
ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሬድዮ ጋዜጠኛ በነበረበት ጊዜ ወደ ጋሞ ጎፋ ለስራ ሲሄድ፣ በድንገት ካጋጠመችው የሐመር ቆንጆ ጋር የተነሳው ፎቶ ነው።
ምልልሱን ያንብቡ።
በደመቀ ፀሐይ
ከወለላዬ
በቀን አጋማሽ ላይ – በደመቀ ፀሐይ
አካሏ ተጋልጦ – በግማሽ የሚታይ፣
የተዋበች ሐመር – መንገድ ላይ ብትወጣ
አዬ ጋዜጠኛው – የመጣበት ጣጣ፣
እሷ ግን እቀፊው – ሳሚው ሳሚው ብሏት
ጎኑ ብትጠጋው – አሹላ ያንን ጡት፣
የሱም አጉል ፍራት – የሷም አጉል ድፍረት
በደመቀ ፀሐይ
———-
ሰውም ይፈራል ወይ?
ከአበራ ለማ
ጌታ ወለላዬ – ምነዋ አልፈራ
መትረየስ ደግና – ፊቴ ተገትራ፤
ደ’ሞኮ አወጣጧ – ከጫካው ከዱሩ
መፍራት ይነሰኝ ወይ – እንግዳው ላገሩ፤
አያድርስ እንጂ ነው – touch down ብትለኝ
በዚህ በጠራራ – መጋኛስ ቢመታኝ፤
———-
ከወለላዬ
ዘምተህ የተመለስክ – በናቅፋ ተራራ
መሳሪያ የጨበክ – ከጀግኖቹ ጋራ፣
ባዶዋን የመጣች – ትንሽ ልጅ ስትፈራ፣
ታዝቤህ ነበረ – ጋዜጠኛ አበራ።
አሁን ግን ሳስበው – ነገሩን በትኩረት
ጠላትን ሰብስቦ – ማርኮ ለማስቀረት፣
ወታደር መልምሎ – ጦር ሜዳ ከማዝመት
ሳትሻል አትቀርም – አንዷ የሀመር ሴት፣
———-
ያልተነካ …
ከአበራ ለማ
አወይ አለመያዝ – አለመነካት
ጡር ነው ወለላዬ – በነፍሴስ መምጣት፤
ጥግብ ፍርጥም ያለች – ደንደሮ ወጣት
ታስጨፍረኝ ነበር – ኢቫንጋዲ ስልት፤
ናቅፋ ቢበረታም – ይሄ ጋዜጠኛ
ከመሆን አልዳነም – የሐመር ምርኮኛ!!!
—— ||||||||||| ——
“ታመመልሽ ደነገጠልሽ ከቶ በዐይን ብቻ ሳይነካው አካልሽ
ቀረጥ የሌለበት ወረት ያልዳሰሰው ደህና አንቴና ሰቅለሽ
መሳሪያ ሳይዙ መማረኪያ ማን አስታጠቀሽ?
አንቺ የሐመር ቆንጆ እንደምንድነሽ?
ፍራቻው በርትቶ ብርክ ቢይዘው
ዛፍ የለ አካባቢው መቋሚያ የሚሆነው
እጁን ጀርባዋ ላይ ደገፍ ቢያደርገው
ንዝርት በፈገግታ ፀሀይ መብረቅ አለው
ፎቶም ይናገራል ፅፈውም አስታውሰው
የሐመሯ ወለላዬ ውበትሽ ማራኪ አበራ ለማነው!?
በለው!
THANK YOU BELEW FOR YOUR POETIC EXPRESSION!…. I LIKED YOUR REACTION.
ፈረሱም ሜዳውም ይሐው ከተባለ
አስተያየት መስጠት ልብ እንደማለለ
ተፈቅዶ ከሆነ ትዝብት በደፈናው
የ ቦምቡ ማጠፊያ መዘርጊያውም ይሕው»
የሐመርዋን ቆንጆ መሐል አስገብቶ
ሰጣ ገባ መግባት ቃላተን አስማምቶ
የጥንት ማስታወሻ እውጥቶ በፎቶ
ትዛዝ ከተስጠ ከተባለ ጎልጉል
ታሪክ መቼ ጠፍቶ ሁሌም የሚያማልል
ስለዚሕ ይቀጠል ፈረሱና ጋሪ
ጎልጉል እንደሜዳ በተዘዋዋሪ»
ወለላዬ ያቅርብ ከማሕደር ፎቶ
አበራም ይመልስ ብድሩን አሳክቶ
ጌታው አቶ ቦንቡ – አድፍጠው አድፍጠው
ያቀረቡት ሐሳብ – ፍላጎቴን ሳበው
በዚህ አቀራረብ – ቃላት አፈሳሰስ
ምንድነው ችግሩ – ቢሳተፉ እርስዎስ
ታሪክ ገላልጨ – ማህደር ፈትሼ
በቅርቡ እመጣለሁ – ዳግም ተመልሼ
ስለዚህ ለመልሱ – ቀድመው ይሰናዱ
ለግጥም ጨዋታ – ታጭተዋል እንዳንዱ
የላይኛው ወደ ስድ ንባብነት ስለተቀየረ ነው የደገምኩት በለው ግሩም ቅኔ አዘል ግጥም ጽፈዋል በተለይ የመጨረሻው ማሰሪያዎ ሁላችንንም የሚአጣቅስ በመሆኑ ወስጥ አወቅ ሳይሆኑ አይቀሩም ብዬ ገመትኩ ከአክብሮት ምስጋና ጋር
******************
ኢትዮጵያዊነት ፅድቅ ክብር ድንቅ ነው
ሐመርን ያላየ ሀመር ነዳሁ ያለው እንደ አበራ ለማ ነክቶ ይሞክረው !
ውስጥ አወቅ ባልሆንም ዓይን ምሥክር ነው
ወለላ የመሰለች የሚያበራ እያየሁ እንደምን ልለፈው? ከንፈሮቿን ገጥማ አንቴና ብትወጥር
ምንይልክ ተደንቆ በለው! ቢል ቦንብ አድፍጦ ቢወረውር
ወለላዋ ለማ አበራም ስንገጥም እየው ሲያምር!!
******************
ከሰላምታ ጋር!! በቸር ይግጠመን በለው!