ሶስት የብሔራዊ ስለላና የደህንነት ሰራተኞች አገር ለቀው መኮብላቸው ታወቀ። የኮበለሉት የህወሓት/ኢህአዴግ ሰዎች ስደት በጠየቁበት አንድ የአውሮፓ አገር አስቸኳይ ከለላ ማግኘታቸውም ታውቋል።
በቅርቡ አገር እየለቀቁ ከሚኮበልሉት የህወሓት/ኢህአዴግ አባላትና ሰራተኞች መካከል የደኅንነት ሰራተኞች እንደሚገኙበት ያመለከተው የጎልጉል የአውሮፓ ሪፖርተር፤ ድርጊቱ አስቀድመው ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን አስደንግጧል።
በህወሓትና አቶ መለስ በሾሙዋቸው በሻዕቢያ ሰዎች የበላይነት የሚመራውን የስለላ ተቋም ሲያገለግሉ የነበሩትና አሁን የኮበለሉት ሶስት የደህንነት ሰዎችን ስም ዝርዝር ለጊዜው ከመዘርዘር በመቆጠብ መረጃውን ለጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ የሰጡት ከሰዎቹ ጋር በቅርብ ርቀት አብረዋቸው የሚኖሩ ስደተኞች ናቸው።
ሪፖርተራችን ባጠናከረው መረጃ ሶስቱ የስለላ ሰራተኞች በመረጃ ትንተና ዲቪዥን ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሲሆን፣ ሶስቱም የህወሓት አባላት ናቸው። ሰላዮቹ ጥገኝነት በጠየቁ በጣም ጥቂት ቀናት ውስጥ ከለላ ማግኘታቸው ያስደነገጣቸው ወገኖች ጉዳዩን በጥርጣሬ እንደሚመለከቱት ተናግረዋል።
ከኦነግ ጋር ቅርበት ያለው አንድ ስደተኛ “እንዲህ ያለው ድርጊት እየተደጋገመ ነውና ሊታሰብበት ይገባል” በማለት ስጋቱን ገልጾዋል። በስደት ካምፕ ውስጥ በተደጋጋሚ ለህወሓት/ኢህአዴግ ሲሰሩ የሚያዙ፣ ሲነቃባቸው አገር የሚቀይሩ ወይም ወደ አገር ቤት የሚመለሱ እንዳሉም ጠቁሟል።
የጎልጉል ሪፖርተሮች በዚህ ዘገባ ዙሪያ አስተያየትና መረጃ በማሰባበሰብ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ሪፖርት ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ናቸው።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ ለሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Haymanot says
Getachew Belay has run out to America with his wife and kids too. He has served as a minster and other governmental positions including being the assistant manager of EFFORT and for the last year as the main director of private sector workers social insurance agency which collected close to a billion birrs from the private sector since it’s inception a year ago.