• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እና የህወሓቶች አሻጥር (የሰነድ ማስረጃ)

February 25, 2018 01:54 am by Editor Leave a Comment

ጥቅምት 03/2010 ዓ.ም በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር። በወቅቱ “ይህን የተቃውሞ ሰልፍ ማን ነው የሚያስተባብረው?” የሚለው ጥያቄ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በውጪ የሚገኙ የኦሮሞ ልሂቃን የተቃውሞ ሰልፉን እንዳልጠሩ ሲገልፁ ነበር። በተመሳሳይ አዲሱ የኦህዴድ አመራር በጉዳዩ ዘሪያ እጁ እንደሌለበት መግለፁ ይታወሳል። በእርግጥ ሰልፈኞች ከወትሮ በተለየ መልኩ የኦነግን ባንዲራ ይዘው ታይተዋል። በአንፃሩ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ደግሞ ምንም ዓይነት አመፅና ሁከት እንዳይቀሰቀስ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ሲያደርግ ነበር። እኔ በግሌ ከታች የሚታየውን ፎቶ ሳነሳ ፖሊሶች ስልኬን ቀምተውኝ የነበረ ሲሆን ማንነቴን ከአጣሩ በኋላ ነው የመለሱልኝ።

በሌላ እንደ ዳኒኤል ብርሃኔ ያሉ ቀንደኛ የህወሓት ደጋፊዎች “የተቃውሞ ሰልፉ እየተመራ ያለው ከተጠበቀው በላይ ትልቅ በሆነ የህቡዕ ድርጅት” መሆኑን ሲገልፁ ነበር። እኔም ጥቅምት 08/2010 ዓ.ም “የኦሮሞን መብት የበላ ኦነግ፥ ግብፅ፥ ዕቡዕ፥…እያለ ሲለፈልፍ ይውላል!” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ፅሁፍ፤ “በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር ውስጥ በግልፅ ያልተለየ ‘ትልቅ የህቡዕ ድርጅት ተፈጥሯል’ በሚል ሰበብ በክልሉ ሕዝብ ላይ ሊፈፀም የሚችለው ግፍና በደል እንዳሳሰበኝ ገልጬ ነበር።

በእርግጥ ሰልፉ ላይ አንዳንድ የኦህዴድ አባላትና የደህንነት ሰራተኞች የኦነግ ባንዲራን ለሰልፈኞች ሲያድሉ እንደነበር በአካል ተመልክቼያለሁ። ይህ የተደረገበት መሰረታዊ ምክንያት ሰልፈኞች በአሸባሪነት የተፈረጀውን የኦነግ ባንዲራ በመያዝ ሁከትና ብጥብጥ እንዲያነሱ በማድረግ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ እንዲወጡ ማድረግ ነበር። ሆኖም ግን፣ ፖሊሶች ከክልሉ መንግስት በተሰጣቸው ጥብቅ መመሪያ መሰረት ከሰልፈኞች ጋር በመነጋገርና በመግባባት በሰልፉ ላይ ምንም ዓይነት ሁከትና ብጥብጥ እንዳይፈጠር ማድረግ ቻሉ። በተለይ በወሊሶ ከተማ ጥቅምት 03/2010 ዓ.ም የተካሄደው ሰልፍ ፍፁም ሰላማዊና በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተጠናቀቀ። ይህን ማያያዣ በመጫን የቪዲዮ ምስሉን መመልከት ይችላሉ።

ሰላማዊ ሰልፉ ከተካሄደ ከአስር ቀናት በኋላ ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም (በ28/10/2017) ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ከሚቴ አፈትልኮ የወጣ ሰነድ የተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ ለማወቅ ተችሏል። በጥቅምት ወር በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ዋና አስተባባሪዎች የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ናቸው። የዚህ መሰረታዊ ዓላማ፣ አንደ አቶ ዳንኤል ብርሃኔ አገላለፅ፣ የተቃውሞ ሰልፉ የሚመራው በአዲሱ የኦህዴድ አመራር ውስጥ ሰርጎ በገባ “ከተጠበቀው በላይ ትልቅ በሆነ የህቡዕ ድርጅት” እንደሆነ በመግለፅ በተለይ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ ነበር። ከታች በምስሉ ላይ የሚታየው ፅሁፍ የህወሓቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ያቀረቡትን የውሳኔ ሃሳብና የወደፊት አቅጣጫ ነው፡-

አሁን-ያለንበት-ሁኔታ-የኔ-ድምዳሜዎች-ስራ-አስፈፃሚ ገፅ 1-2 (ከዶ/ር ደብረፂዮን ኮምፒውተር ተሰርቆ የወጣ ሰነድ)

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ከኦህዴድና ብአዴን አመራሮች በገጠመው ጠንካራ ተቃውሞ ምክንያት ውድቅ መደረጉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ህወሓቶች ከአስራ ስድስት አመታት በፊት የወጣ “የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት” የሚባል አዋጅ ከተጣለበት አንስተው አመጡ። በድጋሜ የምክር ቤቱን ዝርዝር የአተገባበር ዕቅድና ዓላማ የያዘ ሰነድ አፈትልኮ መውጣቱ ይታወሳል። ይህ ሰነድ በሀገሪቱ የዘር ማጥፋት እየተከሰተ መሆኑን በመጥቀስ ግጭትና አለመረጋጋት ካለባቸው አከባቢዎች የክልል ፖሊሶችን ማስወጣትና የክልሎች ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዎች ስለ ግጭቱ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሚዲያዎች መግለጫ እንዳይሰጡ የሚከለክል ነው።

አሁን-ያለንበት-ሁኔታ-የኔ-ድምዳሜዎች-ስራ-አስፈፃሚ ገፅ 3-4 (ከዶ/ር ደብረፂዮን ኮምፒውተር ተሰርቆ የወጣ ሰነድ)

የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ ሰነድ ይዘት የህወሓቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ለኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። በአጠቃላይ የምክር ቤቱ ዓላማና የተግባር እቅድ በኦህዴድና ብአዴን ተቃውሞ ውድቅ የተደረገው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በብሔራዊ የደሀንነት ምክር ቤት በኩል ተግባራዊ ማድረግ ነው። ነገር ግን፣ በምክር ቤቱ ም/ሰብሳቢ የሆኑት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ የታለመለትን ዓላማ ማሳካት እንዳልቻለ ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ አንዳንድ የክልል መስተዳደሮች የምክር ቤቱን ዓላማና ግብ ለማስፈፀም ተባባሪና ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል።

ከዚያ በመቀጠል አራቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች 17 ቀናት የፈጀ ስብሰባ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዚህ ስብሰባ ኦህዴድ እና ብአዴን በአንድ ወገን፣ ህወሓትና የእሱ መጠቀሚያ እየሆነ ያለው ደኢህዴን ደግሞ በሌላ ወገን ሆነው ባደረጉት ፍጭት የመጀመሪያዎቹ ሙሉ በሙሉ አሸንፈዋል። ነገር ግን፣ የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በኢትዮጲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ-EBC) በኩል የተሰጠው መግለጫ ከስብሰባው ውጤት ፍፁም የተለየ እንደነበር ይታወሳል። በእርግጥ መግለጫው ጥሩ የሆነ ፖለቲካ ነክ ድርሰት ወይም ቲያትር እንጂ የስብሰባ መግለጫ አይመስልም። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ አራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሊቀመንበሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሳለፈው ውሳኔ በቴሌቪዥን ከተላለፈው መግለጫ ጋር ለየቅል እንደሆነ በተግባር ተመልክተናል።

ባለፈው ወር የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለአስር ቀናት ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሳለፋቸው ውሳኔዎች ያለ ምንም መሸራረፍ ተግባራዊ እንዲደረጉ መጠየቁን ተከትሎ በመቶች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ተፈትተዋል። ሆኖም ግን፣ የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር የሆኑት ኦቦ በቀለ ገረባን ጨምሮ አንዳንድ የፖለቲካ እስረኞችን ባለመፈታታቸው ምክንያት ከየካቲት 03/2010 ጀምሮ የገበያና የስራ ማቆም አድማ መጠራቱ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የፌደራሉ መንግስት እነ በቀለ ገረባ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ፈትቷል።

ጥቅምት 03/2010 ዓ.ም እና የካቲት 03/2010 ዓ.ም በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች ፍፁም ተመሳሳይ እንደሆኑ ለመገንዘብ ችያለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ አዲሱ የኦህዴድ አመራሮችና ለእነሱ ቅርበት ያላቸው ልሂቃን በአምስት ወራት ልዩነት በተመሳሳይ ቀናት የተጠሩት የተቃውሞ ሰልፎች እንዲካሄዱ ፍላጎት አልነበራቸውም። የኦህዴድ ፅ/ቤት ኃላፊ የካቲት 04/2010 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች እየተካሄደ ያለው አድማና ተቃውሞ ከዛሬ ጀምሮ መቆም እንዳለበት መናገራቸው ይታወሳል። የክልሉ ፖሊሶችን ጨምሮ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል። ለምሳሌ በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ የከተማ ካንቲባዋ በአካል በመገኘት ሰልፈኞችን ሲያነጋግሩና ሲያረጋጉ ተስተውለዋል።

በተመሳሳይ ቀን በወሊሶ ከተማ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊሶች በኃይል ለማስቆም ጥረት በማድረጋቸው ምክንያት ከሰልፈኞች ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ አስገብቷቸው ነበር። ሆኖም ግን፣ በቀጣዩ ቀን (የካቲት 04/2010 ዓ.ም) እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የከተማና የአከባቢው ነዋሪዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ የፖሊስ አዛዡ በአካል ቀርቦ ሰልፈኞችን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተደርጓል። ይህን ተከትሎ በዕለቱና በማግስቱ በከተማዋ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊሶችና ሰልፈኞች መካከል በጥቅምት 03/2010 ዓ.ም የታየው ዓይነት መግባባት ተፈጥሯል። በመጨረሻም የካቲት 04/2010 ዓ.ም በወሊሶ ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ልክ ጥቅምት 03/2010 ዓ.ም እንደተደረገው ፍፁም ሰላማዊ ከመሆኑም በላይ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ነው የተጠናቀቀው።

የኦህዴድ አመራሮች ለክልሉ ፖሊሶች ጥብቅ መመሪያ በመስጠት፣ እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችን በማስተባበር በአምስት ወራት ልዩነት በተመሳሳይ ቀናት የተካሄዱትን የተቃውሞ ሰልፎች በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ የነበረበት መሰረታዊ ምክንያት አንድና አንድ ነው። ምክንያቱም ህወሓቶች እነዚህን የተቃውሞ ሰልፎች የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ መንደርደሪያ እንደሚያደርጏቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ። “የፈሩት ይደርሳል፣ የጠሉት ይወርሳል” እንደሚባለው ኦህዴዶች እንዳይመጣ የሸሹት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከስድስት ቀናት በኋላ በቴሌቪዥን በኩል ተመልሶ መጥቷል።

በዛሬው ዕለት ወጣ የተባለው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ዶ/ር ደብረፂዮን በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ ካቀረበው የውሳኔ ሃሳብ፣ እንዲሁም ከብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት የተግበር ዕቅድ ጋር ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ የካቲት 09/2010 ዓ.ም የታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ እንደተሰጠው መግለጫ በኢብኮ በኩል የቀረበ ድርሰት ነው። ምክንያቱም የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የታወጀው በተለይ የኦህዴድና ብአዴን አመራሮች በአዋጁ አስፈላጊነት ላይ ሳይስማሙ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል የሆኑት የፌደራል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቪኦኤ በሰጡት አስተያየት “የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጅ የሚያስፈለግበት ሁኔታ አለመኖሩን” ተናግረዋል። ዶ/ር ነገሪ ይህን በተናገሩበት ቅፅበት “ለምን እንደሆነ ባይታወቅም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚዲያዎችን ለ7፡00 መጥራቱን” የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ በፌስቡክ ገፁ ዘግቧል። ነገር ግን፣ ከ11፡00 ሰዓት ላይ የምክር ቤቱ ስብሰባ እንዳልተቋጨ በመናገር ሚዲያዎቹ ወደመጡበት እንዲሄዱ ከተነግሯቸው በኋል በምሽቱ የኢብኮ ዜና ላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁ “በሰበር ዜና” ብለው አቀረቡ።

ከላይ ከተጠቀሰው የዶ/ር ነገሪ አስተያየት እና የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ጥቆማ የኦህዴድና ብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ስለ አስቸኳይ ግዜ አዋጁ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ያሳያል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በትላንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ሰራተኞች ስለ አስቸኳይ ግዜ አዋጁ አስፈላጊነት ሲወያዩ እንደነበር ለማወቅ ችያለሁ። በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የአማራ ብዙሃን መገናኛ እኔን ጨምሮ የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ አስፈላጊነት ዙሪያ አወያይቶናል።

በአጠቃላይ የኦሮሚያና የአማራ ክልል መስተዳደሮች በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ አግባብነት ዙሪያ ሕዝቡ ሃሳብና አስተያየት እንዲሰጥ እያደረጉ ነው። በአዋጁ ዙሪያ የራሳቸውን አቋም ለመያዝ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። በመሆኑም የኦህዴድና ብአዴን አመራሮች በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ዙሪያ ከስምምነት ላይ አልደረሱም። ስለዚህ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ህወሓት ፍርሃቱን ለማስታገስ በቴሌቪዥን የሚያስነግረው ውሸት ነው። ከላይ በቀረበው የሰነድ ማስረጃ በዝርዝር እንደተገለፀው፣ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በዶ/ር ደብረፂዮን የተፃፈ የህወሓቶች አሻጥር ነው፡፡ (ፎቶ፤ ጥቅምት 03/2010 ዓ.ም በወሊሶ ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ (ethiothinkthank))

(ምንጭ: Seyoum Teshome, Ethio Think Tank)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule