በተወለድኩበት በሂርና ከተማ ጎረቤታችን የሆኑ እማማ የልፍተለው እናት የሚባሉ ደግ ሴትዮ ነበሩ። ታዲያ አንድ እሳቸው ያሳደጉት ድመታቸው ከቤት ሸሽቶ ወጥቶ በራሱ ተዳዳሪ ሆነ። በሀረርጌ ከአሳዳሪ ጌታው ቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ዱር ገብቶ በራሱ የሚተዳደር ድመት ዲገላ ድመት (ማለትም እንደ አውሬ ዱር የገባ ድመት ማለት ነው) የሚል ስም ይሰጠዋል። ዲገላ ቃሉ ከኦሮምኛ ቋንቋ የመጣ ሲሆን ዛሬ ግን በሀረርጌ ያሉ አማሮችም የአማርኛ ቃል አድርገውት ከላይ በገለጽኩት ትርጉሙ ይጠቀሙበታል። ይህ ድመት በራሱ ተዳዳሪ ከሆነም በኋላ በሰፈራችን ውስጥ ያሉ ጫጩቶችን እየበላ፤ ድስት እየከፈተ፤ የተሰቀለ ቋንጣ እያወረደ ወዘተ የሰፈሩን ነዋሪ በጣም አስቸገረ። ይህ ድመት የእኛንም የዶሮ ጫጩቶች በተደጋጋሚ በልቶብናል። ይህን ድመት እግዚሃብሄር ከገላገላቸውና ከገደለላቸው ለሂርና ስላሴዎች እጣን ይዘን እንመጣለን ብለው የተሳሉ ጎረቤቶቻችንም እንደነበሩ አስታውሳለሁኝ። ድመቱ ግን የሂርና ስላሴዎችም ሳይገድሉት እንደዚሁ ሰፈሩን እያወከ ኖረ።
ይህ ድመት አንድ ቀን ምሽት ላይ ነፍሱን ይማረውና አባቴ፤ እናቴ፤ እንደዚሁም አንድ የቤታችን ሰራተኛ የነበረች ሴት ሰራተኛችን ከተቀመጥንበት ክፍል ዘው ብሎ ገባ። ይህን ጊዜ አባቴ ቶሎ ብሎ የተቀመጥንበትን ክፍል በር ጥርቅም አድርጎ በመዝጋት ሽመሉን አንስቶ ያንን ድመት መደብደብ ጀመረ። ድመቱ አባቴ ድብደባውን እንዲያቆም እየጮኸና በአይኑ እየተለማመጠው ብዙ ለመነው። ድመቱ የጣር ድምጹን ይበልጥ እያሰማ አባቴን ሊለማመጠው ሞከረ። ነገር ግን አባቴ የድመቱ ልመናና የጣር ጩኸት ልቡን ሳያራራው ድመቱን መደብደብ ቀጠለ። ድመቱ አባቴ በምንም ዓይነት መንገድ ምህረት እንደማያደርግለትና ሊገለው እንደ ቆረጠ ባወቀ ጊዜ ልምምጡን አቆመ። ከዚያም ድመቱ የትግል ዘዴውን ቀይሮ ልክ እንደ ነብር ወደ አባቴ ላይ መወርወርና አባቴን ማጥቃት ጀመረ። እዚያ የነበርነው ሰዎች የድመቱ ባህርይ ወደ ነብርነት መቀየር አስፈርቶን እጅግ ተጨነቅን። እኔም ሆንኩ እዚያ የነበሩት ሁሉ በጣም ፈራን። አባቴም ምንም ፍንክች ሳይልና ሳይደናገጥ ድመቱን መደብደቡን ቀጠለ። በተለይ እኔ የስምንት ዓመት ልጅ ህጻን ስለነበርኩኝ በጣም ፈራሁኝ።
ከዚያን ቀን በኋላ ድመት አደጋ ውስጥ ከወደቀ እንደ ነብር የመቆጣት ክህሎት አለው ብዬ አስባለሁኝ። ያ ድመት የተቻለውን ያህል አባቴን ለማጥቃት ሞክሮ፤ አባቴም ድመቱን ክፉኛ ደብድቦትና አዳክሞት እግሩን ጎትቶ ከቤታችን ውጭ ወስዶ ራቅ ካለ አንድ ጥሻ ውስጥ ጣለው። ያ ድመት እንደዚያ ተደብድቦ ከተጣለ በኋላ በሶስተኛው ቀን እንደ ገና ህይወት ዘርቶ እያነከሰ ሲሄድ አየን። ያ ድመት እንደገና ቆሞ ነፍስ ዘርቶ ይነሳል ያለ ሰው አልነበረም። የድመትም ነፍስ ጥኑ ነች የሚለውን ብሂል ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ማመን ጀመርኩኝ።
የዚህን ዲገላ ድመት ታሪክ ያመጣሁት አለ ምክንያት አይደለም። ባለፈው አንድ ዓመት በተለይም ባለፉት ጥቂት ወራት የሀገራችን ሁለት ዋና ዋና ጎሳዎች የሆኑት የኦሮሞና የአማራ ጎሳ ተወላጆች የወያኔን መንግስት በመፋለም ከሚያደርጉት የሞት የሽረት ትንንቅ ጋር ተዛማችነት ስላለው ነው። አንባቢ ድመትና ሰውን ምን አዛመደው ብሎ ሊጠይቅ ይችላል። እነሆ የዚህን የሂርናውን ዲገላ ድመትና አሁን እየተደረገ ያለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ዝምድና ላሳያችሁ። ድመቱና ወያኔን የሚፋለመው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖር ድመቱ በስርቆቱ ምክንያት ተፈርዶበት ሊገደል ሲል ያልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል ማድረጉ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ በፋሽስቱ አናሳ የትግሬዎች መንግስት ለሃያ አምስት ዓመታት ሲገደልና ሲዘረፍ ከቆየ በኋላ የለም አሁን በቃኝ እንደዚሁ እየተገደልኩና እየተዘረፍኩኝ በዝምታ ከምቀመጥ ከገዳዮቼ ተናንቄ በክብር እየሞትኩ ነጻኔቴን ላረጋግጥ ብሎ መነሳቱ ነው። እርግጥ በድመቱና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ ድመቱን ለግድያ የዳረገው ሌብነቱ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለወያኔ ግድያ የዳረገው መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መጠየቁ ነው። በድመቱና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ያለውን ልዩነት ከገለጽኩኝ በኋላ እስቲ ደግሞ ህይወት ያለው እንስሳም (ድመት) ሆነ ህይወት ያለው ሰው ህይወቱን ሊያጠፋ የመጣ እጅግ ኃያል ገዳይ ሲገጥመው እንዴት እንደሚቋቋመው ላስረዳ። እንስሶችም ሆኑ የሰው ልጆች አንድ ህይወታቸውን ሊያጠፋ የመጣ እጅግ ኃያል የሆነ ጠላት ሲያጋጥማቸው በሶስት ዓይነት መንገዶች በህይወታቸው ላይ የተቃጣውን የሞት ወይም የጥፋት አደጋ ይጋፈጣሉ።
እንስሳትና ሰዎች ህይወታቸው ከፍተኛ አደጋ ላይ ሲወድቅ የሚጠቀሙባቸው ሶስቱ የመከላከያ ዘዴዎች
፩ – Freezing የመጀመሪያው እጅግ አስፈሪ የሆነንና ህይወታችንን የሚያጠፋ አደጋ ሲመጣ የምናደርገው ነገር – freezing (ወይም አደጋውን በድን ሆነን ለማሳለፍ መሞከር ነው)። በድን ስንሆን ወይም freeze ስናደርግ በዚህ ህልውናችንን ሊያጠፋ በመጣ ከአቅማችን በላይ በሆነ ኃይል ምክንያት ደንዝዘንና ተሽመድምደን እዚያው ያለንበት ቦታ በድንጋጤ ክው ብለን እንደ ሃውልት ተተክለን እንቆማለን። ወይንም በተቀመጥንበት ሳንቀሳቀስ እንደ በድን ፍጡር እዚያው እተቀመጥንበት ቦታ ላይ ተሰክተን እንቀራለን። ሰውነታችን አይታዘዝልንም፤ ከድንጋጤያችን የተነሳ አፋችን ከፍተን ድምጽ ማውጣት እንኳን አንችልም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ምን እንደምናደርግ እንኳን አይምሮአችን ማሰብ አይችልም። ከድንጋጤያችን የተነሳ እዚያው ሊገድለን የመጣው ኃይል ፊት በድን ሆነን እንቀራለን። ይህንን ሁኔታ የስነልቦና ጠበብቶች freezing (ወይም በድን መሆን) ይሉታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ በድል አድራጊነት በሻቢያና በሱዳን ጦር ኃይል ታጅቦ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ፤ የኢትዮጵያን ጦር በትኖ ህዝባችንን እንደ ጠላት ቆጥሮ ሲዋረደው፤ ከስራ ሲባርረው፤ ህዝባችን ምንም ነገር ማድረግ ሳይቻለው እንደ በድን ፈዞ ቀረ። ወያኔና ሻቢያ በፈጠሩልን የጎሳና የሃይማኖት ግጭቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከትግራይ በታች ባሉት የኢትዮጵያ ክፍሎት ሲፈናቀሉ፤ ከስራ ሲባረሩ ዝም ብለው በድን ሆኖው ሲያዩ ቆዩ። የወያኔ መንግስት የጤና ጥበቃ ባለስልጣናትና አማካሪዎች እነ ዶክተር አዋሽ ተክለሃይማኖት (የትግራይ ተወላጅ የሆነ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከደርግ ዘመን ጀምሮ ከፍተኛ የወባ መከላከያ መስሪያ ቤት ባልደረባና ኃላፊ የነበረ የወያኔ ደጋፊ) የወባ መከላከያን ድርጅት ሆን ብለው በማፍረስ በዋናው መስሪያ ቤት ውስጥ ያለትን የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ነቃቅለው ወደ ትግራይ ካጋዙ በኋላ ከትግራይ ክልል በታች ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሆን ብለው በወባ ወረርሽኝ እንዲያልቅ ሲያደርጉ የኢትዮጵያ ዝህብ ደንዝዞ ይመለከት ነበር። በወባ ወረርሽኝ የአማራ ክልል በሚባለው ብቻ በ905 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ቅጠል ሲረግፉ፤ እንደዚሁም የኦሮሞ ክልል በሚባለው ውስጥ የሚኖሩ የ550 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ሲረግፉ በጎሳ አጥር ተለያይቶ የተከፋፈለው ህዝባችን ዝም ብሎ በድን ሆኖ የወያኔን ድርጊት ሲያይ ቆይቶአል። በደቡብ ኢትዮጵያም ተመሳሳይ ጥፋት ደርሶአል። ከትግራይ ክልል በታች ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ሌሎችም ብዙ በዝምታ ያሳለፋቸውን ጥፋቶች መዘርዘር ይቻላል።
፪ – Flight ሁለተኛው የሰው ልጅ እጅግ አደገኛ የሆነ የሞት አደጋ ሲገጥመው የሚያደርገው ነገር የሚከተለው ነው። አንድ ሰው ያንን ፊቱ የተጋረጠውን የሞት አደጋ መጋፈጥ ስለማይችል ባለ በሌለ ኃይሉ ህይወቱን ለማዳን ብሎ መሸሽ ይጀምራል። በዚህ ጊዜ የልብ ምቱ በጣም ይጨምራል፤ የሰውነቱ አካሎች የአደጋውን ደረጃ በመገንዘብ ባለ በሌለ ኃይሉ ሸሽቶ እንዲያመልጥ ያደርጉታል። ይህም ሰው ከአደጋው ለማምለጥ ይሞክራል። የኢትዮጵያ ህዝብ አናሳው የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ይዞ የመጣበትን ሞት ለመቋቋም አቅም ስላነሰው፤ ህብረቱና አንድነቱ ስለጠፋ፤ በተናጠል ሆኖ ሽሽቱን ቀጠለ። ግን ወያኔ ዋዛ በድን ስላልሆነ ከፊቱ ተደፍተው ማረን ብለው ቢለምኑትም፤ አንችልህም ተወን እባክህ ብለው ተሸንፈው ቢሸሹትም አሳዶ ይገድላል። በሁሉም አቅጣጫ ከወያኔ ትግሬዎች መንግስት ሞት ማምለጥ አይቻልም። የወያኔ ሞት አማራጭ አይሰጥም፤ ርህራሄና ምህረትን አያውቅም። ይቅርባይነትን (magnanimity) አያውቅም፤ ፈርቶ የሸሸውንም አይተወውም።
፫ – Fight (እንስሳም ሆነ የሰው ልጅ በመጨረሻ ላይ ሞት የማይቀርለት እጣ ሆኖ ጠላትን በድን ሆኖ እንደ እሬሳ ተጋድሞ ማሳለፍም ሆነ ሸሽቶ ማምለጥ የማይቻል መሆኑን ሲገነዘብና ሲረዳ፤ ያንን ሞትን ይዞ የመጣን ጠላት ባለ በሌለ ኃይሉ የሞት ሞቱን ይጋፈጠዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው እንግዲህ የሰው ልጅ ሳይወድ በግድ እንደዚያ አባቴን ሂርና ላይ እንደ ገጠመው ዲገላ ድመት ፊት ለፊት ገጥሞ ገዳዩን ገድሎ ህይወቱን ለማዳን የሚነሳው። የትግሬዎችን የአፓርታይድ ስርዓት የኢትዮጵያ ህዝብ በአስደናቂ ትእግስትና ጨዋነት ታግሶት ቆይቶአል። የኢትዮጵያን ህዝብ የገጠመው የወያኔ ትግሬዎች የፋሽስት መንግስት ፍራቻን፤ ትዕግስትን፤ ይሉኝታን የማያውቅ ነው። የወያኔ ትግሬዎች ተወልደው ባደጉበት የትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ይሉኝታ የሚባል ነገር አይታወቅም (ይሄ ይሉኝታቢስነት በኤርትራ ደጋማ ክፍሎች የሚኖረውን ትግርኛ ተናጋሪ የኤርትራንም ህዝብ ያጠቃልላል)። የትግሬዎች ባህል ለራስ ወገን ማድላትን እንደ ነውር አይቆጥረውም፤ ለዚህም ነው የትግሬ አሳላፊ የለውም ተብሎ የተተረተው። የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲ የሚባለውን ጽንሰ-ሃሳብ ሳያውቅ በፊት ለብዙ ዘመናት ተሳስቦ እንዲኖር ያደረገው ይሉኝታ የሚባል እሴት ነው። በአማራው የቆየ ባህል ውስጥ ይሉኝታ የምንለው፤ በኦሮሞው ባህል ውስጥ ዬሎ የሚባለው ሰው ምን ይለኛል የሚለው አስተሳሰብ በትግርኛ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ውስጥ አይታወቅም።
ባለፉት አርባ ሁሉት ዓመታት በትግራይ ምድር ውስጥ መሰረቱን ጥሎ፤ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የመንግስት ስልጣን የተቆናጠጠው ፋሽስታዊ የሆነ መንግስታዊ ስርዓትና የዚህ ስርዓት መሰረት የሆነው አክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ትግሬዎች ራሳቸውን ልዩ ፍጡር አድርገው፤ ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሳዎች የበለጠ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲያዩ አድርጎአቸዋል። አክራሪው የትግራይ ብሄረተኝነት የትግራይ ተወላጆችን ህሊና አሳውሮአል። የወያኔ ትግሬዎች ህሊናቸው የታወረ መሆኑን የሚያሳየው ማስረጃ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በግፍ አጋዚ በተባለው በጥላቻ ባደጉ የትግራይ ተወላጆች ጦር ሲጨፈጨፍ፤ የትግራይ ተወላጆች ዋሽንግተንና አምስተርዳም ላይ በወርቅና በሹሩባቸው አጊጠው “እናሳያችኋለን” እያሉ መጨፈራቸው ነው። እነዚህ የትግራይ ተወላጆች የኢትዮጵያ ህዝብ የትግሬዎችን የበላይነት በመቃወሙ መጥፋት እንዳለበት አውሬ በቦምብና በጥይት ሲፈጅ ለምንድነው ባዶ እጃቸውን ተቃውሞ የሚያደርጉ ወጣቶችን፤ አዛውንቶችንና አሮጊቶች የምትፈጁት ብለው መሪዎቻቸውን አልጠየቁም። የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንግዲህ ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ብሎ በመነሳት መብቱን ከማስከበር በስተቀር ሌላ አማራጭ የለውም። ወያኔዎችም ሌላ ሰላማዊ አማራጭ አልሰጡትም።
በትግራይ የማምረቻ ፋብሪካዎች ግንባታ፤ በአኖሌ (አርሲ) የጡት- ቆረጣ ሃውልት ግንባታ
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ለሃያ አምስት ዓመታት ለመከፋፈል በመቻሉ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሊዮን የሚቆጠር ህይወት ገብሯል። የኢትዮጵያ ህዝብ መከፋፈሉ ለአናሳው የወያኔ ትግሬዎች አገዛዝ እንዳጋለጠው እየተረዳ መጥቷል። ወያኔ አኖሌ በምትባለው የአርሲ ቀበሌ ላይ የኦሮሞን ህዝብ በጥላቻ የሚቀሰቅስና ከአማራው ጋር ለዘላለም በጠላትነት የሚያቆመውን የልዩነት ሀውልት ሰራ። ይህን ያደረገው እነዚህን ሁለቱን የኢትዮጵያ ትልልቅ ጎሳዎች ለመከፋፈል ነው። በተቃራኒው ወያኔ በትግራይ ውስጥ ከስምንት መቶ በላይ አነስተኛ ማምረቻ ድርጅቶችና እንደዚሁም በደርዘን የሚቆጠሩ ትልልቅ ፋብሪካዎችን በመገንባት ትላንት አንድ ፋብሪካ የነበራት ትግራይ ዛሬ እንዱስትሪዎቿ ከአጠቃላዩ የትግራይ ኢኮኖሚ አስራ ሃንድ በመቶ (11%) የሚሆነውን ድርሻ የያዙባት አዲስ ሀገር ሆናለች። ለኦሮሞው ህይወቱን የሚቀይሩለትን የንጹህ ውሃ ጉድጓዶች፤ የጤና ጣቢያዎች፤ ሆስፒታሎች፤ መንገዶች፤ የመገኛኛ አውታሮች፤ ትምህርት ቤቶች ወዘተ ከመገንባት ይልቅ የመረጡለት አብሮት ለዘመናት የኖረውን የአማራ ህዝብ በጠላትነት እንዲያይ የሚያደርግ “የአኖሌን የጡት-ቆረጣ ሃውልት” መገንባትን ነው። የዚህ በአኖሌ ቀበሌ ምንሊክና አማሮች የኦሮሞን ሴቶች ጡት-ቆረጡ የሚለው የፈጠራ ድርሰት ባለቤት ተስፋዬ ገብረአብ የሚባለው ኤርትራዊ የሆነ የቀድሞ የወያኔ ካድሬ ሲሆን የፈጠራ ድርሰቱንም ”የቡርቃ ዝምታ” በሚባለው 463 ገጾች ባሉት መጽሃፍ አሳትሞ በወያኔ መንግስት እርዳታ በሰፊው አሰራጭቷል። አዲሱን የኦሮሞ ትውልድ የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላት ለማድረግ ሲባል ይኸው መጽሃፍ በቅርቡ ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተበትኖአል።
ወያኔ ለኦሮሞው ጥላቻን የሚያስፋፋ ሃውልት አኖሌ ላይ ሲያቆምለት በተቃራኒው ለዛሬው ትውልድ የሚበጀውን የልማት ስራ አልሰራለትም። ትግራይ ላይ ፋብሪካዎች፤ መንገዶች፤ የንጹህ ውሃ ጉድጓዶችና ቧንቧዎች፤ ግድቦች፤ ተከዜን የመሰሉ ግድቦችና የመብራት ኃይል ማመንጫዎች፤ ዩኑቨርሲቲዎች፤ ኮሌጆች፤ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰራው የወያኔ መንግስት ለሃያ አምስት ዓመታት አማራውና ኦሮሞው ወዘተ የሚኖሩባቸውን ሰፊ አካባቢዎች ንብረት ወደ ትግራይ እያጋዘ እነዚህን ሁሉት ሰፋፊ ክልሎች ለትግራይ እንዱስትሪዎች ጥሬ እቃ (raw materials) አቅራቢዎችና እነዚህ የትግራይ እንዱስትሪዎች የሚያመርቷቸው ያለቁ ምርቶች (finished industrial products) መጣያ ገበያ አድርጓቸዋል። ለምሳሌ ያህል የአማራው ክልል በሚባለው ውስጥ ባሉ አምስት ከተሞች (ደብረ ብርሃን፤ ደብረ ታቦር፤ ባህር ዳር፤ ደብረማርቆስና ኮምቦልቻ) የእንጨት መሰንጠቂያ ድርጅቶችን በመትከልና በአማራው አካባቢ ያለውን የኢትዮጵያ የደን ሃብት በመጨፍጨፍ እንጨቱን ትግራይ ላይ ለተከላቸው ግዙፍ የእንጨት ውጤቶች ማምረቻ ፋብሪካዎች በጥሬ እቃነት እያጋዘ ይገኛል።
የወያኔ ትግሬዎችን መንግስት ያዩ የሚባለውን በኢሊባቦር ውስጥ የሚገኘውን በዩኔስኮ የሰው ልጅ ቅርስ ተብሎ የተሰየመ የሀገራችንን ጥቅጥቅ ያለ ደን ያለበትን ጫካ የድንጋይ ከሰል ፍለጋ በሚል ሰበብ ተክለብርሃን አምባዬ በሚባለው ስግብግብና ቀማኛ የትግሬ ተወላጅ አማካይነት እያስጨፈጨፈ ይገኛል። የሚገርመው ነገር በትግራይ ያለውን እጅግ የተመናመነ የተፈጥሮ ሀብት በመንከባከብ ዓለም አቀፋዊ እውቅናን ያገኘው (The Regreening of Africa የሚለውን ቪዲዮ ለናሙና ይመልከቱ) የወያኔ መንግስት ከትግራይ በታች ያለውን የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት በማስጨፍጨፍና በማውደም ወደ ትግራይ ከማጋዙም በላይ ለውጭ ባለሃብቶች መሬታችንን በሊዝ በማከራየት በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብት ላይ ምንጊዜም ሊረሳ የማይችል ጉዳት አድርሷል። በምእራብ ሀረርጌ የዲንዲን ደን መውደም፤ በባሌ ኦነግን እዋጋለሁ ብሎ ለሳምንታት በእሳት እንዲነድ ያደረገው የተፈጥሮ ደናችን፤ በጋምቤላ በአምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ለቻይናዎችና ለሳውዲ አረቢያ ባለሃብቶች እንዲሸጥ የተደረገው የቀርክሃ ደን (አፍሪካ ውስጥ ካለው ቀርከሃ ሁለት ሶስተኛው እጅ የሚገኘው በኢትዮጵያ ውስጥ ነው)፤ በወልቃይትና ጸገዴ የነበረውን የእጣን ዛፍ በማስጨፍጨፍ የፈጸመው ጥፋት ወዘተ የወያኔ መንግስት እንደ ኢትዮጵያዊ መንግስት ሳይሆን እንደ አንድ ወራሪ መንግስት እንድናየው የሚያደርገን ነው። የወያኔ መንግስት ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ስናገር እንደ ነበረው እንደ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን እንደ አንድ ወራሪ ኃይል መታየት ያለበት ነው።
ባለቀ ሰዓት እንኩዋን የወያኔ ትግሬዎች በተካኑበት የመከፋፈያ ዘዴ መቀሌ ላይ ኦሮሞውን ደግፈው ሰልፍ በመውጣት አማራውን ጠላታቸውን ለመነጠል ማሰባቸውን ስንሰማ ሳንገረም አልቀረንም። አስገራሚው ነገር ወያኔዎች ሌላውን ህዝብ ምን ያህል ደንቆሮ አድርገው ቢቆጥሩት ነው በዚህ ባለቀ ሰዓት ኦሮሞውን በአማራ ላይ እንዲነሳ ያሰቡት? ነው ወይስ አሁንም የማናስብ “አድጊዎች ወይም “አህዮች” አድርገው ቆጠሩን? ይህንን የወያኔ ትግሬዎች መልስ እንዲሰጡበት እተዋለሁኝ። እስቲ በመጨረሻ ይህቺን የወያኔ ትግሬዎችና ኤርትራዎች(ሻቢያ) ሙሽርነት ገብተው የኢትዮጵያን ህዝብ አማራና ኦሮሞ ብለው ሲከፋፍሉ እነሱን በትዝብት ይመለከት የነበረው የኢትዮጵያ ሰው የቋጠራቸውን ስንኞች ከዚህ በታች ላስነብባችሁ። ዛሬ የኢትዮጵያ ስርየት ከኤርትራ (ከሻቢያ) ይመጣል ለሚሉን የግንቦት ሰባት መሪ ካድሬዎችና “Vision Ethiopia” በሚል ስም የግንቦት ሰባት ልሳን በሆነው በኢሳት ቴሌቪዝን ብቅ ብለው ስለ ኤርትራ የኢትዮጵያ ወዳጅና አጋር መሆን ለሚሰብኩን ዋሾ ምሁራን ይህች ግጥም ወያኔም ሆነ ሻቢያ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ያልነጠፈ ጠላትነታቸውን ታመለክታቸዋለች ብዬ አስባለሁኝ።
ዛሬ በግንባር በባዶ እጁ ወያኔን የሚፋለመው የኢትዮጵያ ወጣት ማወቅ ያለበት እውነት ከወያኔ ትግሬዎችም ሆነ ከኤርትራውያን (ሻቢያም ሆነ ጀብሃ) ለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንደማይመጣ ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን ማጥፊያ አድርጎ አድቦልብሎ የፈጠረው የኤርትራዊነት ማንነትም ሆነ የፋሽዝም መገለጫ የሆነው የትግራይ አክራሪ ብሄረተኛነት ለኢትዮጵያ መርዝ ናቸው። ከእንግዲህ ወዲህ የዛሬው የኢትዮጵያ ትውልድ ትናት በተማሪውና በግራው እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሸሽገው ባደፈጡ ወደ ውስጥ ተመልካችና (inward looking) ጎሰኛ የሆኑ ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ የኤርትራና የትግራይ ልሂቃን እንደታለለውና እንደተበለጠው የኔ ትውልድ መበለጥ የለበትም። ለዚህ ለአዲሱ ትውልድ መልዕክቴ ይህ ነው። ይህ ትውልድ ለሃያ አምስት አመታት ለሞት የዳረገውንና ወያኔንና ሻቢያ የነደፉትን ኢትዮጵያን በጎሳና በሃይማኖት ከፋፍሎ የማባላት ሴራ አክሽፎ ራሱን ነጻ እንደሚያወጣ እምነቴ ነው። ይህ ትውልድ ከኤርትራ በጎ ነገር ይመጣል ብለው የሚያሞኙትን ግንቦት ሰባትን የመሰሉ፤ የህዝብ እንቅስቃሴ ሞቅ ባለበት ሁሉ አለንበት እያሉ ከባህር ማዶ ሆነው ባዶ ፉከራ የሚያሰሙ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በኤርትራ በረሃዎች የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ያስቀጠፉ የስልጣን ጥመኞች የማታለያ ፕሮፓጋንዳ እንዳይሰማ እመክራለሁኝ። ግንቦት ሰባትን የመሰረቱት የስልጣን ጥመኞች ቅንጅትን ከማፍረስ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ስለተጫወቱት ሚና፤ በተለይም እጅግ የሚጠሉትን የአማራን ህዝብ ልጆች ለስልጣን መሰላልነት በመጠቀም ለተደጋጋሚ ጥፋት ያጋለጡበትን የተንኮልና የጥፋት ስራቸውን በመረጃ አስደግፌ ወደፊት አቀርባለሁኝ። ይህ ማድረጌ ደግሞ በወያኔ ላይ የሚደረገውን ትግል ያግዛል እንጂ አይጎዳም ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ። እውነት ህብረተሰብን ይፈውሳል እንጂ ጤና አይነሳም!!!!!!
ኢትዮጵያ ውስጥ ጉንፋን ገብቷል አሉ
ኦሮሞና አማራ በጣም ይስላሉ፤
ድምጻቸው ተዘግቶ አክ እንትፍ ሲሉ
አስመራና አድዋ ጦሩን ይስላሉ (1)።
(1) – የግጥሙ ምንጭ ፤ ሀቅ እኔ ስናገር አጫጭር ግጥሞች በቅኔ (በተስፋዬ ጉማ)
እንግዲህ ከሃያ አምስት አመታት የጋራ ስቃይ በኋላ ዛሬ ወያኔን በፊት ለፊት እየተጋፈጡት ያሉት የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ህብረታችሁን አጠናክሩ እላለሁኝ።
This is the soundcloud version of this article can be accessed here.
መልካም ንባብ።
በዶክተር አሰፋ ነጋሽ – (በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ)
4th of September 2016
Email Address Debesso@gmail.com
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Kebede. says
Once you curse(abuse ) a fool , he will always abuse himself. Why you repeat saying that some groups they call ” ahya”, if their master , their colonizer amhara according to ertreans or tigreans be subhumna, then according to the logic they (ertreans /tigreans) would be the slave donkies, or fandyas. In other words the water will not climb uphills. As a doctor you should not associate human beings with any animal. in our society if yoou do that it means you are abusing urself. The amharas are fighting back Gojam/gondor started it . Weyanes are in panic.