• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Left Column

ሥነ-ኪን (ጥበብ) ጥቅሟና ገጽታዋ በሀገራችንና በተቀረው አፍሪካ

January 16, 2015 08:55 pm by Editor Leave a Comment

ሥነ-ኪን (ጥበብ) ጥቅሟና ገጽታዋ በሀገራችንና በተቀረው አፍሪካ

ኪነት (ሥነ-ኪን) በሀገራችን ለሀገራችን ጠቅማ የነበረውን ያህል የማንንም ሀገር አልጠቀመችም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በፈር ቀዳጅነት ማለቴ ነው፡፡ እንዴት ቢባል 1. እናት አባቶቻችን ሊሉ የፈለጉትን ነገር በጊዜውና ያለጊዜው በቦታውና ያለቦታው በመግለጽ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዴት ባለ መንገድ ልናሻግረው እንችላለን የሚል የጋለና የታመቀ ስሜት መነሣሣት እና መንፈሳዊ ፍላጎት ከውስጣቸው አቀጣጥላ የራሳችንን ፊደል እና አኃዝ ወይም ቁጥር መፍጠር መቅረጽ እንዲችሉ አድርጋለች፡፡ 2. በዓይነቱ ልዩ የሆነ የሰማያዊ እና መንፈሳዊ ጥዑመ ዜማ ባለቤት አድርጋናለች፡፡ 3. በዚህም ቀደምት እና ኅብረ ዝማሬንም ለዓለም እንድናስተዋውቅ አድርጋናለች፡፡ 4. ዓለም በድጋሚ ሊያንፃቸው ወይም ሊቀርጻቸው የማይችላቸውን ከወጥ አለቶች የተፈለፈሉ ውብና ድንቅ ረቂቅ የኪነ-ሕንፃ  ውጤት የሆኑ … [Read more...] about ሥነ-ኪን (ጥበብ) ጥቅሟና ገጽታዋ በሀገራችንና በተቀረው አፍሪካ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

የጣይቱ ሆቴል ውድመት “ውዝግብ” ወይስ የእውነት ክህደት?

January 16, 2015 08:35 am by Editor Leave a Comment

የጣይቱ ሆቴል ውድመት “ውዝግብ” ወይስ የእውነት ክህደት?

“የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንደደረሱ ቢያጠፉ ሆቴሉን ማትረፍ ይቻል ነበር” የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ታደሰ፡፡ “በተደወለልን በሁለት ደቂቃ ውስጥ ደርሰናል፤ (የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ባለሥልጣን) 113 ሠራተኞች በ12 ተሽከርካሪዎችና በአምስት አምቡላንሶች ታግዘው፣ 236,300 ሊትር ውኃና 500 ሊትር ፎም በመርጨት ቃጠሎውን መቆጣጠር (ችለዋል)” አቶ ሰለሞን መኰንን የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ፡፡ “በፍጹም በሁለት ደቂቃ አልደረሱም፤ በሁለት ደቂቃ ወይም በሌላ ማለቱን ትተው በደረሱበት ወቅት ማጥፋት ቢጀምሩ ኖሮ፣ እሳቱ ወደ ሆቴሉ ሕንፃ ሳይዛመት ጃዝ አምባ ላውንጅ ላይ እያለ ማጥፋት ይችሉ ነበር፡፡ ስልካቸው አልሠራ በማለቱ በመኪና እዚያው ድረስ ተሄዶ እንደተነገራቸውና ነጋሪው መጥቶ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደርሰዋል፡፡ እንደደረሱም … [Read more...] about የጣይቱ ሆቴል ውድመት “ውዝግብ” ወይስ የእውነት ክህደት?

Filed Under: News Tagged With: Left Column

የፀረ-ኢትዮጵያዊው ገዥ ሥጦታዎች አያባሩም!

January 15, 2015 01:32 am by Editor Leave a Comment

የፀረ-ኢትዮጵያዊው ገዥ ሥጦታዎች አያባሩም!

የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በተደጋጋሚ ለታጋዩ ክፍል የሚያደርገው ልገሣ፤ ማብቂያ ዲካ የለውም። አሁን ደግሞ እልል የሚያስብል ስጦታ ፊታችን ላይ ዘርግፎልናል። በሰላም የሚታገሉትን ድርጅቶች፤ ለማፈራረስና ለመጪው ውድድር እንዳይሳተፉ ለማድረግ፤ ባለ በሌለ ጉልበቱ ዘምቶባቸዋል። ይህ የሚጠበቅ ነው። በርግጥ ሁሉንም ታጋይ ድርጅቶች በአንድ ጠፍር አንቆ ለማጥፍት መጣሩን የሚሳየው ድርጊቱ፤ ሳያውቀው የታጋይ ድርጅቶቹን በአንድነት እንዲሰልፉ በሩን በርግዶ ከፍቶላቸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ታጋይ ድርጅቶች፤ ከገዥው ድርጅት አንጻር አንድ በመሆን፤ አማራጭ ሆነው እንዲቀርቡ ከመጎትጎት ቦዝኖ አያውቅም። አሁን፤ ከመቼውም በላይ ይህ ጉትጎታ በሀገር ውስጥ በሰላም እየታገሉ ያሉትን ሀገራዊ ድርጅቶች፤ እንዲተባበሩ እየገፋቸው ነው። ለዚህም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከፍተኛ ድጋፍ ታክሎበታል። ይህ … [Read more...] about የፀረ-ኢትዮጵያዊው ገዥ ሥጦታዎች አያባሩም!

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር “የምርጫ ግብረ ኃይል” ጥርነፋ እያካሄደ ነው

January 13, 2015 06:32 pm by Editor 1 Comment

ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር “የምርጫ ግብረ ኃይል” ጥርነፋ እያካሄደ ነው

ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን "የምርጫ ግብረ ኃይል" በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን "አልወስድም ስትል ፈርም" እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ "የምርጫ ግብረ ኃይል" በተሰኘው መዋቅር የምርጫ ካርድ እንደማይወስዱና እንደማይፈርሙ ስለሚገልጹት ዜጎች ከሌሎች መረጃ በመጠየቅ ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆንን ገልጸውልናል፡፡ ከዚህም ባሻገር ካድሬዎቹ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለምርጫ ጽ/ቤት አቅጣጫ እንደሚሰጡ፣ የምዝገባ ሰነዶችም በእነሱ እጅ እንደሆኑና የምዝገባ ሂደቱን … [Read more...] about ኢህአዴግ ከምርጫ ቦርድ ጋር “የምርጫ ግብረ ኃይል” ጥርነፋ እያካሄደ ነው

Filed Under: News Tagged With: Left Column

ራስን ፍለጋ

January 12, 2015 07:23 pm by Editor 1 Comment

ራስን ፍለጋ

ጸሃይ አዘቅዝቃ ስትገባ ከቤቷ ጨለማ ሲተካ ደሞ በሷ ቦታ አካባቢው ሁሉ ፀጥ ረጭ ብሎ ከሁከት ጫጫታ ዝምታው አይሎ የነገሰ እለት ያኔ ነው ማዳምጥ የዉስጠትን ጩኸት ፈልጎ ለማግኘት የጠፋን ማንነት፡፡ **** ዉብአለም ታደሰ ፤ 14-02-2007 … [Read more...] about ራስን ፍለጋ

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

“ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ

January 7, 2015 11:21 pm by Editor Leave a Comment

“ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ

የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት የገለፀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ በጉዳዩ ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡ መድረኩ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ጠቁሟል፡፡ ምርጫውን ለማስፈፀምና ለመታዘብ ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ገለልተኛ የሆኑ ሠዎች መመረጥ ያለባቸው ቢሆንም በቅርቡ የተመረጡት አስፈፃሚዎች አብዛኞቹ የገዥው ፓርቲ አባላት መሆናቸው እየታወቀ “የማንም ፓርቲ አባላት አይደለንም” እያሉ ፈርመው ወደ አስፈፃሚነቱ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ሲል ፓርቲው ቅሬታውን ገልጿል፡፡ መንግስት ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጐማ በተመለከተም ገንዘቡ ለሚመለከታቸው ፓርቲዎች ብቻ … [Read more...] about “ከኢህአዴግ ጋር በአስቸኳይ መወያየት እፈልጋለሁ” መድረክ

Filed Under: News Tagged With: Left Column

ትንሽ ምስክርነት ስለ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)

January 7, 2015 06:06 pm by Editor 2 Comments

ትንሽ ምስክርነት ስለ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)

ከመሰንበቻዉ መረራ ጉዲና ከ25 ዓመታት በላይ ካስተማረበት ዩኒቨርሲቲ ተባረረ የሚለዉ አስገራሚና አስደንጋጭ ወሬ ከተዛመተ በኋላ አነጋጋሪነቱ ሞቅ ብሏል፡፡ (በጨዋታችን ላይ የማከብረዉ መምህሬ ስለሆነ አንተ እያልኩ ነዉ የምጠራዉ … እሱም ቢሆን አንቱታዉን ብዙም የሚፈለገዉ አይደለም … አዉቃለሁ)፡፡ በይፋ ከዩኒቨርሲቲዉ መሰናበቱን የሚያስረዳ ደብዳቤ እንደረሰዉ ባይገልጥም ነገሩ እሳት ካየዉ … ነዉ እና የምናዝን እናዝናለን፡፡ ዶ/ር መረራን ሳዉቀዉ ለመጀመሪያ ጊዜ መረራ የሚባል ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ … በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ጎልቶ መዉጣት የጀመረዉ ይመስለኛል በ1992 ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ነዉ፡፡ በዚያን ጊዜ የደመቀ ባይሆንም ጥቂት ፖለቲከኞች ገዢዉን ፓርቲ ሲሞገቱ የሚያሳይ የቅድመ ምርጫ ክርክር በቴሌቪዥን ይለቀለቅ ነበር፡፡ ያኔ ታድያ የብዙዎችን ቀልብ የሳበዉ በእኩልነት … [Read more...] about ትንሽ ምስክርነት ስለ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ከሸአቢያ መልካም ነገርን ከኩርንችት የወይን ፍሬን ማግኘት ይቻል ይሆን?

January 7, 2015 08:14 am by Editor 2 Comments

ከሸአቢያ መልካም ነገርን ከኩርንችት የወይን ፍሬን ማግኘት ይቻል ይሆን?

ኢትዮጵያ ሆይ! አሁንስ ተስፋሽ ማን ነው እግዚአብሔር አይደለምን? መቸስ በጣም ይገርማል! ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ መከራችን ሊያልቅ ነው ስንል ገና መጀመሩ ነው እንዴ ጃል? ጉድ እኮ ነው! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ለመሆኑ ከዚህ በላይ ሌላ የመከራ ዘመናት መሸከም የሚችል ትከሻ አለህን? የአርበኞች ግንባር ግንቦት 7 ሌሎችም በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ኃይሎች ውሕደት ሊፈጽሙ እንደሆነ ካስታወቁ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ደርሶ በይፋ ለሕዝብ ከማስታወቃቸው በፊትም ከዚህ መግባባት ላይ ለመድረስ አጭር የማይባል ጊዜ እንደወሰደ መገመት ይቻላል፡፡ ይሄም ሆኖ “ታጋይ ኃይሎቹ ሊዋሐዱ እንደሆነ ካስታወቁ በኋላ ግን ዓላማቸው ያን ያህል ግልጽና ተጣጣሚ የሚፈልጉትም ከሆነ ምን አንጓተተው?” የሚለው ጥያቄ ከብዙዎች የሚነሣ ጥያቄ ነበረ፡፡ አሁን ግን የዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልጽ እየሆነ … [Read more...] about ከሸአቢያ መልካም ነገርን ከኩርንችት የወይን ፍሬን ማግኘት ይቻል ይሆን?

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!

January 4, 2015 04:42 am by Editor 1 Comment

ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!

“የራበው ሥራ ፈልጐ ማግኘት የማይችልና ልጆቹን ለማስተማር አቅም ያጣ ሰው ከባርነት ነፃ ነው ማለት አይቻልም፡፡” የሚለው የአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ. ጆንሰን ንግግር እውነትነት አሁን አሁን በጆሮዬ መደወሉ ራሴን እያስገረመኝ መጥቷል፡፡ የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ገደማ ሰዎች፤ ስለኑሮ ውድነት ሲጽፍ ብዙዎቻችን እያነበብን ፈገግ ከማለት በቀር ብዙ ልባችን አልተነካም ነበር፡፡ ምናልባትም በጣም አልፎ አልፎ ከምናነባቸው መጣጥፎች ይልቅ መንግስት ስለ ልማት የሚነፋው ጥሩንባ አደናቁሮን ይሆናል፡፡ አሁን አሁን የመንግሥት መዝገበ ቃላት “ልማት” የሚለው ትርጓሜ ግራ እያጋባን መጥቶ ጭራሽ ወደ ብስጭት የተመነዘረብን ብዙ ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ መንግስት ልማት የሚለው ከእኛ አፍ “ቫት” እያለ የሚነጥቃትን ገንዘብ ሰብስቦ ለሌቦች ካጠገበ በኋላ፣ በፍርፋሪዋ የሚሠራትን መንገድና ጤና ጣቢያ … [Read more...] about ጥቂቶችሊመነደጉ፤ብዙዎችአሽቆልቁለዋል!!!

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .

January 3, 2015 07:25 am by Editor 2 Comments

የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .

በጠለምት፣ በበየዳ፣ በጃናሞራ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በአርማጨኾ ነዋሪው እየተባረረ፣ ሀብቱ እየተዘረፈ፣ ያንገራገረው እየተገደለ፤ ሰው በምሬትና በሰቀቀን ኑሮውን መግፋት አቅቶት አጣብቂኝ ላይ ገብቷል። ትናንት ቡያ ነበር ክልሉ። ትናንት በሀከር ነበር ክልሉ። ቀጥሎ ራስ ደጀንን ወደነሱ አካተቱት። ጠገዴን ጠቀለሉት። ገፍተው ስሜን አውራጃን በሙሉ ጠቀለሉ። ወገራ አውራጃን ሽራርፈው ወሰዱና ጎንደር አውራጃን ተጠጉ። አሁን ዘለው የጎንደር ከተማውን ገነት ተራራ፤ የትግራይ መሬት እያሉ ለትግራይ ልጆቻቸው እያሰተማሩ ነው። ጎንደር ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ እየተገፋ ነው። ይህ የመኖርና ያለመኖር፤ ውሎ የማደርና በወጡበት የመቅረት፤ ተገፍቶ ተገፍቶ የገደል ጫፍ ላይ የተንጠለጠለ ሕይወት ሕዝቡን ሰቅዞ ይዞታል። ይህ ጉዳይ የጎንደሬዎች ብቻ ጉዳይ አይደለም። አዎ! በዋግም ተመሳሳይ ተግባር እየተፈጸመ … [Read more...] about የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 57
  • Page 58
  • Page 59
  • Page 60
  • Page 61
  • …
  • Page 85
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የቴሌኮም ጌትዌይ፣ የዳታ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ደህንነት – የዌብስፕሪክስ ጉዳይ ከባለቤትነት ክርክር በላይ ነው! November 17, 2026 11:54 pm
  • “የጫካ ቱጃሮች!”— የፋኖ አመራሮች ስለተሰማሩበት የገንዘብ ዝርፊያ አስደንጋጭ መረጃ November 17, 2026 05:43 pm
  • በየወሩ 4 ሚሊዮን ብር እየተከፈለው ሀገር ሲያፈርስ የነበረው ሪፖርተር November 16, 2026 01:17 am
  • ሻርኮቹ ከውጭ እስከ ሀገር ውስጥ ያደሩት ድር፣ ዌብስፕሪክስን (WebSprix) የመጠቅለሉ ድራማና ብሔራዊ ስጋት November 14, 2026 12:42 am
  • የመለስ ዜናዊን ጭንብል የገፈፈው የትህነግ ሚዲያ (EMF) ምስክርነት November 13, 2026 03:32 pm
  • ትህነግ በወታደራዊና በፖለቲካዊ መስክ እንደሞተ ሁሉ በሪፖርተር በኩል የሚዲያ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል November 13, 2026 01:13 am
  • በከባድ ታክስ ማጭበርበር የሚፈለጉት አቶ አበባው ደስታ፣ አማራጭ የቴሌኮም ጌትዌይ ፕሮጀክትን ሊጠቀልሉ ነው November 12, 2026 03:50 am
  • “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ November 10, 2026 05:12 pm
  • ከትህነግ የተማረኩና ከውጭ ሀገራት የገቡ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በቃሊቲ ለእይታ ቀረቡ November 6, 2026 03:36 pm
  • የመንግሥት ኃላፊዎች ወደ ሁርሶ የተወሰዱበት ምሥጢር November 5, 2026 12:43 pm
  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
Copyright © 2026 · Goolgule