የአዲግራት ወህኒ ቤት ተደረመሰ በትግራይ ክልል ካሉት እስር ቤቶች መካከል ከ1‚300 በላይ የሚሆኑ የሕግ እስረኞችን የያዘው የአዲግራት ወህኒ ቤት ባለፈው ረቡዕ ተደርምሶ 14 እስረኞች ሲሞቱ፣ ከ35 በላይ ደግሞ በከባድ ሁኔታ መጎዳታቸውን ሪፖርተር ምንጮች እንደነገሩት ጠቅሶ አስታወቀ። እስር ቤቱ በምን ምክንያት እንደተደረመሰ ያልገለጸው ሪፖርተር እስረኞቹን ለማትረፍ ሦስት ሎደሮችና በርካታ ወታደሮች ሲረባረቡ ማየታቸውን አመልክቷል። አደጋው ቀን ረፋድ ላይ መድረሱ በጀ እንጂ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል። ተረፉ የተባሉት 35 ሰዎች ክፉኛ በመጎዳታቸው አዲግራት ሆስፒታል ተኝተዋል። ህይወታቸው ያለፈው 14 እስረኞች ግን ከፍርስራሹ መቀበራቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያደረጉት በዶዘር የተደገፈ ርብበርብ በህይወት የተረፉትን ነፍስ እንደታደገ … [Read more...] about ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች