• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ

March 29, 2014 04:54 am by Editor Leave a Comment

ከ1500 በላይ በሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚተዳደር የሚታወቀው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዲፕሎማቱ ቁጥጠር ስር መዋሉን የሚገልጹ ምንጮች ማርች 28 2014 በኤምባሲው ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ተላልፎላቸው የነበሩ ወላጆች ባለመገኝታቸው የስብሰባው አዳራሽ ባዶ ሁኖ መዋሉን አክለው ገልጸዋል።

ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደነበር የሚነገርለትን ት/ቤት ኤምባሲው ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት ከግል ጥቀም የመነጨ መሆኑንን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ት/ቤቱን ከኮሚኒቲው በመነጠል ከወላጆች በሚመረጥ የቦርድ አስተዳደር ይመራል በሚል ሽፋን ላለፉት 5 አመታት በት/ቤቱ ጥሬ ገዝንዘብ ላይ ግልጽ የሆነ ምዝበራ መፈጸሙን ይናገራሉ። ይህን አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዲፕሎማቱ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል እንደሌለ የሚናገሩ ወገኖች ከዛሬ 7 ወር በፊት ለይስሙላ ህብረተሰቡ በቦርድ አባልነት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ማስታወቂያ አውጥተን የሚቀርብ ሰው አጣን ለማለት የመወዳደሪያውን መመዘኛ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ከፍ በማድረግ ማንኛውም ወላጅ በቀላሉ ማቀረብ የማይችላችውን ተጨማሪ ደብዳቤዎች እንዲያቀርብ የሚጠይቅ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ወላጆች ት/ቤታቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ መደረጋቸውን ይገልጻሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ወላጆች ባላቸው አቀም እና የትምህርት ደረጃ አቋቁመው ለዘመናት ያለማንም ድጋፍ እና ረዳት በማስተዳደር ለዚህ ያበቁትን የልጆቻቸውን ዕውቀት መገብያ ማዕከል ኤምባሲው ለመንጠቅ በሪያድ የዲያስፖራው ሃላፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ተመስገን ኡመርን በጓሮ በር አሾልኮ በመስገባት ቀደም ብለው ያዘጋጇቸውን ታማኝ አገልጋይ የቦርድ አባላት ስልጣን ካፀደቁ በሃላ ዛሬ ወላጆችን ለማደናገር በኤምባሲው ማህተም በተደገፈ ደብዳቤ ስብሰባ መጥራታቸው የዲፕሎማቱን አላውቂ ሳሚነት በግልጽ ያሳይል ተብሏል።

ዲፕሎማቱ በኤምባሲ ሽፋን ህገወጥ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩ ወገኖች 1500 በላይ የሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚቆረቆሩለት የሚነገርለትን ት/ቤት ቁጥራቸው ከ 50 የማይበልጡ የት/ቤቱ ጉዳይ የማይመለክታቸው ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አዳራሽ በማስገባት «አይጥ በበላው ዳዎ እንዲሉ» ምንም የማያውቁ ወላጆችን የ 1.7 ሚሊዮን ሪያል ባለእዳ የሚያደርግ ሪፖርት በዲይስፖራው ሃላፊ አማካኝነት በማቅረብ ዲፕሎማቱ የመረጣቸውን ህገ ወጥ የቦርድ አማራር አባላት ህጋዊ ለማድረግ ከወላጆች ጀርባ ዛሬ የፈጸሙት ደባ በህግ ሊያስጠይቃቸው የሚገባ ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ስብሰባው ላይ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ዑመርን ለማነጋገር ያደርኩት ሙከራ አልተሳካም።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule