ኢህአዲግ ለሚቀጥሉት አርባ ዓመታት ለመግዛት በማለም፣ ላለፉት ዓመታት የሚከተለውን የአስተዳደርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ „በባለ ራዕዩ“ መሪያቸው የ ተነደፈውን ባደባባይ ለውይይት ለማቅረብ እየሸነጠው ነው። በመሰረቱ ወጣም ወረደ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ይህ ፖሊሲ በተግባር ይውል እንደነበረ ባለሙያዎች ሆኑ የውጭ ሀይሎች ደጋፊዎቻቸው የሚያውቁትና የአደባባይ ምስጢርም ነው።
አሁን ግን ይበልጡን ጡሩንባ ተለቆለት፣ ባደባባይ እንዲወጣና አዲስ የሚነዳ የርዕዮተ ዓለም ፈረስ ሆኖ ብቅ ያለው፣ የቀድሞው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቲዎሪ ነዳጅ ስለ አለቀና የሚያሳምን ስም ስላላተረፈ፣ ለአገዛዝ ማሰንበቻ፣ በልማት ስም፣ ልማታዊ መንግሥት /developmental state/ የሚባለው የተወሰነና ከዛኛው የበለጠ ሌጂትሜሲ/ ተቀባይነት ያስገኛል በሚል ምኞት ነው።
በተለይም በልማት ሰበብ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች የተረገጡበት ስርዓትን ታቅፎ ለመሰንበት፣ ያለአንዳች ማህበራዊ ቁጥጥርና እስካሁን የበላይነት ባገኙት፣ በተወሰኑ ቡድኖች ፍቃድ ስር ህዝብ እንዲማቅቅ፣ ሀገሩ የአለም አቀፍ በላሃብቶችና የአዳዲሶቹ የጅ አዙር ቅኝገዢዎች መፈንጫ እንዲሆን የተተለመ አስተዳደር ነው።
ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪቃም ጭምር ይህ የተጠነሰሰላት የአዲሱ አይዲዮሎጂ ፍሬ ነገር ምንድን ነው? (Click here to read the analysis in English)
Leave a Reply