• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የጥላቻው ምንጭ … ፖለቲከኞች፣ ብሔረተኞች፣ የጥላቻ ሰለባዎችና ጽንፈኞች የሚተፉት መርዝ ነው” ኦባንግ

August 9, 2020 01:35 am by Editor Leave a Comment

“በኦሮሚያ ክልል በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት  ከሰውነት፣ አብሮነትና ኢትዮጵያዊነት ይልቅ በሃሰተኛ ትርክትና በማንነት ጥላቻ ላይ ለበርካታ ዓመታት ሲሰራ የነበረ ስራ ውጤት ነው፤ ሊወገዝ የሚገባው የከፋ ድርጊት ነው ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ተናገሩ።

በኢትዮጵያዊነትና ሰብዓዊነት ላይ የሚሰሩ ድርጅችን በማቋቋም የሚንቀሳቀሱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ አባንግ ሜቶ ከሰሞኑ በዝዋይና ሻሸመኔ ተዘዋውረው ጉዳት የደረሰባቸውን ግለሰቦች አነጋግረዋል።

ከጉብኝታቸው መልስ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታም ሰኔ 22 ሌሊት ጀምሮ በተፈጠረው ጥፋት የተጎዱ የ17 ግለሰቦችን ቃል መቀበላቸውን ተናግረዋል። በተፈጸመው ድርጊት የደረሰው ጉዳት ልብ የሚነካ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ይደረጋል ተብሎ የማይጠበቅ አሰቃቂ አገዳድል የተፈጸመበት አሳዛኝ ክስተት ነው ሲሉ ገልጸውታል።

የጉብኝታቸው ዓላማም ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መሬት ላይ ያለ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ብሎም ተጎጂዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እንደነበር አውስተው፤ ድርጊቱ በተራ ግርግር የተፈጸመ እንዳልሆነ ማረጋገጣቸውን ገልፀጸዋል።

ከዚያ ይልቅ በአርቲስት ሃጫሉ ሰበብ ሆነ ተብሎ በተደራጀ አካል ስም ዝርዝር የወጣባቸው ሰዎች እየተመረጡ ግድያ እንደተፈጸመ ቤት ንብረታቸውም ከጎረቤት በተለየ ተመርጠው እንዲወድሙ መደረጉን ተናግረዋል።

በተለይም “ነፍጠኛ” በሚል ቃል የተለዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን እንዳረጋገጡ ነው የተናገሩት። “ድርጊቱ የትናንት ውጤት ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ፤ ትናንት ኢትዮጵያዊነት፣ አብሮነትና አንድነት ላይ ሳይሆን ‘ነፍጠኛ’ በሚል በአንድ ህዝብ ላይ ላይ ያነጣጠሩ ዘር ተኮር የጥላቻ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰዋል።

“በተለይም ህወሃት የሐሰት ታሪክ በመፍጠር፣ ሰዎች ከሰውነት ወጥተው ማንነታቸው ብሔር ብቻ እንዲሆን መደረጉ፣ እኔና እነሱ በሚል ክልል በመፍጠር እርስ በርስ የጥላቻ ስራዎች መሥራቱ ነው” ሲሉ ለአብነት አንስተዋል።

“የተዘራው ኢትዮጵያዊነት፣ ሕብረት፣ እኩልነት፣ ሰላም፣ መከባበር ሳይሆን ዘረኝነት፣ ጥላቻ፣ ቂም በቀልና የሃሰት ትርክት” እንደሆነ ገልጸዋው፤ የተዘራው መጥፎ ዘርም መጥፎ ፍሬ አፍርቷል” ብለዋል።

በተለያዩ ጊዜያት የተፈጠሩ አሰቃቂ ጥቃቶች በማስታወስም “ሰዎች ሰውነታቸውን እንዲረሱ፣ በትምህርት ስርዓቱም ጥላቻ ያነገቡ፣ የአገር ፍቅር የማያውቁ፣ ንቃተ ህሊና የሌላቸው ወጣቶች በማፍራት ለጥፋት መጠቀሚያ መሳሪያ ተደርገዋል” ሲሉም ያብራራሉ።

መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰቱ ድርጊቶች ትምህርት ሊወስድ እንደሚገባ መክረው፤ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ግጭት በሚል ሳይታለፉ፤ በጉዳዩ ላይ በግልጽ በመነጋገርምር ጥፋተኞችን ተጠያቂ ማድረግ ይገባል ይላሉ።

“ለሰው እንጂ ለብሔር አልወግንም” የሚሉት አቶ ኦባንግ ሰዎች በታዋቂነት ብቻ ሳይሆን በሰውነታቸው ሊከበሩ፣ ሲሞቱም እኩል እንዲታዘንና ክብር እንዲሰጥ፤ መላው ኢትዮጵያዊም ድርጊቱን በጋራ እንዲያወግዝ አሳስበዋል።

መንግሥት በሺዎች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች መያዙን ቢገልጽም፤ ጥፋቱ ተራ ግጭት ባለመሆኑ በማንና እንዴት እንደተፈጸመ ግልጽ መረጃ መስጠት አለበት ብለዋል። ይህ ካልሆነ ፍትህ ሊሰፍንም ሆነ የተጎጂዎች ህሊና ቁስል ሊሽር አይችልም ብለው ወደፊት ሌላ ተመሳሳይ ድርጊት ላለመፈጸሙ ዋስትና የለም ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል።

ድርጊቱ መላውን የኦሮሞ ህዝብና የእስልምና እምነት ተከታዮችን እንደማይወክል ገልጸው፤ በጥፋቱ ወቅት ስም ዝርዝር ወጥቶ ሲፈለጉ የነበሩ ተጠቂዎችን ህይወት እየደበቁ ያተረፉ ጎረቤቶች እንደነበሩ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

“የጥላቻው ምንጭ ከታችኛው ህዝብ ሳይሆን ሥልጣን ላይ ለመውጣት በሚፈልጉ ፖለቲከኞች፣ ብሄርተኞች፣ የጥላቻ ሰለባዎችና ጽንፈኛ ቡድኖች የሚተፉት መርዝ ነው” ሲሉም አብራርተዋል።

ሰው ከመሆን ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሚገልጹት አቶ ኦባንግ፣ በየትኛውም ቦታ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው እንደሚገባ አብራርተዋል።

መንግሥት የችግሩን ምንጭ ከሥሩ በመረዳት “ሕገ መንግሥት ከማሻሻል ጀምሮ፣ በዘር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካን ማከም፣ ተደራጅተው ሰዎችን የገደሉ አካላትም በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ተጠያቂ ማድረግ ይገባዋል” ሲሉም አሳስበዋል።

ለአንድ ህዝብ ተለይተው የሚሰጡ “ነፍጠኛ” የመሳሰሉ ቃላትም ሰዎችን ከሰውነታቸው የሚነጥሉና ለጥቃት የሚያጋልጡ መሆናቸውን በመግለጽ ሊወገዱ እንደሚገባ ነው አቶ ኦባንግ ሜቶ የተናገሩት ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Interviews, Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule