• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና

February 10, 2014 04:11 am by Editor 1 Comment

ባሳለፍነው ሃሙስ የወላጅ መምህራን ስብሰባ ላይ ስለጅዳው አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤት አስተዳደር ፍትሃዊነት የቅጥር ሂደት እና በትምህርት ጥራቱ ዙሪያ ላይ አንድ በኢኮኖሚክስ ትምህት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ ወጣት የሰላ ሂስ አቀረበ። በቀረበው የወጣቱ የዩኒቨርስቲ መምህር ስደተኛ ስራ ፈላጊ አስተያየት ድጋፍና ተቃውሞ ቤቱን በየተራ ናጠው።  በትምህርት ጥራት አለመኖር የሚስማማው ወላጅ በጭብጨባ ድጋፉን ሲገልጽ የትምህርት ጥራቱን አንድ ከኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የ12 ኛ ክፍል ተማሪ ጋር በእንግሊዝኛ ትምህርት እውቀታቸው የኤርትራ ኢምባሲ የ7ኛ ክፍል ተማሪ እንደሚልቅ በንጽጽር ማቅረቡ የተከፉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖርቲ አባላትና ደጋፊዎች ውግዘት አስከተለበት። አንዲት የወላጅ መምህራን ህብረቱ አባል ለትምህርት ጥራቱ ንጽጽር “ኤርትራ” የምትባለውን ሃገር ከአፉ ያወጣውን ወጣት ምሁር በአደባባይ ወጥተው ወረፉት። የወላጆችና መምህራን በሆነው ስብሰባ ለምን ይሳተፋል ሲሉም ከስብሰባው እንዲውጣ ሲሉ በድፍረት እስከመናገር ደርሰው ብዙሃን ተሰብሳቢውን አሳፈሩ::

ግማሽ ሌሊት በዘለቀው ስብሰባ የሚጨበጥ መፍትሔ ሳይያዝ ተበተነ።  ስብሰባው አብቅቶ ወደ የቤታችን ለመሔድ ከግቢው እንደወጣን ከአዳራሹና ከኮሚኒቲው ግቢ ውጭ “የተከበሩት” የድርጅት ሰዎች ወጣቱን ከበው ሲያዋክቡት ደረስኩ። ምክንያቱን መጠየቅ አላስፈለገኝምና ግርግሩን  በአርምሞ መታዘብ ጀመርኩ። ወጣቱን ከመካከል አድርገው ሲያዋክቡት ቁልጭ ቁልጭ እያለ ለሚሰነዘርበት ትችት መልስ ለመስጠት ይሞክራል። እነሱ ይዝታሉ፣ ያንቋሽሹታል። “የትምህርት ንጽጽሩን በተጨባጭ ካየው እውነታ ጋር  የመናገር ነውርነቱ ምኑ ላይ ነው? ” የሚሉት በአንጻሩ የባለጊዜዎችን ቁጣ በመቃወም በእሰጣ ገባው መካከል ለወጣቱ ድጋፋቸውን መግለጽ ሲጀምሩ ክርክሩ ሜዳ ላይ ለአፍታም ቢሆን  ተፋፋመ።

አፍ የፈታበት ትግርኛ ቋንቋ አፉን ያዝ እያደረገው መልስ የሚሰጠውን ወጣት ምሁርን በራስ መተማመን ስመለከት የመቀሌው አብርሃ ደስታ ትዝ አለኝ። ልዩነቱ አብርሃ መቀሌ ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ስርአት አልበኝነትን የሚቃወም ሆኖ ሳለ ይህኛው ወጣት የሚሞግተው ፖለቲከኛ ሆኖ ስለፖለቲካና ኢፍትሃዊ አስተዳደር  እያወራ አለመሆኑ ነው። ወጣቱ በ3000 ታዳጊዎች የትምህርት ማዕከል ላይ የሚታየውን የአስተዳደር ኢፍትሃዊነትና የትምህርት ጥራት አለመኖር በድፍረት በመናገሩ በወንዙ ልጆች ዘንድ “አይንህን ላፈር” አስብሎ በእርጉም አስፈርጆታል።  ግርግሩ በረድ ሲል ወጣቱ ወደ ቤቱ ለመሄድ ከአንድ ወዳጀ ጋር የሚያደርሳቸው ሲያፈላልጉ አየኋቸውና እግረ መንገዴን ላደርሳቸው ጠራኋቸው። ወጣቱ ኢኮኖሚስትና “አላጠፋም አትንኩት!” ሲል ይሞግትለት የነበረው ወዳጀ ከእኔው ጋር ተሳፍረው መጓዝ ጀመርን … እናም ከሰላምታ በኋላ እኔ እንደለመደብኝ መጠየቅ እሱም መመለስ ያዘ …

ገና ልጅ እግር ነው። እድሜው ከሃያዎቹ አያልፍም። በ1990ዎቹ ከትግራይ ክልል ተነስቶ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ዘመነኛውን የኢኮኖሚክስ አስተዳደር ትምህርት ለስድስት አመታት ተከታትሎ በማዕረግ ተመርቋል። ከ2000 ዓም ወዲህ በትምህርቱ የላቀ ውጤት በማምጣቱም እዚያው አዳማ ለስድስት አመታት ዩኒቨርሲቲ አስተምሯል። በሃገር ቤት የኑሮ ውድነት ጣራ ነክቶ አልመቸህ ቢለው ባንድ ክፉ ቀን ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ወደ ውጭ ሃገር ሄደው በስደት የተሻለ ገቢ አግኝተው በሚሰሩት ሁኔታ ዙሪያ ተመካከረ። “በሳውዲ በኩል ወደ ሌላ አውሮፖ ሃገር መውጣት ይቻላል!” የሚባል መረጃ ለእርሱና ለጓደኞቹ ስለደረሳቸው በአሳር በመከራ ያጠራቀሟትን ጥሪት በመሰባሰብ ቪዛ ገዝተው ከአመት በፊት ወደ ሳውዲ ጅዳ ከተፍ አሉ።

… ሳውዲ አረቢያ ግን እነሱ እንዳሰቧት ሆናም ሆነ ወደ አውሮፖ የሚደረገው ስደት የቀለለ አለመሆኑን የአረቦቹን ኑሮ በተቀላቀሉ ቅጽበት ማገናዘብ ቻሉ። በቃ እሱና ጓደኞቹ ሳውዲን እንዳሰቡት አላገኟትምና ብዙ ሳይቆዩ በጅዳ የተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ስራ ፍለጋ ጀመሩ … በሰው በሰው በጅዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት “የመምህራን እጥረት አለ!” ሲባል ሰምተው ከአንድ ጓደኛው ጋር ወደ ትምህርት ቤቱ አስተዳደር በመሄድ የትምህርት መረጃቸውን አቀረቡ። ምንም እንኳን ትምህር ቤቱ ካላቸው ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ አንጻር ባይመጥናቸውም እንደ ዜጋ ዝቅ ብለው ለመስራት እና ለዚህ ትውልድ  እውቀታቸውን ለማካፈል እድል አገኘን ብለው ያቀረቡት አቤቱታ ግን በትምህርት ቤቱ አስተዳደር በኩል ለውድድር ቀርበው ግልጋሎት መስጠት የሚችሉበት እድል የተነፈጋቸው መሆኑን ወጣቱ አጫወተኝ! ይህ ወጣት ምሁር አክሎ እንዳጫወተኝ ከሁሉም የሚያስገርመው የ11 ኛ እና የ12 ኛ ተማሪዎችን በኢኮኖሚክስ ያልተመረቀ መምህር ታዳጊዎቹን በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት እንዴት በሙያው የተካንን፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዩኒቨርሲቲ የማስተማር ብቃት ያለው ዜጋ ዝቅ ብየ ላስተምር ሲል እንዴት እድሉን ይነፈጋል? ሲል የሚያጠይቀው ወጣት የትምህርት መረጃዎችን ተቀብሎ ማወዳደር መጠየቅና ተገቢውን ለታዳጊዎች የሚጠቅም እርምጃ መውሰድ ሲገባ “ስትፈለጉ እንጠራችኋል!” በሚል መልስ መሸንገላቸውን በስሜት ገልጾልኛል!

“በዜጎች ላይ አንቀልድ፣ በነገ የሃገሪቱ ተስፋዎች ልንቀልድባቸው አይገባም” ሲል ስሜትን በሚነካ መንገድ የገለጸልኝ ይህ ወንድም በአሁኑ ሰአት የተለያዩ ተማሪዎችን በየቤታቸው እየሄደ በማስተማር ትምህርት ቤቱ ሊከፍለው ከሚችለው ገንዘብ በላይ ገቢ እንዳለው የገለጸልኝ ሲሆን ያም ሆኑ ትምህርት ቤቱ ለመደገፍ ይቻል ዘንድ ባለው ትርፍ ጊዜ መምህራን እንዴት ራሳቸውን ብቁ አድርገው ማስተማር እንዳለባቸው የተለያዩ ትምህርት ማጎልመሻ ስልጠናዎችን በነጻ ለመስጠት ከጓደኞቹ ጋር ጥያቄ ቢያቀርብም ትምህርት ቤቱም ሆነ ባለቤት ተብየው ለጅዳ ኮሚኒቲ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት እንዳላገኘ በቁጭት አጫውቶኛል። እስኪ እሰበው ” ዜጎችን እንደግፍ ስንል ለምን እድሉ አይሰጠንም?” በማለት ያጠይቃል!  ወጣቱ እውነት አለው!

3000 ታዳጊዎች የምናስተምርበት ትምህርት ቤት ባልረባባ ምክንያት በአደጋ ላይ እንዳለ በስብሰባው በግልጽ ተመልክቷል።  የመምህራንን እጥረትን መሰረት አደረገ የሚባለው የትምህርት ጥራት እያደረ ማሽቆልቆል በስብሰባው በአደባባይ በወላጅ እና መምህራን ህብረቱ ፣ በስብሰባው ተሳታፊ ወላጆች እና በመምህራን በግልጽ ተነግሮናል። ይህ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ ለትምህርት ጥራቱ ማሽቆልቆል የመምህራን እጥረት ምክንያት በሆነበት የትምህርት ማዕከል የላቀ እውቀት ያላቸው አቤቱታ ወገኖች አቤቱታ ለምን ተፈነገለ?  የ11ኛ እና የ12 ኛ ክፍል ወሳኝ ክፍሎች አዋቂ ሳይጠፋ እውቀቱ በሌላቸው መምህራን እንዲማሩ ማድረግ ለምን አስፈለገ?  በዚህ መሰል አስተዳደር የሚመራው ትምህርት ቤት የትምህርተ ጥራቱን አስጠብቆ ልጆቻችን ወደ ተሻለ የእውቀት ጎዳና ያደርሳቸዋል ብሎ ማሰብስ እንዴት ይቻላል?  ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ያለባቸው ወጣቱን በመረጃ በአደባባይ መሞገት ያልቻሉት ወገኖች እና አጫፋሪዎቻቸው ቢሆኑ ደስ ይለኛል። ኤርትራ የምትለው ሃገር ስለተነሳች ያንገበገባቸው ወገኖች ንጽጽሩ ከሱዳን አለያም ከፖኪስታን ተማሪዎች ጋር ቢሆን እንዲህ ያንገበግባቸው ነበርን?  ጉዳዩን በቅንነት ማሰብ ከቻሉ ኤርትራን የምትለውን ቃል ትተው የትምህርት ጥራት የለም ለሚለው የወጣቱና የብዙሃን ወላጅ አስተያየት ለምን በአደባባይ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም? ለነገሩ ይህንን ለማድረግ ሞራል የላቸውምና አልፈርድባቸውም። እኔም ቢያንስ ከዚህ ተነስቸ ይህንን ደረቅ እውነት ለመገምገም የተለየ ክህሎት ይጠይቃል ብየ ስለማላምን  በማለዳ ወጌ ተነፈስኩት  …

ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. sawa says

    February 15, 2014 08:47 am at 8:47 am

    The young guy might have seen them speaking fluent English in sawa death camp. Of course those who opposed him were correct. He is spy of shabia or weyane

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule