ሰሞኑን የዐድዋ ድል መታሰቢያ 121ኛ ዐመት የሚዘከርበት ወቅት ነው። በፍቃዱ ዘ. ኀይሉ የተሰኘ ከታቢ (blogger) “Bilisummaa adda-ዋ!” በተሰኘ እና በድረ ገጽ እና በፌስ ቡክ በተሰራጨ አነጋጋሪ ጽሑፉ ስለ ዐድዋ ድል እና ስለ ምኒልክ አመራር ብዙ ቢልም በተለይ ኹለቱ ትርክቶች የሚጐረባብጡ፤ ፈራቸውን የሳቱ ኾነው ስላገኘኹዋቸው እነሱ ላይ ሀሳቤን ማካፈል ወደድኩ።
ኹለቱ የበፍቃዱ ዘኀይሉ “Bilisummaa adda-ዋ!” ትርክቶች፤
1) የዐድዋ ድል በታሪክ አጋጣሚ የተከሰተ ነው እና
2) ዐድዋ የጨቋኝ ምርጫ የተሰኙት ናቸው።
ኹለተኛው ትርክት ቃል በቃል ባይኾንም የዐድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነጭ ጨቋኝ የጥቁር ጨቋኝ መርጦ የተዋጋበት እንጂ የዐድዋ ጦርነት ሕዝቡ ለነጻነት የተዋጋበት ጦርነት አይደለም ነው። በትክክል ተረድቼው ከኾነ በፍቃዱ መነሻ ሀሳቡን ያገኘው ከ 2012 የታምራት ነገራ ጽሑፍ ነው። የኔ አቋም በአጭሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዲሞክራቲክ የኾነ ሥርዐት ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ኖሮ ስለማያውቅ የዐድዋ ጦርነትና ድል ተነጥሎ ጭቆና የሚለው ቃል ሊለጠፍበት አይገባም ነው። ጣሊያን ሊጨቁነን አይደለም የተዋጋን፣ ባሪያ ሊያደርገን ሊያጠፋን እንጂ! ይህን ደግሞ አንዴ አይደለም ደግሞ ደጋግሞ አሳይቶናል። ጭቆናና ባርነት ብሎም መጥፋት ለየቅል ናቸው፤ መዛነቅ የለባቸውም። ባርነት የአገዛዝ ሥርዐት አይደለም፤ የሕልውና የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው። በድምዳሜው ኹለቱም ታምራትም ኾነ በፍቃዱ የተሳሳተ ትርክት አራምደዋል። ሊያርሙ ይገባል።
ወደ ዋናው እና በፍቃዱ ደግሞ ደጋግሞ ስላለው የብዕር ወለምታ አይደለም ወዳሰኘኝ ጉዳይ ለመንደርደር የበፍቃዱን ኹለት ዐረፍተ ነገሮች ልጥቀስ፤ በአንዱ አንቀፅ “ዳግማዊ ምኒልክ በታሪክ አጋጣሚ የዐድዋ ድል የተበሰረበትን ጦርነት በንጉሠ ነገሥትነት መርተዋል።” ይህ የአንቀጹ የመነሻው ዐረፍተ ነገር ሲኾን፣ ወረድ ብሎም በሌላ አንቀጽ አምስተኛ ዐረፍተ ነገሩ ዳግማዊ ምኒልክ “በታሪክ አጋጣሚ የዐድዋ ድል ባለቤት ኾነዋል” ይለናል።
ሲጀመር የዐድዋ ድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ድል ነው። ይህንን ድል ምኒልክ እንደ ንጉሠ ነገሥትነታቸው መርተዋል። በቦታው ምኒልክ እንደ ንጉሠ ነገሥት፣ እንደ መሪ፣ እቴጌ ጣይቱ ሌሎችም የዘመኑ መሪዎች ስብዕና፣ አመራር እና ቁርጠኝነት ባይኾን ኖሮ የዐድዋን ጦርነት አናሸንፍም ነበር ብዬ አፌን ሞልቼ በመረጃም በማስረጃም አስደግፌ ደግሜ ደጋግሜ ልል እችላለኹ። ዐድዋ -ዐምባ አላጌን ለማሸነፍ ሻለቃ ቶዜሊን ሳይኾን ገብርዬን መኾን ግድ ይላል፤ ዐድዋ መቀለን ለማሸነፍ ሻለቃ ጋሊያኖን ሳይኾን ጣይቱን፣ አባተን፣ ባልቻን መኾን ግድ ይላል፤ ዐድዋ – ዐድዋን ለማሸነፍ ጄኔራል ባልዲሰራ፣ ጄኔራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል ዳቦርሚዳ፣ የጣሊያንን ጦር፤ ባንዳው አስካሪን ሳይኾን ምኒልክን – መኮንንን – ታፈሰን፣ መንገሻን፣ አሉላን፣ አውዐሎምን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ መኾንን ግድ ይላል።
ከዐፄ ምኒልክ በቀደሙትና በተከተሉት ነገሥታት የተመሩት ጦርነቶች እናም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪካችን ተሸናፊ ነው የኾኑት የኾንነው፤ በዐፄ ቴዎድሮስ አመራር በእንግሊዝ፣ በዐፄ ዮሐንስና በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አመራር በደርቡሾች፣ በዐፄ ኀይለ ሥላሴ አመራር በጣሊያን የዐፄ ዮሐንስ ከግብፆች ጋራ ጦርነቶች ሲቀር። ስለዚህ ታሪካችን ሽንፈትን እንጂ አሸናፊነትን አያሳየንም።
አጋጣሚ የሚለውን ትርክት ማብራራት የነበረበት በፍቃዱ ቢኾንም ትልቅ ግድፈት መኾኑን ለማሳየት የዐድዋ ጦር በአግባቡ የታቀደ፤ የተወጠነ፤ ብዙ የተደከመበት፤ የተለፋበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ውጤት ነው ባይ ነኝ።
ዝርዝሩን በሰፊው መጻፍ ባልችልም በተለያዩ ጽሑፎች እንደምናነበው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጣሊያን ጋራ ጦርነት እንደሚገጥም አስቀድሞ ግንዛቤ ነበረው። ለዚህም ሕዝቡም ኾነ መሪው ለጦርነቱ እንደተዘጋጀበት የምናውቀው፤
1) እያንዳንዱ ንብረት የነበረው ሕዝብ ጥሬ ገንዘብ አዋጥቶ ከጣሊያን የተበደርነውን ዕዳ ከፍሏል።
2) ከዕዳ ክፍያ በተረፈው እና ከግብር በተገኘው ተጨማሪ ገንዘብ የጦር መሣሪያዎች ከጣሊያን ሳይቀር ተሸምተው ወደ ሀገራችን ገብቷል። እንዲሁም ተዘፍኗል፤
ባመጣው ወጨፎ ባመጠው እርሳስ
ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ
3) ለጦርነቱ ዝግጅት ከጦርነቱ አስቀድሞ ከጦርነት መሪዎች በተለይ በእቴጌ ጣይቱ እና መሰል አመራሮች ዘንድ የጣሊያን ደጋፊዎች ወሬ አቀባዮች ሰላዮች ዘመዶቻቸው ሳይቀሩ ከሀገር እንዲባረሩ፤ እንዲወገዱ ተደርጓል።
4) በዐፄ ምኒልክና አብረዋቸው በዘመቱ ሌሎች የጦር አዝማቾች መካከል ምክክር፤ የውሳኔ ሓሳብ አካኼድ በድምጽ ብልጫ ሳይኾን በአጠቃላይ ስምምነት ነበር። ይህም እያንዳንዱ ወገን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል። እንደ አስረጅም፦የኢትዮጵያ ጦር የመቀሌውን የጣሊያን ጦር እስከምሽጉ ዘልቆ ሊዋጋ ተወስኖ በሞተ ሰዓት ራስ መንገሻ ደርሶ የውሳኔውን ሃሳብ አስቀይሯል። ይቺ ጉዳይ ብታንስም በጦርነቱ መሪዎች መካከል የነበረውን መናበብ እና የሀሳብ ፍሰት (communication) አመላካች ነው።
5) ከጦርነቱ በፊትም፣ በጦርነቱ ወቅትም የተነሱ የውስጥ ግጭቶች ከሞላ ጐደል በመቻቻል እና በዕርቅ መፍትሔ (conflict resolution) እየተበጀላቸው የኹሉም ሰው ሀሳብ ጦርነቱ ላይ እንዲያተኩሩ ኾኗል።
6) በጦርነቱ ወቅትም ቢኾን፤
6.1 የጣሊያን ሀገር-በቀል ሰላዮች እንዲከዱና መልሰውም ጣሊያንን አደናጋሪ መረጃዎች እንዲያደርሱት ተደርገዋል። ይህ የዛሬ 121 ዓመት ሳይኾን የዛሬም የጦርነት ሳይንስ ነው።
6.2 የጣሊያን የመቀሌን ምሽግ ለማስለቀቅ ከውጊያ ይልቅ ዘዴ ተቀይሶ (strategy and tactic) ከዘጠኝ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን በሦስት የጦር አዝማቾቻቸው ሕይወታቸውን ገብረው የውሀ ምንጭ በመያዝ በመድፍ ያልተበገረውን የጣሊያንን እንዳኢየሱስ-መቀለ ምሽግ አስለቅቀዋል።
6.3 ዐድዋና አዲግራትም ተመሳሳይ እርምጃዎች ተወስደው ነው የኢትዮጵያ ጦር በዋናው የጦር አዝማች የዳግማዊ ምኒልክ አመራር ለዚህ ድል የበቃነው።
ይህ ድል የታሪክ አጋጣሚ አይደለም፤ ታስቦ፤ ታቅዶ፤ መስዋዕትነት ተክፍሎበት በጦር ሜዳም የምዕራብ ዓለሙን የጦር ትምህርት የተማሩ በጄኔራሎች የሚመራውን የጣሊያንን ጦር ከጨዋታ ውጪ በማድረግ ነበር በኢትዮጵያ ሕዝብ በድል አድራጊነት የተጠናቀቀው። ይህ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል። ጥያቄም ማስነሳት የለበትም።
“የታሪክ አጋጣሚ ነው”፤ “የጨቋኝ ምርጫ ነው” ትርክቶች ሳይኾን ሊጠየቅ፣ ልንነጋገር የሚገባን ባይኾን እንደበቀደሙት እና እንደተከተሉት ነገሥታት የተመሩት ጦርነቶች መሸነፍ ነበረብን። ይህ እንደ ምርምር መላምት መጠየቅ ያለበት አግባብ ጉዳይ ነው። ይህ ከኾነ ለምን እንዳልተሸነፍን “የታሪክ አጋጣሚ” የሚለው ትርክት ሊገልጸው አይችልም፤ ዝርዝር ምክንያቶቹን ከረምረም ብለን ብንመለስባቸውስ?
እንኳን ለ121ኛው የዐድዋ ድል በዐል አደረሰን!
ሰናይ ንባብ
ከዳንኤል አበራ
ለአስተያየቶቻችኹ: danlinet@yahoo.com
ከዝግጅት ክፍሉ: የበፍቃዱን ጽሁፍ ለንፅፅር ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Melaku Beyan says
Gosh, gosh wondime Daniel Aberra. You have dwarfed the bunch of nameless creatures who attempt to distort our proud history to their very diminutive sizes.
Because of their own genuine inferiority, they have difficulty associating themselves with the history of our courage-incarnate and valiant ancestors who dealt the enemy a mortal blow over a century ago.
Let Befeqadu Behailu delight himself for having scribbled a set of lies he tried to peddle. His motive for regurgitating the tired and nonsensical notion is poorly veiled. But Ethiopians will no longer forgo their right to keep every inch of their historical lands.
Whatever his mission, his willful perversity will only make him a laughing stock.
Bisrat says
Daniels informed rebuttal is commendable. It is the paucity of such responses that has emboldened those who are avowedly hostile to everything Ethiopian like Messers Jawar Mohammed , Hizkiels and their ilk to threaten and slight us with impunity. The jihadist Jawar had threatened to decapitate Christians in his so-called Oromia. The other fellow Hizkiel who is masquerading as a historian is another pathetically ignorant soul who is full of his little self. How else can one attempt to rewrite his make-believe Oromo history (my history) in the way that belittles the very people he claims to speak for.
The Befeqadus, therefore, deserve to be educated if they can learn as a matter of course. Once again, the rest of us should as well emulate Daniel. The deliberately distorted enemy narrative must be debunked and rebuffed authoritatively.
በለው! says
…. “የዐድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከነጭ ጨቋኝ የጥቁር ጨቋኝ መርጦ የተዋጋበት እንጂ የዐድዋ ጦርነት ሕዝቡ ለነጻነት የተዋጋበት ጦርነት አይደለም ነው። በትክክል ተረድቼው ከኾነ በፍቃዱ መነሻ ሀሳቡን ያገኘው ከ 2012 የታምራት ነገራ ጽሑፍ ነው። የኔ አቋም በአጭሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዲሞክራቲክ የኾነ ሥርዐት ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ኖሮ ስለማያውቅ የዐድዋ ጦርነትና ድል ተነጥሎ ጭቆና የሚለው ቃል ሊለጠፍበት አይገባም ነው። ጣሊያን ሊጨቁነን አይደለም የተዋጋን፣ ባሪያ ሊያደርገን ሊያጠፋን እንጂ! ይህን ደግሞ አንዴ አይደለም ደግሞ ደጋግሞ አሳይቶናል። ጭቆናና ባርነት ብሎም መጥፋት ለየቅል ናቸው፤ መዛነቅ የለባቸውም። ባርነት የአገዛዝ ሥርዐት አይደለም፤ የሕልውና የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው። በድምዳሜው ኹለቱም ታምራትም ኾነ በፍቃዱ የተሳሳተ ትርክት አራምደዋል። ሊያርሙ ይገባል።”
******************************!
“ነገሩ እንዴት ነው ጃል? የኢህአዴግ ተሃድሶ/ታድሶ በታሳሪዎችና በረጅም ገመድ በተለቀቁት ላይ መስረፁን በቡረቃቸው ላይ ተገለጠ!? ሠርተፍኬት የተሰጣቸው የለየላቸው ተሳዳቢ አልያም የፓርቲ መሪ ራዕይ አስቀጣይ መሾማቸውን የሺዋስ አሰፋ (ሰማያዊ) አብርሃ ደስታ (አረና) ዞን ፱ የሚዲያው ተንታኝ…የዜና…የታሪክ ..ጦማሪ(አጠናባሪ) መሆናቸውን ይታዘበና ዘይገርምዩ ይላሉ።
» የመንዚቷ ልጅ ፍቃዱ ዘነበች!? እጁን አጣምሮ ፎቶ ከተነሳ በኋላ በተሃደሶው ስልጥና.” አይደገምም!” ብሎ ቃል ገብቶ የምሥክርነት ሰርተፈኬቱን ሁሉ ለሕዝብ ተጸፅቻለሁ እወቁልኝ ሲል በየአጠቢያው ለጥፎ እንግዲህ ያ! ታጋይነቱ ተባነነ አሁን አገልጋይ ሆነ ማለት ነው” መራራ የነፍጠኛው የልጅ ልጆች ያላቸው ምነው ንፍጣም ሆኑ ማለት ይቻላል?
ለነገሩ በሬ ካራጁ አሉ ” ከመንዝ ወራሪዎችና ከትግራይ መጤዎች እኛ ኦሮሞዎች ለፊንፊኔ እንቀርባለን ያሉት” መራራ ማን ነጻ ያወጣውን መሬትና ሀገር ነበር? ዞን፱? ወይንስ ‘ኦነግ’ የቅሊንጦና ቃሊቲ ሰልጣኞች ሲለቀቁ ብሕዝብ ላይ የመፈላሰፍ ትምህርት ባፋን ኦሮሞ ኮርስ እስር ቤት ይሰጣቸው ይሆን? “እስር ቤቱ አፋን ኦሮሞ ይናገራል ያለው ጮሌ ማን ነበር?” እስቲ የመንዚቷን ልጅ ይህንኑ በአማርኛ ይጻፈውና እንሳቅ መቼም ለመሳቀቅ የታደለን ነን። በፍቃዱ ዘነበበት በለው!