና በናንተ ሙሉ ምክር ከኋላና ከፊት በምታደርጉት ጥረት የተደረገ ነው …” በማለት በተሳሰረ አንደበት የተናገሩት።

ሙሉ የኢህአዴግ ምክር ቤትን ያመሰገኑት አቶ ኃይለማርያምና አቶ ደመቀ ለደንብ ያህል ቃለ መሃላ መፈጸም ብቻ የሚቀራቸው ጠ/ ሚኒስትር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን አቶ በረከት ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ በግልጽ ተናግረዋል። በዚሁ መሰረት በወስከረም ሶስተኛ ሳምንት አቶ ሃይለማርያምና አቶ ደመቀ የአዲሱን በትረ ሹመት ስርዓተ ፓርላማ ያከናውናሉ። የአቶ ሃይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬም ቀዳማዊት እመቤት ሆነው አራት ኪሎ ከነቤተሰቦቻቸው ይዘልቃሉ።

ህወሓት አቶ ስዩምን አቅርቦ መሸነፉን ኢቲቪ አሳብቋል። 180 አባላት ያለው የኢህአዴግ ምክር ቤት ያካሄደውን ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ቅዳሜ ምሽት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፈው ኢቲቪ ድምጽ ቆጠራውን ሲያሳይ የአቶ ስዩም መስፍን ስም በድንገት ታይቷል። የጎልጉል ዘጋቢ ከአዲስ አበባ እንዳረጋገጠው ኢቲቪ የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት ለውጪ አገር ዜጎችና ዲፕሎማቶች ለማሳየት ባሳየው ፊልም ላይ የታው የድምጽ መስጫ ወረቀት ሶስት ስሞች ያሉበት ነው። የአቶ ስዩም ስም በሶስተኛ ደረጃ ላይ ታይቷል። አቶ በረከት ስም አይጥቀሱ እንጂ ሶስት እጩዎች ለውድድር ቀርበው እንደነበር ማረጋገጣቸውን አገር የሰማውን ወሬ “ሰበር ዜና” ሲል ያጋጋለው ሪፖርተር አስታውቋል።

ለጊዜ ማግኛ የአቶ መለስ ህልፈት ምስጢር ተደርጎ በድርጅት ውስጥ ለውስጥ የነበረው ሽኩቻ ከረገበ በኋላ በጋራ የተያዘውን አቋም ሲያንከባልል የቆየው የኢህአዴግ ምክር ቤት ህብረተሰቡንና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን የሚማጸን መልዕክት አስተላልፏል።

“በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለምትንቀሳቀሱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች” በማለት ኢህአዴግ በመግለጫው ያልተለመደ ውዳሴ አቅርቧል። “በጽሁፍና በአካል በመገኘት በሃዘናችን ስላጽናናችሁን እናመሰግናለን” ያለው መግለጫው በማያያዝ ስለ ምርጫና ስለ አብሮ መስራትም ጠቁሞ አልፏል።

“…አብረን እንሰራለን። በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ በሰለጠነ መንገድ ለመወያየት ዝግጅታችንን እንገልጻለን” ሲል ቃል የገባው ኢህአዴግ ተቋማዊ ለውጥ ስለመደረጉ የሰጠው ፍንጭ ግን የለም። አሁን በስራ ላይ ያለውን ምርጫ ቦርድ ይዞ ኢህአዴግ ስለ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ መናገር አይችልም። የመድረክ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ገብሩ አስራት ህወሓት/ኢህአዴግ በትግራይ ተቃዋሚዎችን ከነድራሹ ለማጥፋት እየሰራ መሆኑን በተለይም ህወሓት ይህንኑ በተደጋጋሚ በይፋ መግለጹን ባለፈው አርብ ለአሜሪካ ሬድዮ ተናግረዋል። በዚህ መነሻ የኢህአዴግ የእንተባበር ጥሪ የተለመደ ማደናገር እንደሆነ ተደርጎ ተወስዶበታል።

የፖለቲካውን ወንበር የተነጠቀው ህወሓት የጦር ሃይሉን፣ ፖሊስንና ደህንነቱን ቆንጥጦ መያዙ አገሪቱን ወደ ወታደራዊ አስተዳደር እንዳያመራት ስጋት የገባቸው ክፍሎች አቶ ኃይለማርያም የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥነት ይስሙላ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮቹን ጠቅሶ ከምርጫው ሶስት ቀን አስቀድሞ ህወሓት በፖለቲካው የአመራር ሰጪነቱ ሚና እንዳከተመበት በመረዳቱ የጦር ኃይሉና ደህንነቱ ላይ ያለውን አቅምና ኃይል ለማጠናከር ትኩረት መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል። ከተሿሚዎቹም መካከል የመጀመሪያዋን ሴት ጄኔራል (አስካለ ብርሃኔ ተድላ) ከአቶ መለስ ትውልድ ቦታ አድዋ ማድረጉ ለአብነት የሚጠቀስ ነው፡፡

በተመሳሳይ ዜና በስፋት ሲወራ ስለሰነበተው የሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ጉዳይ አቶ በረከት ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። አቶ በረከት ቅዳሜ ምሽት በሒልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጣይ ይሾማሉ ስለተባሉት ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች  የተጠየቁት ከጋዜጠኞች ነበር። ለጥያቄው መልስ የሰጡት አቶ በረከት “ሶስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር የለም። የሚወራው ሁሉ ወሬ ነው። ኢህአዴግ ደግሞ በወሬ አይመራም” በማለት ትንበያውን አጣጥለውታል። አቶ በረከት ይህን ይበሉ ጉዳዩ እንደ አቶ መለስ ሞት ሰነባብቶ ይፋ ላለመሆኑ ማረጋገጫ የለም።

(በጎልጉል ሪፖርተር)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. eshetu says

    September 17, 2012 12:49 am at 12:49 am

    ብዙ ሰወች የሀይለማሪያምን ና የደመቀን ስም ስልጣን ቦታ ላይ መምጣት እንደትልቅ ለውጥ በማየት exited የሆኑ ሰወች በዝተዋል ለኔ ግን ኣዲስ ነገር ይመጣል ብየ ኣልጠብቅም። በመጀመሪያ የተመረጡት ሰወች ራሳቸው የመለስን እቅድ ና አላማ እንቀጥላለን እያሉ ፎክረዋል። እነዚህ ሰወች ከ10 አመት በላይ ከመለስ ስር ቁጭ ብለው እየታዘዙ ሳይቃወሙ የሰሩ ሰወች ናቸው በዚህ ላይ የኢህአዴግ ስርአት አለ ኣልተቀየረም በሽታው ያለው ከስርአቱ ነው አቶ ሃይለማርያም ይህን መቀየር ይችላሉ? የምናየው ይሆናል ። እኔ በጣም እማዝነው ግን የአቶ ደመቀ መኮነን ወደ ከፍተኛ ስልጣን መምጣት በጣም ያሳዝናል። ብዙ ሰወች በኢትዮጵያ ላይ የሰሩትን ወንጀል የሚያውቁ ኣይመስለኝም። ከጎንደር ለሱዳን በነጻ ተቆርሶ የተሰጠውን የኢትዮጵያ መሬት የአማራ ክልል ፕረዘዳንት ኣቶ ኣያሌው ኣልፈርምም ሲሉ ለመለስ ታዛዥ በመሆን የፌረሙት በዚያን ወቅት የአማራ ክልል ምክትል ፕረዘዳንት የነበሩት ኣቶ ደመቀ መኮነን ነበሩ። አሰብን አሳልፎ ክመስጠት ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ክህደት መሆኑን ሁሉም የሚያስታዉሰው ነው።ከዚህ ሰው ምንም ኣትጠብቁ። we have been looking for a leader who have an ethiopian mentality do these people have an ethiopian mentality?

    Reply
  2. abebe says

    September 17, 2012 02:17 pm at 2:17 pm

    It is at least a releif to see new faces in Ethiopia’s top politcal postions. Both Haielemariam and Demeke are the most harmless individuals with in the ranks of EPRDF. Though these two individuals will not have the gut to question the dominance of TPLF in the regime, their existence will at least force TPLF to share some of its top secrets with these two aliens. But the democratic forces need to foster their pressure for political reform rather than speculating on the possible reforms to be made by these two mediocrity leaders that came to power due to mere chance rather than merit.

    Reply
  3. Kinfe-M. Abay says

    September 17, 2012 03:39 pm at 3:39 pm

    Please check again whether the 3rd. candidate was really Seyoum Mesfin. Tesfaye G/ab. at least mentions another name on EMF!? Sofian Ahmed?!

    Reply
  4. ዳዊት says

    September 18, 2012 12:19 am at 12:19 am

    ሶስተኛው እጩ አቶ ስዩም ስለመሆናቸው ጎልጉል ኢቲቪን ጠቅሶ ” አየሁ ” ያለውን ነው ያሰፈረው። አቶ ተስፋዬ ደግሞ ከምንጮቻቸው ” ሰማሁ” ያሉትን ነው የዘገቡት።

    Reply
    • Editor says

      September 18, 2012 11:26 pm at 11:26 pm

      አቶ ዳዊት – ጎልጉል ለጻፈው ዜና ማስረጃውን ጠቅሶዋል እንጂ “ሰማን” ብሎ አይደለም የጻፈው:: አቶ ተስፋዬ ምንጭ ያደረገው ራሱን ነው – ይህም የራሱን መላምት የሰጠ ለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለውም:: ዜና በመላምት ወይም “እኔ ጋዜጠኛ ነኝና ራሴን ምንጭ ነኝ” በማለት የሚዘገብ ከሆነ “ጋዜጠኛ” የባለሙያነት መጠሪያ ሳይሆን “ሰው” እንደሚለው ቃል ሁሉም ሊጠቀምበት የሚችል የወል ስም ሆነ ማለት ነው:; ለነገሩ አቶ ተስፋዬ ሁሉንም ነገር በዘር መነጽር የሚያይ በመሆኑ ነው “አቶ ሱፊያንን” በዚህ የምርጫ ስሌት ውስጥ ማስገባት የፈለገው::

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      https://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  5. ዳዊት says

    September 18, 2012 12:40 am at 12:40 am

    አንድ ጥያቄ ለጎልጉል። የዚህ ዜና ባለቤት ማን ነው? ተመሳሳይ ዜናዎችንና ተመሳሳይ ዲዛይን ያላቸው ዜናዎችና ጽሁፎች በተለያዩ ድረ ገጾች ላይ ተመለረክቻለሁ። እናንተ ናችሁ ከሌሎች የምትወስዱትና የወሰዳችሁበትን ድረ ገጽ ሊንክ የማትገልጹት ወይስ ሌሎች ከናንተ ወስደው ነው? ጽሁፍ ሲወሰድ በግልጽ የጽሁፉን ባለቤትና ጽሁፉ የተገኘበት ምንጭ ከነ ሊንኩ መቀመጥ እንዳለበት ባለሙያዎች ይናገራሉና መልሳችሁ ምንድነው? ጽሁፍ በመወራረስና በኩል ለጽሁፉን ባለቤት የሚገባውን ዋጋ መስጠት ጨዋነት ነውና ለጥያቄ መልስ ባትነፍጉኝ እላለሁ። የናንተን መልስ ካደመትኩ በሁዋላ የበኩለተን ለማለት እሞክራለሁ። ይህንን አስተያየት በግል አድራሻችሁ መጻፍ ሲኖርብኝ ያላደረኩት ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው ካሉ ለመጋበዝና ወደ ፊት ለምጽፈው አስተያየት ዝግጅት እንዲመቸኝ ነው። ለዜናው ግን አመሰግናለሁ።

    Reply
    • Editor says

      September 18, 2012 12:08 pm at 12:08 pm

      ሰላም አቶ ዳዊት
      ድረገጻችንን በማንበብ አስተያየትዎን ስለለገሱን ከልብ እናመሰግናለን:: ጥያቄዎን ባጭሩ ለመመለስ የዜናው ባለቤት “ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ” ነው:: በድረገጻችን የመጨረሻ ገጽ ላይ “Copyright © 2012 · Golgul” የሚል በመስፈሩ በህግ የዜናው ሙሉ ባለቤት ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ነው – ምንም የሚያጠያይቅ ነገር የለም:: ሌሎቹ ድረገጾች ላይ ይህ የእኛ ዜና ተለጥፎ እርስዎ ያዩበትን ሁኔታ በተመለከት ማለት የምንችለው ነገር ቢኖር እንደ ባለሙያ በሰለጠነ ዓለም የፈጠራና የኮፒራይት ህግጋት በተከበረበት አገር ከፍተኛ የሆነ የህግ ጥሰት እየተከናወነ ነው ለማለት እንገደዳለን:: ለምሳሌ Associated Press የዘገበውን ዜና BBC እንደራሱ አድርጎ ቢያቀርበው ምን ዓይነት ሁኔታ በBBC ላይ እንደሚከሰት ለመገመት የሚያዳግት አይመስለንም:: በአኛ ሚዲያ ዘንድም ይሀው ዓይነት ህጋዊነትና መከባበር ቢለመድ መልካም ነበር:: አለበለዚያ አቶ በረከት ከሚመሩት የሚዲያ አውታር የመለያያው መስመር የት እንዳለ ለማወቅ የሚያዳግት ይመስለናል::

      አርታኢ/Editor
      ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ/Golgul: the Internet Newspaper
      http://www.goolgule.com
      editor@goolgule.com

      Reply
  6. ማለዳ ታይምስ says

    September 20, 2012 05:45 am at 5:45 am

    በማለዳ ታይምስም ይህንን ዜና ከጎልጉል ወስዶ መስራቱ ይታወቃል ነገር ግን ምንጩን ጠቅሶ በመስራቱ የስራ አጋርነቱን ያሳያል ፣ችግሩ የተፈጠረው ከማለዳ ታይምስ ላይ የወሰዱት ሰዎች ምንጩን ማድረቃቸው አስቸጋሪ ሊያደርገው ችሏል ስለዚህ አስተያየት ሰጭው ያደረጉት ገንቢ ነው እና ሁላችንም የሚዲያ ባለቤቶች ትብብር እናድርግ እርስ በርሳችን ሚዲያችንን እና ህብረታችን ምንጩን በመጥቀስ ይሁን ማለዳ ታይምስ

    Reply
  7. Abel says

    September 25, 2012 01:04 pm at 1:04 pm

    Enante Ethiopiawian le selam yaltadelachu mekejoch zerejoch kefu dehaa fetret nachu lezich meder Enant Asmara kewererachu geeze jemro new selam yataneew i m proud to be Eritrean one people one heart enante gen 800 leb yezachu mech selam tagejalachu ahun demo welayta hadeya endyet yegezanal belachu fokeru

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule