ዶ/ር አክሊሉ ሀብቴ አቋማቸውን በየጊዜው በመቀያየር፡ የዋሽንገትን ዲሲ ቅድስት ማርያምን ወደ አቡነ ማትያስ ጉያ ለመክተት ከፈለጉት ሰዎች ጋራ መስማማታቸው ሰውን ግራ አጋባው።
በትምህርት፡ በሽምግልና፤ የዩንቨርሲቲ ፕሬዝደንት ሆነውም፤ የምሁራንን ጭንቅላት በመምራት እና ፤ ጥራት ባላቸው መምህራን በሚቀርብላቸው የእውቀት ትምህርት እንደ ሰንጋ ፈረስ የሚቁነጠነጠውን የተማሪ አዕምሮ በመግራት ሰፊ ልምድ አላቸው የሚባሉት ዶክተር አክሊሉ በዚህች ጦማር ከዘረዘርኳቸው ሰዎች ጋራ ራሳቸውን ደምረው ራሳቸውን ማስመዘናቸው የራሳቸውን ሁለንተናነት በማዋረድ ተመልካቹን ግራ እያገቡ ነው።
ይልቁንም ምሳሌነታቸው ለሚዛንነት ከሚጠቀስላቸው በኢትዮጵያ ታሪክ እና በትውልድ ጭንቅላት ላይ እንደ ወርቅ አእማድ ሲፈልቁ ከሚኖርት አባቶቻችን ጋራ መደመር በተገባቸው ነበር። የወርቅ አእማድ ያልኳቸው አባቶቻችን፤ ነፍሳቸውን ይማርን ለዶክተር አክሊሉ እድሜ ቅርብ የሆኑት ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው ከብዙዎቹ ጥቂቶች ናቸው። እነዚህም፦ ክቡር አቶ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፤ በጅሮንድ ተክለ ሐዋርያትና፤ አምባ አሳደር ዘውዴ ረታ ናቸው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡ የመልስ ጽሁፍ ባድራሻችን መላክ ይቻላል፡፡
Leave a Reply