በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ ሳምንት አሰራጭቷል! ያለ አንዳች መረጃ። “ለነጮች እጄን አልሰጥም!” ብሎ አድዋ ላይ ስላዋረዳቸው ምኒሊክን ለማንቋሸሽ ምንም መረጃ አያስፈልጋቸውም።
እልፍነሽ ቀኖ የተባለች የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ በአንድ ወቅት በለቀቀችው ነጠላ ዜማ ምክንያት ማእከላዊ እስር ቤት ታስራ ነበር። ምርመራውን የሚያካሂዱት ሰዎች በመጀመርያ የዘፈኑ ግጥም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም አደረጉ። በግጥሙ ምንም አይነት የወንጀል ነገር ሲያጡ ግጥሙ “የህግ ትርጉም ይደረግለት” ሲሉ አዘዙ። የህግ ትርጉሙም ብዙ ስላላስኬዳቸው ለግጥሙ የፖለቲካ ትርጉም እንዲሰጠው አደረጉና ሙዚቀኛዋን “ጥፋተኛ ነሽ” ሲሉ ከሰሱ። የፖለቲካ ትርጉሙ “ይህን ያለችው እንዲህ ለማለት ነው…” ከማለት ተነስቶ አቀንቃኝዋ በልቧ አስባው ይሆናል የሚለውንም ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ “የፍትህ ሰዎች” የምናስበውንም ያውቁ ኖሯል።
የበደሌ ቢራ አድማ ጠሪዎች ቴዲ አፍሮ በልቡ ያሰበውን የማንበብ ሃይል እንዳላቸው አናውቅም። እሱ ግን የተባለውን ነገር እንዳልተናገረ ገልጾላቸዋል።
አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያከሄዱት ጦርነት “ቅዱስ ጦርነት ነው” ወይንም “አይደለም” የሚለውን ሙግት ለግዜው ወደጎን እንተወው። ምክንያቱም የዚህ ውይይት ውጤጥ የኦሮሞ ህዝብ አሁን ላለበት ችግር የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። የህሊና አይኖቹን ክፍት አድርጎ ለሚመለከት ሁሉ፤ የዛሬው የኦሮሞ ህዝብ ችግር የበዴሌ ቢራን ከመጠጣት እና ካለመጠጣት የላቀ ነው። ለነገሩ እንጂ 90 በመቶ የሚሆነው የኦሮሞ ህዝብ የሚተዳደረው በግብርና፤ ኑሮውም ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑ የበደሌ ቢራን የመጠጣት አቅሙም ሆነ እድሉ የለውም። የዚህ ዘመቻ መሪ ተዋንያን የሆነው ጃዋር መሃመድ እንደነገረን ከሆነ ደግሞ 90 በመቶው የኦሮሞ ህዝብ የሙስሊም እምነት ተከታይ ነው። በሙስሊም አልኮል “ሃራም” ነው።
“እስር ቤቱ ሁሉ ኦሮምኛን ይናገራል!” ያለው ማን ነበር? አዎ! የስርዓቱ ቁንጮ የነበረው ስዬ አብርሃ ነው። ስዬ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ከርቸሌ ታስረን የነበርን ጋዜጠኞች የእነ ኦቦ ባይራን ጉዳይ እያነሳን በኦነግ ስም በግፍ ለታሰሩት ስንጮህ የዝሆን ጆሮ ነበር የሰጠን። አቶ ስዬ አብርሃ አይኑ የተከፈተውና ጆሮው ኦሮምኛን መስማት የጀመረው እጆቹ የኋሊት ታስረው ቃሊቲ ሲወርድ ነበር። በእርግጥ ማየት ማመን ነው። ያየውንና የሰማውን በመመስከሩ ሊመሰገን ይገባዋል። ልብ በሉ። እስረኛው ሳይሆን እስር ቤቱ ነው ኦሮምኛ እየተናገረ ያለው።
ሂዩማን ራይትስ ዋች ሰሞኑን በለቀቀው ዘገባ፤ በኦሮሞ ወገናችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን አስከፊ ስቃይ በድምጽና በምስል ጭምር አሰራጭቷል። ይህንን ስቃይ ለማስቆም የፌስቡክ ታጋዮቹ ስንት ሺህ ፊርማ እንዳሰባሰቡ አልነገሩንም። የበዴሌ ቢራን የኦሮሞ ህዝብ እንዳይጠጣ በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 ሺ ፊርማ ተሰብስቧል ብለውናል።
እርግጥ ነው። “ሰብአዊ መብት ይከበር!” የሚል ዘመቻ ከመጀመር ይልቅ “ቢራ አትጠጡ!” ማለቱ ቀላል ሊሆን ይችላል። በምእራቡ አለም የሚመረተውን ሄነከን ቢራ ራሳቸው እየተጎነጩ ይህንን ቀጭን ትእዛዝ ሲያስተላልፉ ግን በዚያ ትልቅ ህዝብ ላይ እያሾፉበት መሆኑን የዘነጉት ይመስላል።
የኦሮሞ ልሂቃን ግራ ያጋቡኛል። ይህን ስል ያለምክንያት አይደለም። በአባ ጅፋር ግዛት ተወልጄ በኦሮሞ ባህል ታንጼ ነው ያደግኩት። በደሙ ብቻ ‘ኦሮሞ ነኝ’ እያለ ከሚመጻደቀው ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ ማንነት ጠንቅቄ አውቀዋለሁ። ቋንቋው፣ ባህሉና ስነልቦናው ውስጡ ሰርጎ ሳይገባ በደሙ ብቻ ራሱን እየለካ ከህልም እና ከቅዠት አለም ውስጥ ገብቶ የኋሊት ከሚራመደው በተሻለ መንገድ። . . . እናም አንድ የኦሮሞ ህዝብ አውቃለሁ። በቋንቋው፣ በባህሉና በታሪኩ የሚኮራ ህዝብ። ታታሪና ሰራተኛ ህዝብ። ከሌላው ጋር ተዋልዶና ተከባብሮ በፍቅር አብሮ የሚኖር ህዝብ። የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር በደም ተሳስሯል። ሃቁ ይህ ነው። ግና ፖለቲከኞቹ ከዚህ ህዝብ በሁለት ሺህ ማይልስ ርቀው በምእራቡ አለም በሚሰሩት ስራ ይህንን ትልቅ ህዝብ እጅግ ትንሽ የሚያደርግ መሆኑን ያስተዋሉት አይመስለኝም።
በቅርቡ ሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመችውን ግፍ ለመቃወም በአለም ዙርያ ያለ ኢትዮጵያዊ በጋራ በሚጮህበት ወቅት አንድ እንግዳ ክስተት በኢንተርኔት ላይ ወጥቶ አየን። “ሳውዲ አረቢያ ኦሮሞን አትግደሉ፣ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አይደለም፣ ኦሮሞ ወንጀለኛ አይደለም።” የሚል መፈክር የሚያሰሙ ሰዎች ለብቻቸው ሰልፍ ወጡ። እነዚህ ሰዎች የተሰለፉት “ኦሮሞን አትንኩ። ሌሎቹ ግን ወንጀለኞች ስለሆኑ ይገባቸዋል” የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር። መቼም ከማንም ሰብአዊ ፍጡር እንዲህ አይነት ኢ-ሰብአዊ አባባል አይጠበቅም። ድርጊታቸው ያሳፍራል። አንገትም ያስደፋል። ይህ አሳፋሪ ድርጊት እኔን እንዲህ ካሸማቀቀኝ፤ አፈር ስንፈጭ ያደግነው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሮ የኦሮሞ ልጆች ቢያዩት ምን ሊሉ እንደሚችሉ በምናቤ እስል ነበር። በዚያ ትልቅ ሕዝብ ስም አደባባይ ወጥተው፣ ተግባራቸው ግን ማስተዋል የተሳነው ትንሽ ህዝብ ነበር። ያንን ኩሩ ህዝብ እንዲህ … እንዲህ እያሉ ሊያሳንሱት አየን።
እ.ኤ.አ. በ1998 ገደማ አቶ ዳዊት ዮሃንስ በሆላንድ ውስጥ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ከስብሰባው መሃል አንድ ሰው ከመቅጽበት ተነስቶ ”ለኦቦ ነጋሶ ጊዳዳ የሚያደርሱልኝ ጥብቅ መልእክት አለኝ” አለ። ስብሰባውን የሚመራው አቶ ዳዊት ዮሃንስም ሰውዬው ተነስቶ መልእክቱን እንዲናገር ፈቀደለት። ሰውየው ከመቀመጫው ተነሳ።
“ፊንፊኔ መሃል ላይ ያለው የምኒሊክ ሃውልት በአስቸኳይ እንዲነሳ ይንገሩልን!” አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ በኩራት እየተናገረ። በስብሰባው የነበርን ሰዎች ግን ለተናጋሪው አፈርን። ያሳፈረን ይህንን መልእክት ማስተላለፉ አልነበረም። ሰውየው ሊናገር ከመቀመጫው ሲነሳ ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ያነሳል ብለን ገምተን ስለነበር እንጂ። ”ሰዎች በዘራቸው (በኦሮሞንታቸው) ብቻ የሚታሰሩት፣ የሚሰቃዩትና የሚገደሉት እስከመቼ ነው?” የሚል መልእክት ነበር የጠበቅነው። ምክንያቱም ወቅቱ በቁጥር 20 ሺህ የሚደርስ የኦሮሞ ተወላጆች የጦር ካምፕ እስረኛ እንዲሆን ካደረጉ በኋላ፤ የኦነግ መሪዎች በባሌ ሳይሆን በቦሌ እየተሸኙ የወጡበት ሰሞን ነበር። የኦነግ መሪዎች ከህወሃት ጋር በጋራ መስርተውት የነበረውን ቻርተር ረግጠው በመውጣታቸው ምክንያት ኦሮሞው ወገናችን የህይወት መስዋእትነት ጭምር ይከፍል የነበረበት ወቅት።
ዳዊት ዮሃንስም አግባብ ያለው ጥያቄ መሆኑን ከተናገረ በኋላ መልእክቱን ለርእሰ-ብሄሩ እንደሚያደርስ ቃል ገብቶ ሄደ። መልእክቱን ለዶ/ር ነጋሶ ያድርስ፤ አያድርስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በዚያን ወቅት የሃገሪቱ ርዕሰ-ብሄር ነበሩ። እንኳንና የተባለውን መልእክት ሊያስፈጽሙ፤ እሳቸውም የዛ ስርዓት ሰለባ ሆነው አየን።
የተዛባ ታሪክ ይዘን፣ ጥላቻን ብቻ በምናባችን አርግዘን የት እንደምንደርስ አላውቅም። አሁንም በመፍትሄው ላይ ሳይሆን በችግሮቹ ላይ ተወጥረናል። የምኒሊክ ሃውልት ተነሳም አልተነሳ እንደ እንስሳ ለሚታደነው የኦሮሞ ህዝብ ምን ፋይዳ አለው? “በእስር ያሉ ወገኖቼ ይፈቱ!” ለማለት እንኳን ሞራል ሳይኖረን አእምሯችንን በአፈ-ታሪክ ብቻ ወጥረን አንዲት ኢንች እንኳን ወደፊት መራመድ እንዳልቻልን ለምን አናስተውልም?
አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን ግዛት አንድነት ለማስፋፋት ባደረጉት ጦርነት ወንጀል ፈጽመው ከሆነ አጽማቸው ወጥቶ ለፍርድ ይቅረብ ነው የምትሉት? ወይንስ ይህ ትውልድ የዚያ ወንጀል ውርስ አለበት? ውርስ ካለበትስ ማን ነው ወራሹ? አማራው? ጉራጌው ወይንስ ኦሮሞው? እንደ ዘረኞች፣ ደም መለካት ካለብን እኚህ መሪ ከአማራም፣ ከኦሮሞም፣ ከጉራጌም ይወለዳሉ። ጠለቅ ብለን ከሄድን ደግሞ ራስ ጎበና ዳጬን በዚያ ስእል ውስጥ እናያለን። ምእራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያን በሃይል የያዙና ያስገበሩ የአጼው የጦር መሪ። ራስ ጎበናን ልንጠላቸው እንችል ይሆናል። ኦሮሞነታቸውን ግን ልንክደው አንችልም። የወንጀል ውርስ በተዋረድ (guilt by association) ውስጥ ከገባን የኦሮሞን ህዝብም በአእምሯችን ለፈጠርነው ወንጀል ወራሽ ልናደርገው ነው።
የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” አልበም የሚያሞግሰው ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት የታደጉትን ጀግኖች ነው። እነ ፊታውራሪ ሃብተጎርጊስ ዲነግዴን እና እነ ባልቻ አባ ነፍሶ። ቴዲ አፍሮ ለነዚህ ጀግኖች ባያቀነቅንላቸውም ከታሪክ መዝገብ ላይ ልንፍቃቸው አንችልም። የታሪክ ተመራማሪዎች ስለነዚህ ጀግኖች የጻፉት አፈ-ታሪክ ወይንም ድርሰት አይደለም። በጀግኖቹ የምንኮራው በዘራቸው ሳይሆን የሰሩት ገድል ነው። በ’ጥቁሩ ሰው’ የተመራው ይህ የጸረ-ቅኝ ግዛት ገድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው አፍሪካና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህ ሊዋጥላችሁ የሚገባ እውነታ ነው። በዚያ ገድል የሚያፍሩ ካሉ የራሳቸው ጉዳይ። መላው የአፍሪካ ህዝብ ግን ይኮራበታል። የአለም ጥቁር ህዝብም ሲያስታውሳቸው ይኖራል።
ዘር እየቆጠርን ከሄድን ብዙ የሚጎረብጡ ነገሮችን ልናነሳ ነው። በግዛት ማስፋፋቱ ሂደት ግን አንድ ሃቅ አለ። ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ህልቀ መሳፍርት ኢትዮጵያዊ አልቋል። ይህ ደግሞ የድንበር መስፋፋት፤ እድገት እና ስልጣኔ ይዞት የሚመጣው ችግር እንጂ አንድን ህዝብ ለመጨረስ ጥናት ተደርጎ የተሰራ እንዳልሆነ ታሪኩን ከስር መሰረቱ ማየቱ ይበጃል። ችግሩ በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በአያሌ ሃገሮች እንደተከሰተ የታሪክ መዛግብት ይነግሩናል። በ17ኛው ክፍለዘመን የተከሰተው የኢንዱስትሪ አብዮት ሳብያ እንኳን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የማይተናነስ እልቂት ነበር።
አጼ ምኒሊክን ከጀርመኑ ኦቶ ቮን ቢስማርክ ጋር የሚያመሳስሉ ምሁራንም አሉ። እርግጥ ነው ጀርመን አሁን የያዘችውን ግዛት ቅርጽ እንድትይዝ ያደረገው ፕሩሲያዊው ቢስማርክ ነው። ቢስማርክ የጀርመንን አንድ ታላቅ ኤምፓየር ለመፍጠር አንባገነን፣ ሃይለኛና ጦረኛ መሆን ነበረበት። ታዲያ ይህችን ሃያል ሃገር በመመስረቱ ጀርመኖች አልጠሉትም። ይልቁንም የጀግንነት ስያሜ ለግሰውታል። አያሌ የመታሰቢያ ሃውልቶችንም አቁመውለታል።
ቢስማርክ የህግ ምሁር ነበር። አጼ ምኒሊክ ግን መደበኛም ሆነ ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ ሰው አልነበሩም። ከታሪክ እንደምንረዳው በአጼ ልብነድንግል ዘመነ መንግስት፤ የግራኝ አህመድ ወረራን ተከትሎ የነበረውን መከፋፈልና መተላለቅ ለማስቆም መሪዎች ተነሱ። ሃገርን አንድ የማድረጉን ትግል አጼ ቴዎድሮስ ጀመሩት፣ አጼ ዮሃንስ ቀጠሉበት ከዚያም እምዬ ምኒሊክ ተረከቡት።
አጼ ምኒሊክ ለአመታት በኦነግ ሰዎች ተወግዘዋል። ውግዘቱ አሁንም እታገልለታለው የሚሉትን ህዝብ ችግር ሲፈታው አለየንም። በ1991 ከህወሃት ጋር ጋብቻ ፈጽመው የምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሲገቡ ይናገሩት የነበረውን ሁሉ ረሱት። ከቶውንም ያነሱት የነበረው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጉዳይ ሳይሆን የስልጣን ጥያቄ ለመሆኑን አረጋገጡልን። የሽግግር መንግስቱን ቻርተር ሲያጸድቁ “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” የሚለውንም ሳያውቁ ዘንግተውት ነበር። ከገዢው ፓርቲ ጋር የጀመሩት ግዚያዊ ጋብቻ በፍቺ ሲጠናቅቅ የምኒሊክ ጠላትነት መፈክራቸውን እንደገና አነሱት።
የዘር ፖለቲካው ስካር ሞቅ ብሎ በነበረበት በዚያን ወቅት እንደቀልድ ይነገር የነበረ አንድ ቁም ነገር አለ። አንድ የምግብ ቤት በር ላይ በላቲን ፊደል “አማራ መግባት ክልክል ነው!” የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል። የጽሁፉ ትርጉም ያልገባው አንድ የአማራ ተወላጅ ጎራ ብሎ ምግብ አዘዘ። አስተናጋጆቹ የሰውየው ድፍረት አስደነገጣቸው። ባለስልጣን ስለመሰላቸው አስተናገደዱት። ዳግም እንዳይመለስም እጥፍ ዋጋ አስከፈሉት። ሰውየው በድጋሚ ሲመጣ ሶስት እጥፍ አስከፈሉት። በሌላ ግዜ ከአምስት ጓደኞቹ ጋር መጥቶ ምግብ አዘዘ። ከተስተናገደ በኋላም አራት እጥፍ ቢል አቀረቡለት። በዚህ ግዜ ቲፕም ጨምሮ ሰጣቸው። የሆቴሉ ባለቤት በነጋታው “አማራ መግባት ክልክል ነው!” የሚለውን ጽሁፍ አንስቶ “ኦሮሞ መግባት ክልክል ነው!” በሚል ቀየረው።
በአሁኑ ዘመን ከበድ አለ እንጂ፣ ሰዎችን በጎሳ አደራጅቶ ከማሳደም የቀለለ ትግል የለም። ደም ከውሃ ይወፍራል እንዲሉ፤ ሰዎች በጋራ የሚጋሩትን ነገር እያነሱ ስነልቦናዊ ዘመቻ ማድረግ ስኬት ሊኖረው ይችላል። ዘለቄታ ግን አይኖረውም። የዘር ፖለቲካ ልክ እንደ ስካር ነው። ይሞቃል ከዚያም ይበርዳል። በርግጥ በሞቅታ ግዜ የሚፈጠረው አደጋ ቀላል ላይሆን ይችላል። እ.ኤ.አ. በ1993 በምስራቅና በምእራብ ኢትዮጵያ የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ለዚህ ዋቢ ነው። የኦነግ ልሂቃን የ19ኛውን ክፍለ ዘመን ጉዳይ እየደጋገሙ ያነሱልናል። በ21ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው እጅ የተፈጸመው ግድያ ግን በብሄራዊ ቴሌቭዥን ጭምር እንድናየው ተደርጓል። ነብሰ-ጡር ሴቶች በጩቤ ሆዳቸውን እየተሰነጠቁ ሲገደሉ አየን። ነብስ ያላወቁ ሕጻናትና የ90 አመት አዛውንት ጭምር ከተራራ ላይ እየተወረወሩ ሲጣሉም የአይን ምስክሮች ነን። እነዚህ ሰዎች የምናስታውሰው ይህን በመሰለ ወንጀል ብቻ አይደለም። ድርጊቱ የቂምና የቁርሾ አሻራ ጥሎ አልፏል።
ይህ ሁሉ በደል በዘመናችን ተፈጸመ። በዳዮቹ ግን አሁንም በቀልን አርግዘው ይጓዛሉ።
የበደሌ ቢራን አለመጠጣት የኦሮሞን ችግር የሚፈታ ከሆነ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቢራውን መጠጣት ያቁም። የአኖሌን ሃውልት መሰራት ለኦሮሞ ህዝብ ፍትህ የሚያመጣ ከሆነ ደግሞ፤ ሃውልቱ በየከተማው ይገንባ። ግና ይህ ሃውልት ለመጭው ትውልድ ጥሎት የሚያልፈው ቂምና በቀልን እንጂ፤ ለሚታገሉለት ህዝብ የፍትህ ጥያቄ ዋስትናው ምን እንደሆነ ልንረዳው አልቻልንም። አሁን ያለው ትውልድ ያልፋል። ከዚህ ትውልድ በኋላ ለሚወለዱት ልጆች ጥለንላቸው የምናልፈው ቅርስ ጥላቻ፣ ቂም እና በቀል ብቻ ይሆናል።
ከዘመናችን ታላቅ ሰው ከኔልሰን ማንዴላ አንድ ነገር እንማር። ማንዴላ የደቡብ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን የአለምን ፖለቲካ የለወጠ የፖለቲካ ነብይ ነው። ይህንን ሲያደርግ የፖለቲካ ፎርሙላ አልነበረውም። ክፉን ነገር በበጎ ለማሸነፍ ወሰነ። ጥላቻን በፍቅር ለወጠ። ልክ እንደ ክርስቶስ፣ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ብሎ በፍቅር አሸነፋቸው። ታሪክ ሰርቶ አለፈ። ስሙም ከመቃብር በላይ ለዘልአለሙ ይኖራል።
endalk says
tekekelegna zegeba new yeminilek tarike eko yemmelaw ethiopiaw tarik new .ye amar wyem yesemen shew sewche aydelem besachew merint melaw yehagere gobez yeseraw TARIK!!!!?!
fisseha says
oh. min ayinet agelalets new. endet lib yinekal. wunet internet lay rezem yale tsihuf lemejemeria gize temesiche anebebkugn. bewunet betam tiru astemari neger new. Europe 1 lemehone eyetaru new egna gin 1 bet wust tekemiten eskahun eyetetalan new. eski ketilubet astemirun.
Ameseginalehu.
semen e says
selam . bergit betam astemari xuhuf new. gin and neger lastawisih . ye oromo hizib simet anete banebebkew eniji oromo huneh atawqewum .simetachew ketarik gar lemin mewtat tesanachew lemilut gin kexafkew tenesiche liteyq .wendme oromowoch haxe minilikin mersat aychilum mikniyatum be minilik gize tebedeln eyalu new . endetebedelu demo enawqalen silezih yqrta bilenal lezih hizb alalnim .minilik le ethiopian andinet yhun le ethiopian andinet yefelegkewin belew oromo ennde sew yqoter alneberem . silezih qim beqelinetin enditewu bilen kaln engas lemin lenesu metfo simet yemifetirlachewin hawelit anafersewum .1enesu beteyqut bicha sayhon engas min mehon endalebin masebu 2simetachew esti oromo hunen enasibew ena yane ygebanal . hasaben lemateqalel (yeminilik hawelt le oromo hizib metfo simet kalew bifersna keneziya simet endiwetu biniredachew. )haweltu endifers endematifeligu ygebangal . and neger gin lastawisachu haxe minilik letiqur hizb andinet leafirika kurat nachew awo yes. wanaw tiqur hizbib asafari tarik yesera tiqur hizbin yawarede hizbun al nechet asalifo yesete asafarini tarik biresaw yshalal kemibalu meriwoch new .silaltewegachu laygebachu ychilal yetewegan gin aniresawum . sorry qireta kalechu hasaben new
Fufa Kediro says
We Ethiopians, we are one and the same. We are sharing all happiness and sadness together. No one can separate us. Yes, different regimes in the country worked very good and bad things. But, from the experience of developed countries what we learn is to strengthen those good things and leave the rest for the history. We have never seen any developed countries playing ZERO game. So, we Ethiopians should follow such experience. Otherwise, by the name of unity, it is not good to remind those devil activities. For the sake of politics, nowadays we are listening artificially made history of Ethiopia before 100 years. Do not be foolish, we have seen our fathers, mothers, sisters and brothers slaughtered and thrown away during the past 20 years. Yes, who did that? We are Ethiopians. We have to work for our development. We have to struggle for coming out of poverty. Dear brothers and sisters, do not be confused by those employees who are selling the name of our nation Oromo. They do represent us. They are just crying for their Dollar. Otherwise, they know nothing about Oromo people history. If they know history, they do not accuse of their ancestor. They do not accuse their blood.
Atse Milinik was the emperor of Ethiopia. He was the first person to bring civilization to Ethiopia. His thought was ahead of time. Even ahead of the present time. In fact, he was not educated but he had brilliant mind. He was exercising Federalism. He was not racist. His ministries were from all corners of the country. Let me ask those employees who are crying for their Dollar, do you know BALCHA ABA NEFSO, Fitawrari DINEGDE. Fitawrari Balcha was the hero of Adawa. He was the decisive person for the country. Fitawrari Dinegde was the ministry of defence force. You guys especially those who are crying for Dollar, please stop for some time and think for your nations Oromia. Oromia is our mother land. please work for it. Do not merely cry for your Dollar.
Teddy Afro our brother, please keep up your momentum! Do not worry about the employees. They are just crying for their Dollars. We your brothers and sisters are besides you.
Ittiyoophiyaan biya Waqqayoo dha!
Galatoomaa!
aradaw says
I really do not understand this logic at all. Let “to strengthen those good things and leave the rest for the history”. Atse Menelik is a very controversial king and as such is a sign of division rather than unity. Praising Menelik and his war lords does not bring unity. It is a historical fact that Menelik fought the Italian invaders. It is also a historical fact that he invaded the southern part created massive depopulation, systematic wealth appropriation, enslavement . This is also historical fact. What the above writer telling us is just praise his war against Italy and shut anything that happens in the south. Dear friend you can not create unity when half of the population have serious grievances and outright neglect to what happened in the south. Menelik may not a resist but absolutely he was equal opportunity oppressor and exploiter. He will use anything and anyone until his goal of oppression is fulfilled. I am very sorry where you read your history (artificial history) Anything that does not fit your twisted mind is artificial. Let me tell you two evils does not equal justice. What happen then and what happen today are both evils and should be condemned and not tolerated. You can not condone one and tolerate the other evil is evil. Dear friend, please do not spit what comes to you mind, think twice before you use the key board. Again, as before, unity can not be achieved with those like you who twist history and do not think logically and with those like you who insult others as “employee”. Unity can only be achieved with those who really know Ethiopian history who are tolerant and compassionate and who see the pain of the others and walk with their shoes. Give a chance to reason and if you can read history, tell the truth, show an olive branch to those who has been insulted abused oppressed.
Abraham says
touching. I wish if they could I understand this. please God don’t let us kill each other
Mela Mela says
……… እንደነገረን ከሆነ ደግሞ 90 በመቶው የኦሮሞ ህዝብ የሙስሊም እምነት ተከታይ ነው። በሙስሊም አልኮል “ሃራም” ነው።
አእምሯችንን በአፈ-ታሪክ ብቻ ወጥረን አንዲት ኢንች እንኳን ወደፊት መራመድ እንዳልቻልን ለምን አናስተውልም? well said
Z Gamel says
Right!!! you touch my heart. really you have explained it shortly and precisely. please continue and I will follow you…..
Dereje woldeyes says
Even the writer of this material is pregnant with hate;foolish habeshat;try to update your self still menelik? Geze alfobehal;tesfa kurat
Hundaol says
Bizu neger lemeweret mokirehal… Lemehonu le Oromo bizu atasib! Yeminilikin amagnoch we don’t need u such! U’re our enemy at any time! Stupid neftegna! Kan akka teeti taanatu dhiiga ilmaan Oromo baay’ee dhuge.
Martha says
May God richly bless you. We need Ethiopians like you who are positive-minded, who foresees the future of our country instead of hate-mongering individuals hiding in the west.
Afadis says
Jawar said ” ine beminoribet akababi 90 be metow muslim new”. And you said “90 be metow ye oromo hizb muslim new ale jawar”. Misleading? You are obviously anti-oromo. If u beleive in ethiopian unity u ve 2 try to compromise. Chifin amara akrari athunu ebakachu:(
I'm Not Amara I'm Not Oromo says
I believe both Christinity and Muslim religion teache’s about forgiveness so I wonder why we are not experienceing to forgive eavhother and move on , and grow together we have to know that if we devided we fall but if we united we grow ,if you believe this or not this the truth ! the western are becoming one nation and we have nothing and we are fighting each other what shame ? Do you guys believe Children has to get punished for the sins committed by their parents ? I don’t think so , Minilik is not from our generation I don’t even understand why this new generation talks about him Grow up please forget about menelik good and bad part and let’s focus how we can fix our current problem ” sele mote sew jegnenet ena kifat mawerat min waga alew ” weak up people lets not talk about dead person his dead end of story weather he was good or baf again he is dead done finish no point talking about him ” sera fet yasebelal ” ere please we can do much better than this this is so childish both side amara and Oromo stop this childish game and let’s love one another hate is from the devil not from God or Allah so love one another STOP fighting about bedel beer and fighting about menilik that’s so silly
Nancy says
“UNITY” is the key of our victory, because of few narrow minded mad cow, we chose to follow their path. That is why the division is growing fast and in a very aggressive way.
The reason was, we kept silent when those educated Amharas kicked out of other regions, we kept silent when Amhara people was murdered in a horrific way and thrown from the hill to the deepest part of Harar, we kept silent when those intelligent Ethiopians slathered by these animals, we kept silent when people elicited from ancestor lands and left to die we kept silent when a child shot by soldiers in the field, we kept silent when those journalists thrown to prison, tortured, and injected with infectious diseases and die, we kept silent when our sisters injected not to have a child, we kept silent when young man thrown to jail and die with no justice, we kept silent when those criminals killed thousand of our brother and sisters with no crime committed, we kept silent when we refused to morn when we lost our sisters and brothers in Saudi, we kept silent when we chased, bitten and thrown to prison in front of Saudi Embassy to protest about the treatment our brothers and sisters, and Childers received. we kept silent when 78K farmers evicted from the land they fertile and live for a long time and left to die, we kept silent when chines raped our sisters in groups, tortured and killed our people, in general we kept silent and waited for our turn to come to be taken to the slathered house by these Government while they make not million but billions of
dollar while nation suffers in many way
Tell me how these nation able to forgive and forget the horrible experience we received for the last twenty two years and have a normal life???? How can we hold one another hands and stand together when ethnic division promoted and implemented instead we say “NO”
Let almighty God bring his mercy upon us and punishment for those who killed, tortured, oppressed the nation and still work hard to destroy our history, culture and free land.
Otherwise we are a heading in unnecessary direction and by then it will be too late to resolve the situation.
Michael W.Ruphael says
The hardly won battle of Adwa over the colonialists was led by MenlikII; most of the Generals were Oromos- Menlik himself is an interesting compromise between the two large tribes. His relentless struggle for united Ethiopia is a pride for all of us incliuding other African notionalities. He lived in a very trying age of colonization, modernization, democratization and emancipation of human beings from slavery and other maladminstrations throughout the globe.
History will remember Menilik II. The Colonialists painfully try not to remember Him. Few old pro -colonialist writers helplessly tried to paint a bad image of him. But most contemporary scholars have placed him in the altars of leadership histoy. Now what is a big fuss after a century and quarter of years. Why not we dwell on the prevailing burning issues that we currently face; instead of execusing ourselves on what had had happened a century ago. Let’s work out with our differences and go forward for a practical resolution. Let us practice a good part of history on magnanomity from Menilik and later from Mandela. Whatis currently hanging on our neck don’t give a luxury of criticizing the past but do a better thing for our people now and immediately now.