• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ!

May 28, 2014 12:16 am by Editor 3 Comments

እኔ ወ/ሮ እታገኝ መኮንን ካሣ አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 760/ሀ ነዋሪ ነኝ፡፡ በአሁኑ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ከላይ ቁጥሩ በተገለፀበት ቤት ከ40 ዓመት በላይ ተከ ራይቼ ስኖር በ1990 ዓ.ም በኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ መያዜን አወኩ፡፡

ቤቴንም ሆነ ልጆቼን እን ዲጠብቅልኝና እንዲረዳኝ በማለት ከ1994-1997ዓ.ም ድረስ በውክልና ሰጥቸው የነበረ ሲሆን ከ97 በኋላ ግን ውክልናውን ትቶ የራሱን ቤት ሰርቶ ሄዷል፡፡ ቤቱ እስከታሸገበት ጥር 12 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ለአቶ ደረጄ ጎዳና ከመንግስት ተከራይ በማስመሰል በቤት ቁጥር 760/ሐ በአቶ ደረጄ ስም የአንድ አመት (በ1998 ዓ.ም) የቤት ኪራይ በስማቸው ቀበሌ ሂዶ ከፍሏል በማለት እኔ ደካማና በሽተኛዋን የፍርድ ቤት ውሳኔ ነው በማለት ቤቴን ጥር 12 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በመ ድኃኒቴ እና በንብረቴ ላይ በማሸግ በእኔም ሆነ ቤተሰቦቼን ከፍተኛ ችግር ደርሶብናል፡፡

ሆኖም መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም እኛን በፖሊስና በመሣሪያ ኃይል ከግቢ ውስጥ አስወጥተው ንብረቴን በሌለሁበት አውጥተውብኝ እኔ ስምንት ቤተሰቤን ይዤ ዕቃ ቤት እንድኖርና ግማሹ ንብረቴን ውጭ ተጥሎ ለዝናብምና ለፀኃይ እንዲጋለጥ በማድረግ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስብኝ አድርገዋል፡፡

በየደረጃው ላሉት የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ አቤት ብልም ቤቱን ለፈለጉት ሠው ለመስጠት ሲሉ ያላደረኩትን አድራጎት እያቀረቡ ጥፋተኛ ነሽ በማለት ለረዥም ወራት እያንከራተቱኝ መሄጃው ጠፍቶብኝ እገኛለሁ፡፡

ሁከት ስለፈጠሩብኝ ይወግድልኝ ጥያቄ ለፍርድ ቤት ባቀርብም የወረዳ 09 ቤቶች ልማት ፅህፈት ቤት የሀሰት ማስረጃ እያቀረቡ ሁከት አልፈጠረም በማለት ውሳኔ ተሰጠብኝ፡፡ በበኩሌ በ2005ዓ.ም ይግባኝ ብልም ወረዳውን መጥራት ሳያስፈልገኝ የተሠጠው ውሳኔ ትክክል መሆኑን አረጋግጭአለሁ፤ መልስ ሰጪውን መጥራት አያስፈልግምብሎ መዝገቡን ዘግቶብኛል፡፡

እንዲሁም ሠው ሁልጊዜ ከማስችገር በማለት ትንሽዬ የሸራ መጠለያ አድርጌ ከሰል ቸርችሬ የማድርባትን መጠለያ የደረጄ ነው በማለት ግቢው ውስጥ ሁለት ክፍል አድርገው ቀምተው ሰኔ 16/2004 ዓ.ም ለአስቴር መለስና ለጌታቸው መለስ የልማት ተነሺ ናቸው በማለት ሰጥተውብኛል፡፡ አሁን ደግሞ የምኖርበትን ከመንግስት በየአመቱ የምዋዋልበትን ቤት ለኃይልና ለውኃ ልማት በፃፉት ደብዳቤ ቤቴ መሆኑን በማመልከቻ ላይ ገልጸውልኛል፡፡

እኔ እታገኝ መኮንን በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 09 መንግስት ቤት ቁጥር 760ነዋሪ መሆኔን በ26 ዝውውር 2006 እስከ ዛሬ እኖርበት የነበረውን መኖሪያ ቤት ለልማት ተነሺዎች የተሰጠ መሆኑን በደብዳቤያቸው አረጋግጠዋል፡፡

እኔ የ63 አመት አዛውንት የሙት ልጆች ይዤ ብርድና ፀሀይ እየተፈራረቀብኝ እገኛለሁ፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ እላለሁ! (ምንጭ: – ነገረ ኢትዮጵያ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. mahi says

    May 29, 2014 11:16 am at 11:16 am

    berasachewu bet ema edi mederegi yelebetm 🙂 meseteti alebachewu betachewu 🙂 hgi yelem ede 🙂 qoyi ede

    Reply
  2. በለው ! says

    May 29, 2014 03:50 pm at 3:50 pm

    “በዚሁ የየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ ፰ ውስጥ ሁለት ተያያዥ ቤቶች አሉ። ሁለቱ ተከራዮች ቢያንስ ቤቱን ከመንግስት ተከራይተው የኖሩበት ከ፶ዓመት በላይ ነው። አንደኛዋ ተከራይ ፫ የደረሱ ልማታዊ ልጆችና አንድ በራሱ የተመካ መሀንዲስ አማች አላቸው። ሁለተኛዋ ተከራይ ፮ ልጆች ሲኖራቸው ፫ከዚህ ዓለም አልፈዋል።የሁለቱም ቀደምት ኖሮ ዝቅተኛና ተመሳሳይ ነበር። ሁለቱም ተከራዮች የመግቢያ ጠፈጠፍ ሲያስቸግራቸው በአንድ ቆርቆሮ ዕርዝምት በረንዳ ዘርግተው ለመሸፈን ሲፈልጉ ልጆችና አማች ያላቸው ፍቀድ አጝኝተው መሠረቱ በኒሚንቶ ቋሚው በብረት አራት ቆርቆሮ ድርድረው ሠርተዋል። ሁለተኛዋ ተከራይ ግን ቆርቆሮውን አቁመው በረንዳውን በእንጨት ቀስት እነጂ በብረት ለመሥራት አልተፈቀደላቸውም።(ዳግማዊ ደርግ!)…. በዚያን ዘመን ሁለት ቀበሌ ተመራጮች ለ፲፯ዓመት የቤት ኪራይ ሳይክፍሉ በመጣው ምርጫ ሁሉ የማሟያ ምርጫ እየተባለ ሲጠቀሙ ኖረዋል ዛሬ በኢህአዴግ የኪራይ ቤታቸውን ባላቤት ሆነው ሸጠው በጥሩ አሸናኘት ተደርጎላቸው መላ ቤተሰባቸውን ይዘው በአሜሪካ ይኖራሉ። ይህ ነበር የኖርንበት እሳቸውም ሚኖሩበት አለም!!

    **በውጭ ሀገር ተቀምጣችሁም እያማሰላችሁም ያሳረራችሁን..ሀገራችሁ ገብታችሁ ፵/፷ የምታበስሉ…ፖለቲካ በድረ ገፅ የምትቀቅሉም ይሁን..በፓልቶክ የምትቆሉ…ይህ የተዘበራረቀ በቀለም ያበደ ባንዲራ ይዛችሁ የሰው ሀገር የምትቀውጡም…የፀሐዩ መንግስት እያላችሁ እንጀራና ቅመማቅመም ከሕዝብ ጉሮሮ ነጥቃችሁ በመሸጥ የከበራችሁ…ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሃይማኖት ቋንቋ መልካም ሥነምግባርን ጥለው የባዕድ ይዘው ገደል እንዲገቡ ጥረት የምታደርጉ እራስ-ወዳዶችም ብትሆኑ…ለግል ጥቅም አድርባይነት..አውርቶ-አደርና ሠርቆ-አደር መሆን ዘለዓለማዊ ለሚመስላችሁ…በቀን አስር ግዜ እየበላችሁ ለወገኖቻችሁና ለፆም-አዳሪው ወጣት ትውልድ የማቀጣጠያውና መቃጠያው ነዳጅ የምታቀብሉ ዲያስፐርስ…ዘረኝነትን ሙስናን ጎጠኝነትን ዘርታችሁ የድሃ ልጅ በጥይት ለምታስቀጥፉ ሁሉ…የምታመጡት ለውጥ ከነበረው የተሻለ እንጂ ጭራሽ በመከፋፈልና በጎሪጥ በመተያየት ጥቅማጥቅመኞት(ለልማት ተነሳሺ!) ካድሬ… ታማኝ ምሁራን…አክቲቪስት አርቲስት ኢንቨስትር…ተብለው ሥርዓቱን እንዳለ ያለ ‘ተፎካካሪ ተወዳዳሪ አማራጭ’ ፓርቲና የነፃ ሚዲያ እራሱ አውርቶ.. እራሱን አድንቆና አጨብጭቦ እንዲቀጥል ለሚያደርጉ ምቹ ሁኔታን መፍጠራችሁ እነደሆነ ልትገነዘቡ ይገባል። ዝምታም ትብብር ነው!።ከበላተኛውም ጎን ሆኖ በሌላ አጀንዳ ንጹሕ ሕዝብን ማተራመስም ሥርዓቱን መተባባር ነው!።

    **አቶ መለስ ” እኛ ለሽማግሌውና ለአዛውንቱ ግድ የለንም እኛ የምንፈልገው አዲሱ ትውልድ እንዲከተለን ብቻ ነው” ብለው ነበር…አዎን! በዚህ ዘመን በአራቱም አቅጣጫ(ማዕዘን) የሚሰራው ይህ ነው። ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያ ታሪክ የላቸውም የሚያስተምሩት ብሄርና የግለሰቦችን ራዕይ ነው.. ሽማግሌና አሮጊት የድሮ ሥራዓት ናፋቂ ይባላሉ ግን ያለ እነኝህ ዜጎች አስተዋጽዎ ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር።፡አዲሱ ትውልድ እነደፈለጉት የሚነዱት የቁም ከብት ሆኖ ተከልሎና ተከልክሎ ጸጥ ብሎ ይገዛል!! ዕለታዊ ጉርሱን በቀን አበልም ይሁን ጥቅማጥቅም ካገኘ እናቱን ለገንዘብ ያስማማል… እናት በሎ ሀገር አደለምን!?ቻይና ሕንድ ዓረብ ቱርክ ሲከራየውና ሲገዛው መች እንቢኝ አለ!? ዙሪያውን ይጨፍር የለምን! ታዲያ እርስ በእርሱ ሲሆን ሜንጫ ስሎ! ሽመል ቆርጦ እሳት ጎርሶ.. እሳት ልሶ አቃጥሎ በጥይት ይቃጠል ለምን!? አልቅስ ያለው ዓይን ጭስን አጥብቆ ጠየቀ!

    ***አቶ ኀይለመለስ “ኢትዮጵያዊነት ደምቋል አሉ” በሸውራራ ዓይን መነፅር ተደርጎ ተጥበርብሮባቸው ካልሆነ ወይንም ይህ ዙሪያውን የሚጠዛጠዘው ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አደለም ካላሉ ወይንም እራሳቸው እንዲበጣበጥ ከላዘዙና በእጅ አዙር እንቨስት ካላደረጉ በቀር የደመቀች ኢትዮጵያ የት ነሽ? ወይ ተበድሮና ለምኖ መድመቅ!? ፻፷፮ ኪሎ ሜትር ወልቂጤ ከተማ እሳት አዳጋ መኪና የሌላት የ፷፭ዓመት አዛውንት ፰ቤተሰብ ይዘው ቤታቸው ተነጥቆ ዜግነታቸው ተረግጦ ይህ ዕድገት…ሠርቶ በማፍረስ የት ይደርሳል! እነኛ በበረሃ የአሞራ እራት ሆነው የቀሩ ታጋዮች ጭቆናን አስወግደው ብላ ተባላን መርሆአችን፣ አንድነታችን እፍረታችን!ብሔር!፩ ብሔረሰብና፪ ሕዝቦች ፫ (የአፓርታይድ ከተማ) መስርተው ልዩነታችን ውበታችን! ብለውን ለመናገር.. ለመንቀሳቀስ.. ለመሰብሰብ..ለመዘዋወር..ለመሰለፍና ሞተንም ለመቀበር አሳውቀን አስፈቅድንና ለምነን በፍርሃት እንድንሸበብ አድርገው ከልለውና አስከልክለው ለእራሳቸው ለቤተሰባቸው ለወገኖቻቸው ለእኛና ለኢትዮጵያ ሳይሆኑ ገድለውን ለምን አረፉ!!!?ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን!

    Reply
  3. abikiya says

    May 29, 2014 11:57 pm at 11:57 pm

    Not fair

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule