ዛሬ ጊዜ መቼም ሳጥን የሚወዱ ዓይነታቸው ብዙ ነው።
አንድ ዓይነት ሁሉንም የሚያደርጋቸው ግን አንድ ጉዳይ አለ።
ሳጥን ውስጥ መቅረት ስለሚፈልጉ፣ ሁሉም ከኔ ወዲያ ባዮች መሆናቸው ነው።
እስቲ አማርኛችንም ወደ ሳጥን (1 ከመላኩ በፊት፣
የለም እንዳውም እንዳይላክ ስንል እንናገርበት፥
*
አንድ ዓይነት ሁሉንም የሚያደርጋቸው ግን አንድ ጉዳይ አለ።
ሳጥን ውስጥ መቅረት ስለሚፈልጉ፣ ሁሉም ከኔ ወዲያ ባዮች መሆናቸው ነው።
እስቲ አማርኛችንም ወደ ሳጥን (1 ከመላኩ በፊት፣
የለም እንዳውም እንዳይላክ ስንል እንናገርበት፥
*
ከኔ ወዲያ
ነጋ ጠባ እኔ ማለት
ትልቅ ምንጩ ፍርሃት
ሆኖ እኮ ነው ብቸኝነት፤
የሚ-ኖረው ለጥፋት፣ በጥፋት፤
በድክመት፣ ያለምነት፤
ላይቀር ሞት።
ከኔ ወዲያ ማ-ይሙት
እየማለ ሲገዘት
ምኑን አወቆ ስለ መብት፤
ግማሽ ጽዋው የሚ-ሞላው
መች ባወቀው ይኸኛው፣
ለመሆኑ በዛ ማዶው
በ-ዚያ ሌ-ላው።
መች አ-ርቆ አሰበው፣
ከኔ ባዩ የጎደለው
ግማሽ ጎኑ አምላኩ ነው፤
ባምባው ብቻ የማይገነው፤
ከኔ ወዲያ የማ-ይለው፣
በሁሉም ቤት የሚ-ሆነው፤
ለ ዝንተ ዓለም የሚዘልቀው።
*
(1) ባገራችን የባህልና ታሪክ ቅርስ የሆኑትን ሁሉ ለማፈራረስ የመጣብንን የባዕድ ሥልጣኔ አባዜ ለማመልከት ነው። (ፎቶ: በጸሐፊው የተላከ)
Leave a Reply