• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሥራ ባልደረባዬ ሆይ! እንካ ስሙኒህን!!

December 27, 2019 05:27 am by Editor Leave a Comment

አንድ አሜሪካዊ የሥራ ባልደረባዬ ተሁለት ሳምንታት በፊት አለወትሮው ቆጣ ብሎ ጸጉሩን እየነጨ ሲትከነከን አገኘሁት። “ምነው በመላጣህ ምክንያት የቁንጅና ውድድር ወደክ ወይስ የቀጠርካት ጉብል ቀረቺብህ!” ብዬ ልቀልድ ብሞክርም አለወትሮው ከንፈሮቹ አልሳሳ ጥርሶችም አልታይ አሉ። ሁለቴ ጠበቅ አድርጎ “እፍፉ…” ብሎ ታምቆ የቆዬ እስተንፋስ ከተነፈሰ በኋላ “ይህ ትራንፕ እሚባል ሰው ተቀናቃኙን ለማጥቃት ስልጣኑን መጠቀሙ ቅደመ አያቶቻችን የመሰረቱትን የአሜሪካ መሰረት የሚንድ ነው!” አለና ብሶቱን ደጋግሞ ገለጠ።  

አቶ ትራንፕ ተቀናቃኛቸውን በፖለቲካ ለማጥቃት የስልክ ንግግር ማድረጋቸው ይኸንን ጓደኛዬን እንደ ሽንኩርት ቁሊት ማትከንከኑ ገርሞኝ አይኔን አፍጥጬ ሳለሁ አንድ አገራችን እሰማው የነበረ ተረት ቁልጭ ብሎ ተፊቴ ተደቀነብኝ። “ማን? መቼ? የት? ” እያላችሁ ነፍሰ-ገዳይ ገዥዎቻችሁን ጠይቃችሁ በማታውቁት ጥያቄዎች እንደ ንፍፊት አትወጥሩኝ። ተረት ነው እማወራው ብያለሁ።

አንድ ሰው መቶ ብር ይጠፋበታል። ይህ ያልታደለ ሰው በጠፋበት ገንዘብ ልቡ እንደ እባጭ ቆስሎና አንጀቱ እንደ ሰንበር ተመትሮ ወገቡን በግራ እጁ ደግፎና በቀኝ እጁ የሚንዠቀዠቀውን እንባውን እየጠረገ እናቱ የሞተችበትን ያህል ያለቅሳል። “መቶ ብር ይኸንን ያህል ያስለቅሳል?” በሚል ከንፈራችሁን እንደ እማማ የሻረግ አሸራማችሁ አታሽሟጡ። በተረቱ ጊዜ የነበረው መቶ ብር የዛሬው ግማሽ ቢሊዮን ብር ነበር። ይህ ሰው አንዴ ጎንበስ ሌላ ጊዜ ቀና እያለ፣ በእጁ አንዴ ወደ ፊት አየሩን እየገፋ፤ ሌላ ጊዜም ማጅራቱን ጠፍንጎ እየያዘ ሰፈር መንደሩ ድብልቅልቅ እስከሚል ድረስ “ኡኡኡ!” እያለ ወዮታውን ያቀልጠዋል። 

መቶ ብር የጠፋበት ሰው ኡኡታውን በሚለቅበት ሰዓት ተዚያው ሰፈር ሌላ ያልታደለ ሰው “ወይኔ ገንዘቤ! ወይኔ ንብረቴ፣ ወይ…ወይኔ!!” እያለ እንዲያውም ከመጀመሪያው ሰውዬ ይበልጥ እንደ ክረምት ዝናብ እንባውን እያዘነበ፣ ፊቱን እየነጨ አገሩን በለቅሶ ማናጋት ይጀምራል። ነጋዴ እሚበሳጨው እራሱ ስለከሰረ ሳይሆን ሌላው ስላተረፈ ነው ይባላል። ይህንን የተመለከተ መቶ ብር የጠፋበት ሰውየም “ለካስ ተእኔም የባሰ በዚች ምድር አለ!” ብሎ በመጽናናት ለቅሶውን ገታ አደረገና ወደዚህ ወደ ሁለተኛው ሰውዬ ጠጋ ብሎ “የኔ ወንድም እንዲያው ምን ያህል ገንዘብ ቢጠፋብህ ይሆን ይህንን ያህል ፊትህን የምትነጨው?” ብሎ የሚመልሰውን ለመስማት ጆሮውን እንደ ሙሰኛ ኪስ ቦርግዶ ይጠይቀዋል። ሁለተኛው ሰውየም አጽናኝ በማግኘቱ ልቡ ረጋ ብሎ ነገር ግን ሳግ እየተናነቀው “ እንደ ወርቅም… እንደ … አልማዝም የሚ..ያበራ የሰው እጅ ያልነካው ስሙኒ” ብሎ ይመልሳል። መቶ ብር ያጣው ሰውየም ቆጣ ብሎ “የኔ ወንድም እንካ ስሙኒህን! ለቅሶዬን አታበላሽብኝ!” ብሎ ሃያ አምስት ሳንቲሙን ለሁለተኛው አልቃሽ ሰጥቶ ዝም ካሰኘ በኋላ ትቶት የቆየውን ለቅሶውን እንደገና ማቅለጥ ጀመረ ይባላል።

የሥራ ባልደረባዬ በአቶ ትራንፕ ይትከነከን የነበረው የሚሊዮኖችን ነፍስ በመደዳ እንደ ትንኝ ያጠፉ፤ እግር እንደ ግንድ የቆረጡ፤ ጥፍር እንደ ስንጥር የነቀሉና ቆዳ እንደ ሌጦ የገሸለጡ አረመኔዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በድሎት ስልጣን ተንፈላሰው በሚገኙበት ሰዓት ነው።

የሥራ ባልደረባዬ በአቶ ትራንፕ ስልክ ጥሪ ይትከነከን የነበረው በእኛዋ አገር ተላይ በተገልጡት ወንጀሎች ተሳታፊና ተባባሪ የነበሩት ጭራቆች “ተሰማይ የወረዱ ሙሴዎች!” እየተባሉ በሚመለኩበትና በሚሸለሙበት ሰዓት ነው።

የሥራ ባልደረባዬ ተራ ወንጀልም ባልተገኘባቸው የሕዝብ ተመራጭ ይትከነክን የነበረው የእርሱ አገር አስራ አምስት እጥፍ የእድሜ ታላቅ በሆነችዋ የእኛዋ አገር መንጋዎች በዘር ማጥፋት ወንጀል በቀጥታና በተዘዋዋሪ የተሳተፉትን የሂትለር ደቀመዛሙርት እንደገና እንደ ቅርቀብ ሊጫኑ ድብዳባቸውን ተጀርባቸው እያስቀመጡ ባለበት ጊዜ ነው። መስማት ላልታከተው ዝርዝሩ ብዙ ነው።፡

ስሙኒ የጠፋብህ የሥራ ባልደረባዬ ሆይ! ጩኸትህ የእኛን በርካታ ሚሊዮን ሕዝብ ያጣነውን ጩኸት እያበላሸው ነው። እንካ ስሙኒህን! ልቅሷችንን አታበላሽብን!

4/2/2012 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule