
የጋምቤላ ምርጥ “ቶክ” አንገቱን ደፋ
የኢትዮጵያው ቡናው እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ የጋምቤላ ምርጥ ውጤት ቶክ ጀምስ ይርጋለም ላይ በአንዳንድ የሲዳማ ደጋፊዎች በዝንጀሮ ድምፅ በቆዳ ከለር ተሰድቧል።
በቦታው የነበሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊው ቶክ በድንጋጤ ከሜዳው ወጥቶ የተቀያሪ ወንበር ላይ አንገቱን አቀርቅሮም ታይቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የግለሰቦች ስም እየጠሩ የሚሳደቡ እንዳሉ ይታወቃል።
በውጭ አገር ተጨዋቾች በሌሎች አገር ደጋፊዎች ከቆዳ ከለር ጋር በተያያዘ ሲሰደቡ በእኛ አገር ደግሞ ዘረኝነት በራሱ ዜጋ ሲሰደብ ከማየት ምን የሚያስደነግጥ አለ?
ቶክ በወገኑ እንደ ዝንጀሮ ተሰድቦ አንገቱ ደፍቷል፤ ይህ ነገር ወደፊት በድጋሚ እንደማይከሰት ምን ማረጋገጫ ይኖራል? (ኢቲዮኪክአፍ እናመሰግናለን)
**********
ምንጭ: ድሬ ቲዩብ ላይ ተለጥፎ በነበረ ጊዜ የተወሰደ
ለወንድማችን፡ቶክ፡ጀምስ፣እግዚአብሔር፡የሰጠህን፡አትፈርበት።ዝንጆሮዎቹ፡እንደ፡ዝንጀሮዎቹ፡ጯሂዎች፡ናቸው።በ፡ሀገርህ፡ላይ፡በሀገርህ፡ልጆች፡ድንቁርና፡
በመደረጉ፡ቅርር፡አትሰኝ።ሐፍረቱ፡በ፡እነሱ፡ይሁን።ለግዜው፡ያናድዳል።ካሰብክበት፡ግን፣ምንም፡አይደል።አንተን፡መስደብ፡ማለት፡ፈጣሪህ፡እግዚአብሔርን፡
መስደብ፡ስለ፡ሆነ፣እግዚአብሔር፡ለሰዳቢዎችህ፡ሁልሉ፡ሰዳቢ፡ያወርድባቸዋል።ጉብዝናህን፡አጠናክረህ፡አጨዋውትህን፡ቀጥል።እንደዚያ፡የጮሁት፡ጐበዝ፡
ስለ፡ሆንክ፡ቀንተውብህና፡የምቀኝነት፡ነው።አይዞህ!!።ለ፡ዓላማህ፡እንጂ፣ለስድብ፡ተገዥ፡አትሁን።እግዚአብሔር፡ብርታቱን፡ይስጥህ።
I love it,nice
A society that has no accomplishments, has lost self confidence and might look down others to feel better. When this character passes to the next generation, it becomes culture. It has been a culture for long long time, but it can be reversed
it absolutely shame work for us,why we division between us?we have one ancestor, why we are trying to make difference between us?
this is strongly strongly … enough ….
አናንተ የሲዳማ ደጋፊዎች ድንጋይ ራሶች!!! መጀመሪያ ጽዳት ተማሩ