• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአማራና ኦሮሞ ሕብረት ለዘላቂ ለውጥ!

December 8, 2017 12:43 am by Editor 3 Comments

የመቀሌው ስብሰባ ማራቶን ሹምና ሽረቱ የመግለጫ ጋጋታው የጥልቅ ተሃድሶው ውጤት ከግር ጥፍሩ እስከ ዶቃ ማሰሪያው በንጹሀን ደም ለጨቀየው የሌባና የሰው በላ የወያኔ ቡድን ለዳግም ግፍ ለበለጠ አፈና በሚያመቸው መልኩ የጭካኔ ጠበብቶቹን መሪ አድርጎ ሊዘምትብን መዘጋጀቱን አውጇል። የሕዝብ ለህዝብ መተላለቅን የሚሰብኩ ጀሌዎቹን አሰልፎ በሕዝባችን ላይ ከነመርገሙ ሊጫንብን አፈር ልሶ ተነስቷል። የህወሃት ትዕቢት ጨለምተኝነቱና ለህዝብ ያለው ንቀት ድንበር የለሽ በመሆኑ አማራና ኦሮሞን በእሳትና ጭድ መስሎ በአደባባይ የተናገረውን ስቅላት ይገባው የነበረን ጸረ ሕዝብ ግለሰብ ከፍ ላለ ወንበር መሾም ነደው እንዲጠፋ በተመኘላቸው ሕዝቦች ላይ ሌላ ዙር የከፋ ዘመቻ አቅዶ ለመነሳቱ አመላካች መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።

የትግሬ ነጻ አውጪውን ወያኔን በተንኮሉ አይነት በጭካኔው ደረጃ በክፋቱ ልቀት ሰይጣንን በእድሜ ካልሆነ በተገባር እንደማይስተካከለው በማህበራዊ ድረገጽ ያየሁት አባባል የወያኔዎችን ባህሪ በሚገባ ያሳያል። ኢትዮጵያን በመሰለ የደጎችና የመንፈሳዊያን ምድር እንዲህ በድርጊቱ ከዲያቢሎስ የከፋ አረመኔ አገዛዝ በታሪኳ ገጥሟት አያውቅም። ከአንድ መሐጸን የፈለቁትን አቤልና ቃዔልን ደም ያፋሰሰ ጋኔል ፤ በትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ተበልጦ በዘመናት አብሮነት እንደ ሰርገኛ ጤፍ ተቀላቅለው የኖሩትን የአማራና የኦሮሞ ወንድማማች ነገዶች በሃሰት ወሬ፤ በጥላቻ ቅስቀሳና፤ በፈጠራ ታሪክ የተሳሰሩበት ገመድ እንዲላላ አብሮነታቸው ጥርጣሬ እንዲያጠላበት የማድረጉ ሴራ ተሳክቶለት ላለፉት 26 አመታት ፍላጎቱን ለማሳካት አስችሎት ቆይቷል።

በበዳይና ተበዳይ ትርክት ባለፍ የታሪክ ምጣድ ላይ ሆንን ስንፋጅ ወያኔዎች የዘረፋና የአፈና መዋቅራቸው ሃዲድ ጓዳችን እስኪደርስ ሲዘረጉት ለመንቃት ባለመቻላችን ገና በግዜ በቀላሉ እንገላገልው የነበረውን የወንበዴ ቡድን ዛሬ ነቅተን ለመታገል ስንነሳ ብዙ መስዋዕትነት ባላስከፈለን ነበር። ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየጎለበተ ያለውን የአማራና የኦሮሞ አብሮነት ይበልጥ እንዲጠናከር የቅልበሳ ሰለባም እንዳይሆን ነቅቶ መገኘት ግድ ይላል። ሂደቱን በተገቢው መንገድ በተደደራጀ መልኩ የተናበበ የሕዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመፍጠር መንገድ ጠራጊ እርምጃዎችን በየደረጃው መከተል ይኖርብናል። ሃገራችንን ከብተና ነጻነታችንን ከግፈኛ ለመታድግ የፖለቲካ ልሂቃኑና የሕዝብ ድርጅቶች ለዘሌቄታዊና ለሰላማዊ ሃገር ምስረታ በሚበጅ መልኩ አብሮነትን ሊያጠናክር የሚችሉ መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀትና በተግባር ለመተርጎም መትጋት ይጠበቅባቸዋል።

በወሎ (ወልዲያ) ለነቀምት ከነማ ቡድን ተጫዋቾች የራት ግብዣ ተደርጎላቸው – ፎቶው ከማኅበራዊ ድረገጾች የተገኘ

ከዚህ አንጻር ማንም ምንም ይበለው ከበስተጀርባው ያነገበው ስውር ተልዕኮ ይኑረው አይኑረው ፖለቲካዊ ፋይዳው፣ ታክቲካዊ አሰላለፉ በፈለገው ደረጃ ይተርጎም የባህር ዳሩ የአማራና የኦሮሞ የፖለቲካና የማህበረሰብ መሪዎች የጋራ ምክክር መድረክ ታሪካዊነቱን ማንም ሊነሳው አይችልም። ይህ ያልተለመደና ያልተጠበቀ የፖለቲካ ቡድኖች ግንኙነት ሊያስገኝ የሚችለው ማህበራዊ፣ ሰብዓዊና፤ አብሮነታዊነትን የሚያጠናክር ተግባር ተምሳሌታዊ ነው። በሳትና ጭድነት ተፈርጀው እርስ በእርሳቸው እንዲጫረሱና እንዲጠፋፉ ዕቅድ የተነደፈላቸው ወገኖች የህወሃትን የአፓርታይድ ከፋፍለህ አፋጅተህ ግዛው የጥፋት ፖሊሲ ያከሸፉበት አጋጣሚም ነው። የአማራውና ኦሮሞው የዘመናት አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር ታሪካዊ ክንውን እና አዲስ ምዕራፍ ከፋችም ሆኗል።

ስለነዚህ ሁለት ኢትዮጵያዊ ታላላቅ ነገዶች ብዙ ተብሏል። እንደ ሁለት ጎረቤታማች ሕዝቦች እስኪታዩ ድረስ ለመለያየት ተደክሟል። እሳትና ጭድ ሆነው የትግራይ ቀማኛና ሰው በላ የናዚ ድርጅት እንጀራ መጋገርያ ሆነው እንዲኖሩ ያልተጫረ ክብሪትና ያልተረጨ ነዳጅ አልነበረም። ክፉ ወያኔዎች በገነቡት የጥላቻ ግምብ አማራና ኦሮሞን የመለያየት ሴራቸው እስከዘላለም እንዲቀጥል ሰይጣናዊ ዘመቻ ሲያቀናብሩ ኖረዋል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ በወያኔ አዝማችነትና ጥላቻን በተጋቱ የዋሃን ስሜታዊ እርምጃ የብዙዎች አንገት ተቀልቷል። ክፋትን በሰበኩ የጥላቻ ደቀ መዛሙርት ተነሳሽነት ብዙ ሺዎች ወልደው ከከበዱበት፣ ጥረው ግራው ካፈሩት ሃብትና ንብረት ተፈናቅለው ለስደትና እንግልት ተዳርገዋል።

በዚህም ብዙ ቤተሠብ ፈርሷል። አረጋዊያን ያለጧሪ፣ ህፃናት ያለአሳዳጊ ሜዳ ላይ ተበትነው ቀርተዋል። አምራቹ ዜጋ፣ የሃገር አሌኝታው አርሶ አደር በደረሰበት ግፍ ለጎዳና ተዳርጎ፤ ምጽዋት ጠባቂ ከርታታ የሃገር ሸክም ሆኖ የሃገሪቱን ማህበራዊ ምስቅልቅል የከፋ አድርጎታል። ተዘርዝሮ የማያልቅ እጅግ ብዙ ግፍ ምንም በማያውቁ ንጹሃን ዜጎች ላይ የብሄር ማንነታቸውን ምክንያት በማድረግ ተፈጽሟል። ከዚህ ሁሉ ግፍ በሗላ የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘው አንዳችም ትርፍ የለም። እንዲያውም ከአጋር ወንድሙ በመለየቱ ምንም እንደማያመጣ እስከመቆጠር ወርዶ በመብትና በሐብቱ ላይ ባለግዜዎች ፍጹም ወሳኝ የሆኑበት ጭቆና ነው ተንሰራፍቶ የቆየበት። ለዚህ ሁሉ ሰይጣናዊ የጥፋት ዘመቻ አቀናባሪ ወያኔዎች ይህ ሁሉ ጅምር እንጂ ፍጻሜ አልነበረም። የጥላቻ መሃንዲስ፣ የዘራፊዎች ሕብረት፣ የሰው በላው ስርዓት ምንጭ የሆነው ሕወሃት ከመነሻው ከደደቢት በረሃ ይዞት የመጣውና ያነገበው እኩይ ዓላማውና ዕቅዱ በማያባራ የመጠፋፋት አዙሪት አማራና ኦሮሞውን ማግደው እስከዛሬ በዘረፉትና ወደፊትም በሚዘርፉት የህዝብና የሃገር አንጡራ ሃብት የቅንጦት ሕይወታቸውን ያለተቀናቃኝ ለማጣጣም ነበር።

ከዚህ አስፈሪ ሐገር አፍራሽና ትውልድ በታኝ የጥፋት አዙሪት ሕዝባችንን ለመታደግና ሐገራችንን ከብተና ለማዳን የአማራና የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎችና ልሂቃን በጋራ ለማሰለፍ እልህ አስጨራሽ ጥረት ሲካሄድ ቆይቷል። ፖለቲከኞቹና ልሂቃኑ በሚያካሂዱት ገመድ ጉተታና አሮጌ የታሪክ ሂሣብ ለማወራረድ በፈጠሩት ጊዜውን ያልዋጀ ፉክክር አስፈላጊው የትብብር እንቅስቃሴ ሲጓተት ቆይቷል።

በእርግጥ የኢትዮጵያ ሐገራዊ ንቅናቄ በይፋ ከተቋቋመ ወዲህ በተለይ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይል ለትብብሩ ራሱን አዘጋጀቶ ሲያቀርብ የአማራው ኤሊት ከአደባባዩ ጠፍቶ ሂደቱ በእንጥልጥል ላይ በነበረበት ወቅትና ሁኔታ ላይ የህወሃት የትሮይ ፈረስ የተባሉት ቅልብ ዘቦቹ ኦህዴድና ብአዴን የሕዝብ ኃይል በፈጠረው ማዕበል ተገፍተው የወያኔን የመጠፋፋት ሴራ ለማክሸፍ የሚያስችል ተግባር ለመፈጸም መነሳታቸው በተቃዋሚው ጎራ ለተሰለፍነው ሊያሰራና ልንሰራበት የሚገባውን አጀንዳ በመነጠቃችንና ባለማድረጋችን ለሃፍረት የዳረገን ሲሆን ለብአዴንና ኦህዴድ ምስጋና ማስገኘቱን በፍጹም ልንክደው የማንችለው ሃቅ ሆኗል። ኢትዮጵያ ሐገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። የኦሮሞና የአማራው ማህበረሰብ ሕልውናም የከፋ አደጋ ተደቅኖበታል። የትግራዩ አናሳ ቡድን የኢትዮጵያን ሕዝብ ረግጦ ለመግዛትና የዘረፋ ስርዓቱን ለማጽናት በሃገሪቱ አብላጫ ሕዝብ የሚወክሉትን የአማራና የኦሮሞ ማኅበረሰቦች እርስ በእርስ እያፋጀ መቀጠል የማያስኬደው እየሆነ መጥቷል። የክፋቱ መጋረጃ ተገልጦ የፀቡ ምንጭና የሴራው ቀማሪ የታወቀበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ሁለቱንም ወገን በኃይል ደፍጥጦና የኅብረተሰቡን ቅስም ሰብሮ በወታደራዊ የበላይነት አፓርታይዳዊ አገዛዙን ለመታደግ የአፈና ዕቅዱን እየዘረጋ ይገኛል።

አማራና ኦሮሞ እንደ ድርና ማግ የተጋመዱ፣ እንደ ሠርገኛ ጤፍ የተቀላቀሉ ዘመን ተሻጋሪ ዕድል ፈንታና ጽዋ ተርታቸው አንድ የሆነ ወንድማማች ነገዶች ናቸው። የአማራውና የኦሮሞው የጋራ ኅብረት ለኢትዮጵያ ኅልውና መረረጋገጥ ጽኑ መሠረት ነው። ለዚህ ነው የአማራውና የኦሮሞው ኅብረት ያስፈለገው አማራው ለኦሮሞው ወይም ኦሮሞው ለአማራው ውለታ ሰጪና ተቀባይ እንዲሆን ሳይሆን አንደኛው ለሌላኛው ኅልውና እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ለረጅም ዘመናት በደምና በአጥንት ተጋምዶ የኖረው የኦሮሞውና የአማራው አብሮነት የተፈጠረበትን መላላት አጥብቆና አጠናክሮ የጋራ ጠላቱን በተባበረ ክንዱ በመደቆስ በዴሞክራሲና በእኩልነት ላይ የቆመ የኢትዮጵያን አንድነት በፀና መሠረት ላይ ለማቆም የሚያስችል እምቅ ኃይል አለው። በጠላት ሴራ ተቋርጦ የቆየውን ኅብረትና አንድነት በማደስና በማጥበቅ የኢትዮጵያ ህልውናን በአፋጣኝ ለመታደግ አማራውና ኦሮሞው ግንባር ቀደም ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል። በዚህ ፈታኝ ወቅት በአስቸኳይ ኢትዮጵያን እንደሃገር ለማቆየት ከአማራውና ኦሮሞው ሕዝብ ጎን በመሰለፍ በተለይ በውጭ የሚገኘው ወገን በነቃና በተደራጀ መልኩ ለሃገር ውስጡ ዕንቅስቃሴ ደጀንና አለኝታ መሆኑን ማሳየት ይኖርበታል።

በአንድ ሃገር የፖለቲካ ሥርዓት ምስረታ ይሁን ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሕዝብ ቁጥር ለውሳኔ አሰጣጥና ለለውጥ ቅልጥፍና ወሳኝ ሚና እንዳለው ይታወቃል። ከዚህ አንጻር በሃገራችን ካለው ወቅታዊ ዘውግ ተኮር አሰላለፍ አኳያ የኦሮሞና የአማራ ማህበረሰብ ከሃገሪቱ ጠቅላላ የሕዝብ ቁጥር ከ70 በመቶ የማያንሳውን የሚወክሉ በመሆናቸው የእነዚህን ሁለት ትልልቅ ብሔሮች በጋራ ማሰለፍ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ወሳኝ አጀንዳ ነው። ሃገር ከብተና እንዲተርፍና አስተማማኝ ለውጥ እንዲመጣ የሚመኝ የየትኛውም የፖለቲካ ይሁን የዘውግ እባል በመጀመሪያ ይህን ጥሬ ሃቅ በቀና መንፈስ መቀበል ይኖረበታል። የኦሮሞና የአማራ አብሮነት በጠንካራ መሰረት ላይ ከቆመ ለሁሉም ሕዳጣን ሕዝቦች የሰላምና የእኩልነት ዋስትና ሊሆን እንደሚችል አያጠራጥርም። አማራውና ኦሮሞውን በዋናነት መዕከል አድርጎ በሕብረብሔራዊ መልክ ይሁን፤ በብሄር ወይም በጆግራፊያዊ አሰፋፈር የተደራጁትን ሁሉ ወደ አንድ የጋራ የትብብር መድረክ በማምጣት ህወሃትን በማስወገዱ የጋራ ዘመቻ ሓቀኛ ትብብር መፍጠር ሃገራችንና ሕዝባችንን ለመታደግ ያለው ብቸኛ አማራጭ ይህን እውነት ተቀብሎ መቆም ሲቻል ነው።

እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

አሜን!!!

ሐይለገብርኤል አያሌው፤ የቀድሞው መዐሕድ አመራር አባል

hailegebrela@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Amharaa - Oromo says

    December 8, 2017 04:22 pm at 4:22 pm

    “አማራና ኦሮሞ እንደ ድርና ማግ የተጋመዱ፣ እንደ ሠርገኛ ጤፍ የተቀላቀሉ ዘመን ተሻጋሪ ዕድል ፈንታና ጽዋ ተርታቸው አንድ የሆነ ወንድማማች ነገዶች ናቸው። የአማራውና የኦሮሞው የጋራ ኅብረት ለኢትዮጵያ ኅልውና መረረጋገጥ ጽኑ መሠረት ነው። ለዚህ ነው የአማራውና የኦሮሞው ኅብረት ያስፈለገው አማራው ለኦሮሞው ወይም ኦሮሞው ለአማራው ውለታ ሰጪና ተቀባይ እንዲሆን ሳይሆን አንደኛው ለሌላኛው ኅልውና እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ለረጅም ዘመናት በደምና በአጥንት ተጋምዶ የኖረው የኦሮሞውና የአማራው አብሮነት የተፈጠረበትን መላላት አጥብቆና አጠናክሮ የጋራ ጠላቱን በተባበረ ክንዱ በመደቆስ በዴሞክራሲና በእኩልነት ላይ የቆመ የኢትዮጵያን አንድነት በፀና መሠረት ላይ ለማቆም የሚያስችል እምቅ ኃይል አለው።”

    በትክክል ብለውታል አቶ ኃይለገብርኤል አያሌው። ምሥጋና ይገባዎታል!!

    Reply
  2. birhanu teshome says

    December 12, 2017 03:27 am at 3:27 am

    1,2,3

    Reply
  3. M. D. Abba Gurach says

    December 20, 2017 07:20 pm at 7:20 pm

    The plight of our motherland will be reversed and reversed soon. Indeed, the salvation of our country has historically rested on the broad shoulders of Amaras and Oromos for the most part.

    It was the manufactured animosity between the two giants that has helped Woyanes to commit unspeakable crimes for so long.

    We will prevail over our eternal enemies including the Woyane tigres and their handlers in the spirit of Menelik, Gobena, Makonen, Balcha, Habte Giorgis, Gebeyehu, Geresu, Jagema, Omar Samatar, Afeworq, and the tens of thousands others who perished in the defence of our motherland.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule