• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ!

February 20, 2014 07:11 am by Editor 2 Comments

ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የተፈጠረው ቅራኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩት ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒቲው ሊቀመንበር እና በማህበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21 /2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል፡፤

በቅርቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የጠራውን የአባላት ሰብሰባ ተከትሎ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ደጋፊዎቻቸውን ወደ አዳራሹ በማስገባት ከማህበሩ ሊቀመንበርነቴ የተነሳሁት ያለአግባብ ነው በሚል በኮሚኒቲው ሊቀመንበር ላይ ቡጢ በመሰንዘራቸው ተከትሎ በተቀሰቀሰው መለስተኛ ግጭት ስብሰባው ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሺክ ሙስጠፋ ሁሴን የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21-2014 የኮሚኒቲው ስራ አመራር በጠራው ጠቅላላ የአባላት ጉባኤ ላይ ሁከት ለመፍጠር በብሄር ላይ የተመሰረተ ቅስቀሳዎችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች ከሪያድ አረጋግጠዋል።

ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ፌብሩዋሪ 14-2014 ምሸት አያሌ ደጋፊዎቻቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኘ አንድ ቢሮ ውስጥ በማን አለብኝነት ሰብሰብው ሲመክሩ መታየታቸውን የሚገልጹት ምንጮች ሼኩ ለግብረ አበሮቻቸው አማራ ስልጣናችን ስለነጠቀን ማንነታችንን ለማስከበር እና ስልጣናችንን ለማስመለስ እኛ ኦሮምዎች እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ፡አይገባንም ብለው በመናገር የጥቂት መስል ደጋፊዎቻቸውን በተሳሳተ መንገድ ቀልብ በመሳብ የኮሚኒቲውን አባላት በዘር በሃይማኖት ከፋፍሎ ለማጋጨት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አጋልጠዋል። የሼክ ሙስጠፋን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ብሄርተኝነትን በስፋት በማራገብ ላይ የተሰማሩት ቅጥረኞች በህገ ወጥ የሃዋላ ንግድ ላይ የተሰማሩ እና ቀደም ሲል በእህቶቻችን ህይወት ዶላር ሲሰብሰቡ የከረሙ የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ደላላዎቻቸው መሆናቸውን የሚናገሩ ወገኖች ግለሰቦቹ የትኛውንም ብሄር አሊያም የሃይማኖት ተቋም እንደማይወክሉ ገለጸው ህብረተሰቡ ከእንደነዚህ አይነት ሴጣናዊ መርህ ካነገቡ መሰሪዎች እራሱን በመከላከል በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል እንደወትሮው ሁሉ በአንድነት የኮሚኒቲውን ንብረት ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባው መክረዋል።

የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን በስማቸው በከፈቱት ሁለት ሰራተኛ እና አስሪ አገናኝ ኤጄንሲ ያስመጡዋቸው እህቶቻችን በህክምና እጦት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን የሚያስታውሱ ታዛቢዎች ሼኩ በሳውዲ አረቢያ የደህነት ሃይሎች ለእስር በመዳረጋቸውን ተከትሎ በኮሚኒቲው መተዳዳሪያ ህገ ደንብ መስረት የሊቀመንበሩን ቦታ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ያሲን ተረክበው መሸፈናቸው ሊያስመስግናቸው እንጂ ቡጢ ሊያሰነዘርባቸው እንደማይገባ የሚናገሩ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሼኩ ከወህኒ ከወጡ በሃላ ጤንነት እንደማይሰማቸው በመጥቀስ የኮሚኒቲ ሊቀመንበርነቴን ለምን በአማራ ብሄር ተነጠኩ በሚል ዘረኝነት የተጠቀሱትን ደጋፊዎቻቸውን በመስብሰብ በአባላቱ መሃከል የብሄር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመጫር እያሰሙ ያለው ጩሀት አብነት መሆኑንን ይገልጻሉ።

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር በስሩ ከሁለት ሺህ በላይ ህጻናትን ተቀብሎ የሚያስተናገድ አንድ አለም አቀፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባለቤት እንደነበር የሚገልጹ አንጋፋ የማህበሩ አባላት ት/ቤቱን ከኮሚቲው በመነጠል ኤምባሲው በራሱ ስልጣን ባስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ት/ቤቱን እንዳሻው እየዘወረ ላለፉት 4 አመታት ገቢ እና ወጪው ሳይለይ እስካሁንም የጥቂቶች ኪስ ማደለቢያ ሆኖ መቀረቱን ይናገራሉ። ዛሬ በኮሚኒቲው ስራ አመራር እና በሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች መሃከል የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ ከጥቅም ጋር የተቆራኘ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች በአሁኑ ግዜ ብቸኛ የማህበሩ ንብረት የሆነው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል ከት/ቤቱ ባላነሰ ሁኔታ ዘረፋ እየተፈጸመበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፤

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ከ8 መቶ የሚበልጡ አባላት እንዳሉት የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ማህበሩ የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21 2014 ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ መወሰኑን በመግለጽ በወቅቱ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ኤምባሲው እና የሚመለከታቸው አካላቶች የዜጎቻችን ህይወት ለመታደግ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባቸው አክለው ጠቁመዋል።

Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል የላኩት

ማሳሰቢያ ከዚህ ላይ የተያያዘው የቪድዮ ሰዕላዊ መግለጫ ቀደም ብሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ውስጥ ጥቂቶች ብዙሃኑን በዘር በሃይማኖት ሲከፋፍሉት የሚያሳይ ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics

Reader Interactions

Comments

  1. Kasim says

    February 21, 2014 12:06 am at 12:06 am

    Yihe tera werena yelele propaganda izaw bikoy Ethiopian Hagere, nebiyu sirak, golgul ina zehabesha Amarawun ina lelawun bihereseb lemanakes yemitnezutin bere welede wushet izaw abkut ye riyad hizb indehone betam astewayina bilih inji benante tera yetilacha polotica bota yemisasat mesloeachihu atilfu. Yemin dem mefases new yemitkazut.
    Inkuwanis dem mefases yikirina haylekal menegagerim aynorim Zim bilachihu yeken kijet atikaju. Yeriyad hizb indenante chelemtegna ina yezer polotica altetenawetewum. Yetekeberewun Amara atasedibu

    Reply
  2. ዘለአለም ወንድሙ says

    February 21, 2014 01:51 pm at 1:51 pm

    ህዝብን እና የመረጃ መረቦቻችን ለማደናገር በአቶ ቃሲም ሰም አስተያየት የሰጡት ግለሰብ እንኳን የሪያድን ህዝብ እርሳቸውን መወከል የማይችሉ ጭብጥ ለማይሞላ ሆዳቸው አስሪ እና ሰራተኛ ኢጀንሲ ከፍተው በእቶቻችን ህይወት ዶላር ሲሰበስቡ የነብር ወንጀለኛ ሰው በመሆናቸው ብቻ እዚህ ገጽ ላይ ያሻቸውን ያህል ቢመጻደቁም መድረኩ ላይ የወንጀለኞች አስተያየት ለምን ተስተናገደ ብዬ እናንተን «https://www.goolgule.com/ » ከመውቀስ ይልቅ ነጻ ሚዲያ መሆናቸሁን በተጨባጭ በማረጋገጣችሁ በዚህ አጋጣሚ ደግሜ ደጋግሜ ለናንተ ያለኝን አድናቆት ስገልጽ እጅግ በጣም ደስታ ይሰማኛል ። ይህ በዚህ እንዳለ ከዚህ በላይ የተቀመጠው አስተያየት የኮሚኒቲው ሊቀመንበራችን አቶ ቃሲም ያሲንን በፍጹም የማይወከል መሆኑንን በዚህ አጋጣሚ ማረጋገጥ እወዳለሁ። «ሊበላኝ ያሰበ አሞራ ያንዣብብኛል እንዲሉ »አስተያየት ሰጪው ምን ያህል የወርዱ ለመሆናቸው የግለስብ ስም እየጠቀሱ ከሰጡት ነወረኛ አስተሳሰባቸው በላይ አብነት ማቅረብ አይገድም። አዎ እነዚህ ነወረኞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ህዝብን በማደናገር ስራ ላይ መጠመዳቸው ዛሬ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ሊፍጽሙ ያሰቡት የእርስ በእርስ ግጨት አንዱ አካል በመሆኑ እኛ በሪያድ የምኖር ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴዎቻቸውን እግር በእግር እየተከታተልን መሆኑንን የኛን ጉዳይ በቀርብ እና በርቀት ለሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ወግኖቻችን ማብሰር እንወዳለን ። በተለይ ይህ ነወረኛ ተግባራቸው በሶሻል ሚዲያ እርቃኑን መቅረቱ ያስደነገጠው በሼክ ሙስጠፋ ሁሴን የሚመራው ቡድን በአሁኑ ሰአት ሺኩ የተናገሩትን ዘረኛ አስተሳሰብ ማነው ለሚዲያ የሰጠው በሚል እርስ በእርስ በመተራመስ ላይ ናቸው። አዎ የኢትዮጵያን ህዝብ እግዝብሄር « አላህ » ይጠብቀዋል። የቀርብ እና የሩቅ ጠላቶቻችን የቱንም ያህል ሰላማችንን ሊያደፈርሱ ህብረታችንን http://www.youtube.com/attribution_link?a=3gohMzNdeoQ&u=%2Fwatch%3Fv%3D2qpaZQa_CVc%26feature%3Dshare ሊንዱ ቢያሴሩም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ ለዘላለም ይኖራል። በመጨረሻ ስልጠቅስ የማላፈው መረጃ ዛሬ ወደ ኮሚኒቲ የስብሰባው አዳራሽ ከአባላት ውጭ መግባት እንደማይቻል እና የመግቢያው በር ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ የተረዱት ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን በአንድ ቀን ጀምበር ከ50 ለሚበልጡ ደጋፊዎቻችው ከ5 ሺህ ሪያል በላይ የአባላነት ምዝገባ ከፍለው የመታወቂያ ካርድ ወስደዋል፡፤ ይህ ማለት በኮሚኒቲው የመተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተደነገግ አንቀጽ ማንኛውም አዲስ አባል የመምረጥም ሆነ የመመረጥ አሊያም በኮሚኒቲው ማናቸውም ጉዳዮች አስተያየት መስጠት የሚችልበት የግዜ ገድብ ተደንግጓል ። ታዲያ ሼኩ ለነዚህ ግብረ አበሮቻቸውን ከትላንት በስቲያ ከ5 ሺህ ሪያል ከስረው ያስመዘግቦቸው ለምን ይሆን ? ሰላም ያሰማን ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ሹመኛ ካድሬዎች February 3, 2025 11:07 am
  • ትግሉን የጎዳው የእስክንድር ነጋ አካሄድ February 3, 2025 10:29 am
  • ኤሊያስ መሠረት “ጭምብሉ ዛሬ ወለቀ”፤ ተከፋይ ነው! February 2, 2025 05:32 pm
  • የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት? January 23, 2025 03:41 pm
  • ታሪካዊዉ የፋሲል ቤተመንግሥት ለምን ነጣ? January 23, 2025 03:04 pm
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተወልደ አስተዳደር ዘመን ለተሠራ ስህተት 425ሺ ዶላር ተቀጣ December 14, 2024 01:44 am
  • በትግራይ ከሞትና ከአካላዊ ጉዳት የተረፉት ለስደት ተዳርገዋል November 27, 2024 12:09 pm
  • የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን እንዲያርም ጥብቅ መመሪያ ተሰጠው November 27, 2024 11:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule