የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ዛፍ ላይ ሆነህ እንቅልፍ ይወስድሃል? ሸለብ እንኳን ያደርግሻል ዛፍ ላይ ሆነሽ? እነደዚያ ነው የአባይ ጉዳይ ለግብጽ። ይኽ እንቅልፍ ማጣት እና ስጋት ዛሬ የጀመረ አይደለም። ባጭሩ ልተርክ። ሪቻርድ ፓንክረስት በግብጽ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ3 ሺ አመቶች በፊት ጀመሮ የግብጽ ነጋዴዎች በእግራቸው የአባይን ወንዝ ዳርቻ ተከትለው እንዲሁም በቀይ ባህር በነፋስ በሚገፉ ጀልባዎች ዛሬ ኢትዮጵያ (ያኔ የፐንት ግዛት) በሚባለው ግዛት ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን እና ግዛቱን ምድረ ታ-ኔትጄሩ (Land Ta-Netjeru) ማለትም “ምድረ አማልዕክት” እንደሚሉት እና “የመጀመሪያ አገራችን ነው” ይሉም እንደነበር የኢትዮጵያውያን ድንበር-መሬቶች (The Ethiopian Borderlands) በሚለው መጽሐፉ ዘርዘር አድርጎ ጽፏል። የቅርቡን ብንመለከት ደግሞ በተለይ ከ1813 ዓ. ም. ጀመሮ ግብጽ የኢትዮጵያ ባለቤትነቷን በጦርነት ለማረጋገጥ የዮሐንስን ኢትዮጵያ ከሱዳን ቀላቅላ ለመግዛት በአራት አቅጣጫዎች ወረራዎች ከፍታ ሳይሳካለት ወደ መጣችበት መመለሷን ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ “ዐፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሐፉ በሰፊው ተርኳል። በኃይለስላሴ እና በደርግ ዘመንም ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የጦር መሳሪያ እና ስልጠና በማቀነባበር፣ ገንዘብ በመለገስ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ አገሮችን በማስተባበር፣ የአማርኛ ስርጭት ሬዲዮ በመክፈት ድጋፍ ማድረጓን እናውቃለን። ህውሃት ከተጠቃሚዎቹ ተቃዋሚዎች ውስጥ አንዱ ነው። በአባይ ጉዳይ ከጥንት ጀምሮ ግብጽ ከስጋት ነፃ የሆነ እንቅልፍ የለታም። ዛሬም ሆነ ወደፊት ግብጽ የሰላሙን መንገድ ትታ የጸበኛነቱን መንገድ ከመረጠች እንቅልፍ አይኖራትም። ይኽን የግብጽ ጭነቀት እና ስጋት ህውሃት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ግንቦት 20 ቀን ጸብ ጫረ። ላብራራ።
የጥናቱን ውጤት ተቀበለችውም አልተቀበለችው ስለ አባይ ጉዳይ በጥናት ላይ የተሰማራው ኤክስፐርቶች ቡድን ሪፖርት እየጠበቀች ሳለች ድንገት ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም. ህውሃት የአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ሰበር ዜና ተሰራጨ። የኢትዮጵያ ሽብርተኛው ኢ.ት.ቭ. አስተጋባ። ዜናው ግብጽ ደረሰ። ከጥንት ጀምሮ የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ ተደናገጠች። አምባገነኑ ሞርሲ ከገበባት የውስጥ ችግር ለማምለጥ የህውሃትን ቁስቆሳ ተጠቀመ። አካራሪ የግብጽ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ጋበዞ ‘እኔ ሳልሞት ግብጽ አትጠማም’ አለ። ያጀቡት አክራሪዎችም ‘ግፋ’፣ ‘በርታ’፣ ‘አይዞህ ከጎንህ ነን’ አሉት። ይኽ ምክክራቸው ዜና ሆኖ አደባባይ ወጣ። ህውሃት ሁካታውን ያልጫረ መስሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግብጽ ልትወጋህ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመረ። የቀድሞ አባቶቻችን ድሎች ሳይቀሩ እየተጠቀሱ የቀረርቶ ድምጽ በአዲስ አበባ እየጎላ መጣ። አልባራዳይን የመሰሉት የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች የግብጽን መንግስት ወቀሱ። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎችም ቀረርቶው ገደብ ይበጅለት አሉ። የኢትዮ-ግብጽ የጦርነት ሁካታ አነሳሱ ይኽን ይመስል ነበር። ህውሃት የማያስፈልግ ጸብ ጭሯል።
ለመሆኑ ለምን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን ተቀየረ? ዜናውስ ለምን ግንቦት 20 ቀን አደባባይ ወጣ? ለዚኽ ጥያቄ አቶ በረከት ስሞዖን ሰኔ 7 ቀን ግድም 2005 የሰጠውን መግለጫ እንመልከት፥ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን የተቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ህውሃት ሰልጣን ከጨበጠበት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ሊያስተባብል ሞክሯል። ይኽ የበረከት ስሞዖን ማስተባበያ በሽብርተኛው ኢ.ቲ.ቭ. እና በኢሳት ተዘግቧል። የአቶ በረከትን መቀላመድ ወደ ጎን አድርገን እውነቱን ሃቁን እንመልከት። የአባይ ወንዝ ፍሳሽ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን እንዲቀየር ያስደረገው ህውሃት ነው። ዜናው ግብጽ እንዲደርስ ያደረገውም ህውሃት ነው። ግቡም ስልጣን ነው። ላብራራ!
1ኛ) የተለየ አሳቢ እና ከድኽነት ነፃ አውጪህ እኔ ህውሃት ነኝ የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ እንዲችል ሆን ብሎ የአባይ ፍሳሽ የተቀየረበትን ቀን ስልጣን ከጨበጠበት ግንቦት 20 ቀን ጋር አገጣጠመው። የዚኽ እርምጃ ፖለቲካዊ ግብ ህዝቡ እንዲያመልክበት እና ስልጣኑ እንዲጠናከር ነው። ግድብ መገንባት አይደለም ግቡ።
2ኛ) የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ለሆነባት ግብጽ የአባይ ፍሳሽ አቅጣጫ መቀየር ዜና የጦርነት ፖለቲካ ውስጥ እንደሚያስገባት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በምላሹ የኢትዮጵያን ህዝብ በአገር ወዳድነት ስሜት አሳውሮ በሚፈልገው የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስጓዝ አስልቶ ነበር። የዚኽም ፖለቲካ ስሌት ግቡ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ኃይሎች ለመምታት እና ስልጣኑን ለማጠናከር ነበር። በአገር ከሃዲነት እና በሽብርተኛነት ሽፋን። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ፈጥነው ስላጋለጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በአባይ ስሜት አሳውሮ የዴሞክራሲ ኃይሉን ለመምታት የሚያስችለው ጊዜ ሳያገኝ ቀረ። ከሸፈበት።
ህውሃት ከግድቡ ይልቅ ስልጣኑ እንደሚበልጥበት ለአንዲት ደቂቃ እንኳን መዘንጋት አያስፈልግም። ወደፊትም ሌሎች ጸቦች ሊጭር እና ከዚያ ግብጽ ልትወጋን ነው ይልሃል። የዴሞክራሲ ኃይሎች የነፃነት ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው በመቀጠል እራሳቸውን ከህውሃት ማጭበርበር እና ጥቃት መጠበቅ አለባቸው።
(girmamoges1@gmail.com)
በለው ! says
የአባይን ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ ማስቀየስ ከተያዘለት ዕቅድ ሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ ልክ ግንቦት ፳ቀን ዋለ!። ኢህአዴጋዊ ኢንጂነሪንግ…ዜናው ግብጽ እንዲደርስ ያደረገውም ህውሃት ልማታዊ መንግስት በድል ቀን ድል ለማብሠር የኢትዮጵያን ህዝብ በአገር ወዳድነት ስሜት አሳውሮ በሚፈልገው የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስጓዝ አስልቶ ነበር።…
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም “አብረን እንዋኛለን?ወይንስ አብረን እንሰምጣለን ? ወያኔ ከዕርዳታ ሰጭ ሀገራት የሚያመልጥበት፣በአሜኒስቲ ኢንተርናሽናል የማይቀወቀስበት፣በአበዳሪ ሀገሮች ተግፃፅ የማይደረስበት…ዘመን ተሻጋሪ.. ትውልድ አምካኝ …ሀገር አጥፊ የሚመለምልበት ታላቁ የገቢ ማንጭ መብራት ሸጦ ነዳጅ እየቀዳ የጦር ኅይሉን የሚያጠናክረበት የሙስና ፋውንዴሽን በዚህ ግድብ መሳካት ብቻ ነው ብሎ በቁርጠኝነት ትውልዱን ለማጭበርበር ታጥቋል ።
ዴያስፖራው: ቱል-ቱል ሲል
ቦንደኞች ፡ጡል -ጡል
አርቲስቱ :ብጉል- ቡጉል
ሟቹ :ዊን ዊን
ካድሬው :ቂን-ቂን
ካይሮ ፡ ፊን -ፊን
ብሔር ፡ ዝልል- ዝልል
ኢንቨስተር :ውጥር- ውጥር
የተገረምን :ጥርጥር- ጠርጠር
ወያኔ ፡ሰጥቶ- መቀበል
ያልገባን ፡ ዘራፍ – ዘራፍ
********ጦርነት በሌለበት ፡የወሬ ፈረስ ጫንን…በዝናብ አቧራ ላስነሳን..በተንገረበበ ቤት ጅብ ለጋበዝን…እናም ታዘብን!!?*****
“እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሠናል አለች አሉ…(ግድበ መቃወም)እና ከእንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ከናዳ፣ ቻይና፣ ከዓረብ፣ እኩል ቦንድ ገዝቼ የባለቤትነት ሠርተፍኬት ይሰጥኝ ማለት ትልቅ ልዩነነት አለው በለው። አራት ነጥብ። ሁለቱ ሀገራት በመን ተስማሙ አንዱ ልግደልህ ሲለው ቆይቶ ሌላው አልሞትም እገልሃለው ሲል በሳምንት ውስጥ ተስማሙ? “ገዳይ መግደሉን እገልሃለሁ ግን ድምፅ በሌለው መሳሪያ ነው ሲለው…ሟች ለመሞት እስማማለሁ ግን ድምፅ የሌለውን መሳሪያ የመምረጥ ሙሉ መብቴ በባለሙያ አስጠንቼ የማቅረብ መብቴ ይጠበቅልኝ ቢቻል መሳሪያውን ላቅርብ (ሰጥቶ መቀበል)ይሁን ሲል ተስማማ።!! እሰይ በዓለም ለየት ያለ ፈጣን ከዊን ዊን፣ ቂን ቂን፣ ከዚያማ እግር ላይ ድፍት!…አቤት አቀባበል ተምች በለው!
የዓባይ ጉዳይ እኛ ዜጎችም ያገባናል። ግልፅና ተጠያቂነት ይኑር ህዝብ የመጠየቅ፣ የማወቅ፣የማይሸራረፍ፣ የማይበረዝና የማይከለስ ሙሉ መብት አለው!!።
*************************************************************
የኢትዮዽያ መንግስት አቋም :
(1) የግድቡ ግንባታ እንደማይቆም፣
(2) ግድቡ ወደ ግብፅ የሚሄደው የውሃ መጠን እንደማይቀንስ (ይሄ እንኳ አቋም አይደለም ማብራርያ እንጂ)
(3) ኢትዮዽያ የድሮ የውሃ አጠቃቀም ውል እንደማትቀበልና የዓባይ ዉሃ ለኤለክትሪክ ሃይል ማመንጫ የመጠቀም መብት እንዳላት ወዘተ …።
(፬) ኢትዮዽያ ግን ጉዳዩ በሰለማዊ መንገድ ወይ በድርድር መፈታት እንዳለበት ትገልፃለች።
ግብፅ ጉዳዩ ለመፍታት ያስቀመጠቻቸው የድርድር ነጥቦች:
(፩) ድርድሩ እስኪካሄድና መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ የግድቡ ግንባታ ‘መቆም’ እንዳለበት፣
(፪) የግድቡ መጠን ከ74 ቢልዮን ኲቢክ ሜትር ወደ 14 ቢልዮን ኲቢክ ሜትር ዝቅ ማለት እንዳለበት (ይህንን ቅድምያ የሚሰጡት ነው)፣ከዛ በኋላም
(፫) የግድቡ ዲዛይን በግብፅ ባለሞያዎች መፈተሽ እንዳለበት … ወዘተ ያስቀምጣሉ።
(፬)ግብፅ (የውሃ ደህንነት) ለማስከበር ‘ማንኛውም ዓይነት መንገድ’ (የሃይል እርምጃ ወይ ጦርነት ጭምር መሆኑ ነው)
******************
(ሀ) “… ቀደም ብሎ በነበረው ስምምነት መሰረት አለም አቀፉ የባለሙያዎች ፓናል ባቀረባቸው የወደፊት ሀሳቦች ላይ ሱዳንን በመጨመር የሶስትዮሽ ምክክር ለመቀጠል ተስማምተዋል”
(ለ) “አለም አቀፍ የባለሙያዎች ፓናልን በተመለከተ ባስቀመጥነው አሰራር መሰረት የአጥኝ ቡድኑ ያወጣቸውን የወደፊት ሀሳቦች ለመተግበር ተስማምተዋል፡፡”
(ሐ) “‘በዓባይ ጉዳይ በቀላሉ መስማማት የሚቻለው ቢያንስ አንደኛው ወገን ብሄራዊ ጥቅሙ አሳልፎ ሲሰጥ ብቻ ነው’
**በግብፅ በዓባይ ጉዳይ ጥናት ያካሄዱና ብዙ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎችና ተቋማት መዓት ናቸው። በኢትዮዽያ አንድም ተቋም የለም። በግብፅ ብዙ ባለሙያዎች የፖለቲከኞች አማካሪዎች ናቸው። የኢትዮዽያ መንግስት ባለሙያዎች አያስተናግድም። በግብፅ ማንኛውም ፖሊሲ ጥናት መሰረት ያድረገ ነው። በኢትዮዽያ ሁሉም ነገር በደመ ነፍስ ነው።
አሁም ሁለቱም ሀገሮች የተስማሙበት የቴክኒክና የፖለቲካ ድርድር ለግብፅ ትልቅ ድል ነው።አሁን የኢትዮዽያ መንግስት ማድረግ ያለበት ሁሉንም ኢትዮዽያውያን ባለሙያዎች እንዲሳተፉ መጋበዝ፣ ወቅታዊ መረጃዎች በግዜውና በአግባቡ ለህዝብ መስጠት፣ ግድቡ ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ብቻ አለማዋል ፤ የሀገር ጉዳይ ነውና የሁሉም ዜጎች ደህንነት ያለ አድልዎ ይጠብቅ፤ ሀገር የሚጠብቁና የሚገነቡ ዜጎች ናቸውና ፍትህም እንደተጠበቀ ሆኖ ያለ ዜጎች ደህንነትና ኅብርት እንኳን ግድብ ሀገርም አይኖርም !! ። በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ
(“የኢትዮጵያ አቋምና የአባይ ፖለቲካ” የተሰኛውን ጽሑፍ ያቀረቡትን ግለሰብ አደንቃለሁ ከምስጋና ጋር!)