• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰሚ ያጣ ሕዝብ

October 24, 2016 06:31 am by Editor Leave a Comment

ሕዝብ ተነሳ። ይህ ከወትሮው የተለየ አነሳስ ይመስላል። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ይህ ሕዝብ ተነስቶ ሲያበቃ እድሉን ለልጆቹ በአደራነት ሰጥቶ ሲቀመጥ፥ መሪዎቻችን የስልጣን ርክክብ አካሄደው ሕዝቡን በዜሮ እየሰደዱት ስልችቶታል። ቁጭ ብድግ ማለቱ በቃኝ ያለ ይመስላል። አሁን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መነሳቱ፥ የስልጣን ርክክብ ለማካሄድ ሳይሆን፥ ዳግም እንደገና መነሳት በማያስፈልገው ሁኔታ ስልጣኑን ራሱ ወስዶ ተረጋግቶ ለመቀመጥ ነው።

ቀድሞ ነገር ባለጉዳዩ ሕዝብ ቁጭ ብሎ መሪዎቻችን ሲተራመሱና ሕዝቡን ራሱን ሲያተራምሱት ምንም ያለማድረጉ በውጭ ለተመልካች ሲታይ ምንም እንደማያውቅ ያስመስለው ይሆናል። እውነቱን ብንመረምር ግን የምናስተውለው ሁሉን አዋቂ እንደሆነና፥ ዝም ያሰኘው ትዕግስቱ መሆኑ በገባን ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲታገስ መሬት ነው። ይሸከማል፥ ይችላል። ረዥም ጊዜ ይሰጣል። ፅዋ ሲሞላና ጊዜው ሲደርስ ይህ ሕዝብ ጠያቂ ነው። በውጭ ሲታይ ሕዝቡ ጉዳይ ፈፅሙልኝ ብሎ አቤቱታ የሚያቀርብ ይመስላል። ግን አሁን እንደዚያ አይደለም። ቀረብ ብለን፥ አጥልቀን ብናይ ይህ ህዝብ በመልካም አስተዳድሩኝ እያለ መንግስትን እየተማፀነ አይደለም። ደግሞም ስም ጠርቶ እከሌ ይግዛኝ ብሎም እየተሟገተ አይደለም። ሕዝቡ እያለ ያለው ስልጣን የሕዝብ ነውና ለሕዝቡ የስልጣን ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥ ድምፁ እንዲሰማ ነው።

መንግስት የሕዝብ ጥያቄ መልስ እሰጣለው ብሎ ጥልቅ ተሃድሶ ላካሂድ ብሎ ተነስቷል። ተቃዋሚ የሕዝብ ጥያቄ እመልሳለው ብሎ ሕገ መንግስት ለማርቀቅ ተነስቷል። በፊት ለፊት የማይታየውን እውነት ለማየት ብንጥር ግን ሕዝብ እያለ ያለው፥ ጊዜው የሁለቱም ተፎካካሪዎች የመምራት ጉዳይ ሳይሆን ሕዝቡ ራሱ የሚመራበት ወቅት መሆኑ ነው። ጊዜው መሪዎቻችን ስፍራቸውን ለሕዝቡ ምሪት የሚለቁበት እንጂ በየፊናቸው በነፍስ ወከፍ ለመምራት ሽር ጉድ የሚሉበት ጊዜ አይደለም። ይልቁንስ ሕዝብ መሪዎቹን ለመምረጥ የስልጣን ባለቤት ሆኖ፥ ድምፁ የሚሰማበትና የሚከበርበትን መድረክ ለማመቻቸት እንወያይና እንግባባ። መንግስትም ሰምቶ ይታዘዝ፥ ተቃዋሚም ሰምቶ ይቀናጅ።

የሕዝቡ ቆራጥነት የትዕግስቱ ውጤት ነው። ጊዜው እስኪደርስ ትዕግስቱ ሲገርም፥ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ ቁርጠኝነቱ የሚደንቅ ነው። ውሎ እንዲያድር ፋታ አይሰጥም። በውጭ ሲታይ ለብዙ ጊዜ የታየው ትዕግስቱ አሁንም አለ ብለን እንታለል ይሆናል። ሕዝቡ ከዝምታውና ከመቀመጫው ሲነሳ ቶሎ ብሎ መታዘዝ ማስተዋል ነው። የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ ብለን እንደለመድነው እንቀጥል ብንል፥ መሬት የሆነው ሕዝብ እሳት ሆኖ ይበላናል። ስልጣኑን የያዘው የሙጥኝ ማለቱን ትቶ፥ ተቃዋሚዉም ስልጣኑን መቋመጡን ትቶ፥ ሕዝቡ ልምራ ሲል በእሽታ ሁሉም የየግል ምኞቱን ለቆ ይመራ። ለዚህም ዓላማ ይህ ሕዝብ በእውነት የስልጣኑ እውነተኛ ባለቤት የሚሆንበትን መፍትኤ በአስቸኳይ ይመከርበት።

አሁን ልተርክ የተነሳሁት ፊት ለፊት ያለውንና ሁላችንም ያሰለቸንን፥ ግን እውነት ስለሆነው ታሪካችንና ተጨባጭ ሁኔታዎቻችን አይደለም። ደግሞም እውነቱ አድክሞኝ የሌለ ነገር ፈጥሬ አፈታሪክ ለማውራትም አይደለም። ዓላማዬ ፊት ለፊት ከሚታየው እውነት ጀርባ ያለውን ግዙፉን የማይታየውን እውነት አስተውለን፥ የሚገርመውን ነገር እንድናውቅ ነው። እንዴት ማለት ጥሩ ነው።  እንግዲህ ከስር መሰረቱ እንጀምር።

1ኛ/ ሕዝቡ የሚገርም ነው።

የሕዝቡ ማንነት የሚገርም ነው። በመሪዎቻችን ማንነት ሕዝቡ ማንነቱን ተጠልፎ መነጋገሪያ የሆነው የመሪዎቻችን ማንነት ነው። ማን ያውራ ስለ ደጉ ሕዝብ? ማን ያውራ በፍቅር ስለሚተሳሰበው ሕዝብ። ሲራብ አብልቶ፥ ሲጠማ አጠጥቶ፥ አብሮ ተቻችሎና ተጋብቶ ለዘመናት የሚኖረውና የሚያኖረው ሕዝብ ማን ማንነቱን ያራግብለት? ያደከመን በመሪዎቻችን ማንነት ላይ የተመሰረተ የፊት ለፊት እውነት እያወራን ስጋታችን መብዛቱ ነው። ሁሉም ዓላማውን የሚያራምደው ኢትዮጵያን የመሪዎቻችን ነፀብራቅ አድርጎ በመውሰድ ነው። ከላይ ላይ ከሚታየው እውነት ጀርባ የተደበቀውና በጊዜ ተፈትኖ ያለፈው ትልቁ ጥልቅ እውነት ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቤተሰብነት ነው።

2ኛ/ የሀገር ልጅ የሚገርም ነው።

መሪዎቻችን ሁሉ ሲታዩ ለየቅል ናቸው፦ ኢአዴግ፥ ግንቦት ሰባት፥ መድረክ፥ ሰማያዊ፥ ኦነግ፥ ወዘተረፈ። እንደገና ግልፅ ከሆነውና ከምናውቀው እውነት ጀርባ ያለውን የማይታየውን እውነት ለማየት ብንጥር ሁሉም የሀገር ልጆች ናቸው። ይህም በራሱ ክብር ነው፥ ምክንያቱም ከታላቁ ሕዝብ አብራክ የወጡ የሕዝቡ ልጆች ስለሆኑ ነው። የሀገር ልጆች ስለሆኑም በውስጣቸው ያለው እስከ ዛሬ ያልታየው ችሎታቸው ታሪክ ለመስራት አቅም አለው።

እነዚህ የሀገር ልጆች ድንቅ የሆነው ችሎታቸውና እምቅ አቅማቸው እስካልተገለጠ ድረስ አንዱ ሌላኛውን ለማጥፋት መሮጣቸውን አያቆሙም። ይህ ያልተገለጠው አቅም በውስጥ የሀገር ልጅነት እውን እንደሆነ ሁሉ በገሀዱ ዓለም እውን ሆኖ እንዲወጣ ተአምር ይጠይቃል። ተአምር ማለት ሲደረግ ታይቶ የማይታወቅና፥ ይሆናልም ተብሎ ሊታሰብ የማይችል ነገር ሲሆን ነው።

3ኛ/ ውይይትና መግባባት የሚገርም ነው።

በሀገር ልጆች ያለው እምቅ አቅም የሚገለጠው፥ በሕዝቡ ቆራጥ ግፊት መሪዎቻችን ውይይትና መግባባትን የችግራችን መፍቻ አድርገው መጠቀም ሲችሉ ነው። ይህ ተአምር የአገር ልጆችን እርስ በርሳቸው ተጨፍልቀው አንድ ወጥ እንዲሆኑ የሚያደርግ ሳይሆን፥ እያንዳንዳቸው ውይይትና መግባባትን ተክነውበት፥ ስልጣኑን ባለቤት ለሆነው ሕዝብ ማስረከብ የሚችሉበት መድረክ የሚፈጥር ነው። ተአምሩ ዲሞክራሲና እኩልነት አይደለም። እነዚህ እሴቶች ተአምራት ከሆነው ውይይትና መግባባት የሚገኙ ውጤቶች ናቸው። ይህም እንደ ድሮ በጠጉረ ልውጥ አሳላፊነት የሚካሄድ ሳይሆን በሀገር ልጆች ሽማግሌነት እውነትን ብቻ ዋና መሰረት አድርገው የሚተገብሩት ጉዳይ ነው።

ፊት ለፊት ያለውን የውጭውን ብቻ ለሚያይ ሰው፥ ውይይትና መግባባት መንግስትን በስልጣን የሚያስቀጥል ጊዜ መግዣ እኩይ ተግባር፥ ወይም ተቃዋሚን በአቋራጭ ስልጣን ላይ የሚያስቀምጥ መሰሪ ድርጊት አድርጎ ይወስዳል። የማይታየውን እውነታ ጠጋ ብሎ ለማየት የታደለ ግን፥ ውይይትና መግባባት እስከ ዛሬ ያልተፈተነ ተግባር ሆኖ፥ የሀገር ልጅነትን ውበት ከመሪዎቻችን ውስጥ አውጥቶ እንደ ብሩህ ብርሃን የሚያስፈነጥቅና፥ ለሕዝብ የስልጣን በላይነት ተገዥዎች እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው።

4ኛ/ የሚጠበቀው ነገር የሚገርም ነው።

ከእንግዲህ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ የለም። ማንም ላይታመን፥ ሕዝቡ ራሱን ብቻ ሊያምን ተነስቷል። ስልጣን የሕዝብ ነው እያሉ በስሙ የሚነግዱ ከእንግዲህ በቃችሁ ተብለዋል። ስልጣን የሕዝብ መሆኑን የሚናገር ሳይሆን በሕዝቡ ለመመራት ራሱን የሕዝቡ ተከታይ የሚያደርግ ብቻ ይፈለጋል። ከትልቅ ትዕግስት በዋላ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሕዝቡ የተነሳው፥ ለመንግስት ስልጣኑን የሚያስረዝምበትን መላ ለማፈላለግ፥ ወይም ለተቃዋሚ የስልጣን ውርስ እንዲያደርጉ ለማመቻቸት ሳይሆን፤ መሪዎቻችን የሕዝቡን ድምፅ እንዲሰሙ እና ስልጣንን ለባለቤቱ (ሕዝብ) ማስረከቢያውን መንገድ እንዲፈጥሩ ነው። ፈሪሃ ፈጣሪ ያለው ይህ ሕዝብ አምላክ እንዳለለት ይታወቅለት።

ኢሜል አድራሻ፦ ethioFamily@outlook.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule