• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፀረ-ኢትዮጵያዊው ገዥ ሥጦታዎች አያባሩም!

January 15, 2015 01:32 am by Editor Leave a Comment

የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በተደጋጋሚ ለታጋዩ ክፍል የሚያደርገው ልገሣ፤ ማብቂያ ዲካ የለውም። አሁን ደግሞ እልል የሚያስብል ስጦታ ፊታችን ላይ ዘርግፎልናል። በሰላም የሚታገሉትን ድርጅቶች፤ ለማፈራረስና ለመጪው ውድድር እንዳይሳተፉ ለማድረግ፤ ባለ በሌለ ጉልበቱ ዘምቶባቸዋል። ይህ የሚጠበቅ ነው። በርግጥ ሁሉንም ታጋይ ድርጅቶች በአንድ ጠፍር አንቆ ለማጥፍት መጣሩን የሚሳየው ድርጊቱ፤ ሳያውቀው የታጋይ ድርጅቶቹን በአንድነት እንዲሰልፉ በሩን በርግዶ ከፍቶላቸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ታጋይ ድርጅቶች፤ ከገዥው ድርጅት አንጻር አንድ በመሆን፤ አማራጭ ሆነው እንዲቀርቡ ከመጎትጎት ቦዝኖ አያውቅም። አሁን፤ ከመቼውም በላይ ይህ ጉትጎታ በሀገር ውስጥ በሰላም እየታገሉ ያሉትን ሀገራዊ ድርጅቶች፤ እንዲተባበሩ እየገፋቸው ነው። ለዚህም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከፍተኛ ድጋፍ ታክሎበታል። ይህ እልል ያሰኛል። ልንጠቀምበት ይገባል፤ ካወቅንበት! ድርጅቶችም እየሰሙና እየተቀበሉት ነው። ለረጅም ጊዜ ስጠብቀው የነበረው ደስ የሚያሰኘው ዜና እልል አሰኝቶኛል።

የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ከመድረክ ጋር በትብብር፤ ከሰማያዊና ከመኢአድ ጋር ደግሞ ውህደት ፈጥሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ስሰማ፤ አሁን የድሉ መንገድ በደንብ ተጠረገ አልኩ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ድርጅቶቻችሁን መታገያ አድርጉ እንጂ አታምልኳቸው ሲል የነበረውን አዳመጡ። “ትግሉ ትግል የሆነው፤ በዚህ ወይንም በዚያ ስም በሚጠራ ድርጅት በመካሄዱ አይደለም። ትግሉ የሚቀጥለው ድርጅታችንን ስለከለከላችሁን ወይንም ስለፈቀዳችሁልን አይደለም። የምንታገለው በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ፤ ትግሉን ግድ ስላደረገው ነው።” በማለት ተነሱ። ከመሰሎቻችን ሀገር አቀፍ ድርጅቶች ጋር አንድ ሆነን እንታገላለን አሉ። ስሙን ውሰዱት አሉ። ከዚህ በላይ ለትግል ሕይወትን መሥጠት የት አለ? ቆራጥነት የት አለ። ለዚህ እኮ ነው አንዱዓለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዩት ዓለሙ፣ በቀለ ገርባ እና ሌሎች እስር ቤት የሚማቅቁት። እናም አሁን ትግሉ የሀገር ሆነ። ትግሉ ለሀገር ሆነ። አንድነት፣ መኢአድና ሰላማዊ ተቀላቅለው ሲሰለፉ፤ ማንም ሳይቀድመኝ የመጀመሪያው አባል ለመሆን ለሩጫዬ ተዘጋጅቻለሁ። ያንዳቸውም አባል አልነበርኩም። አሁን የሁሉም ልሆን ነው። ይህን ጥሩ ሥጦታ ከንቱ ላባክነው አልፈልግም።

ድሮውንም ሥልጣን በምንም ዓይነት መንገድ እንደማይለቅ ያሳወቀው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በሰላም እየታገልን፤ አቤቱታችንን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እናሰማለን ያሉትን ሰላምተኞች፤ መፈናፈኛ አሳጥቶ አፍኗቸዋል። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ፤ በራሱ የዕለት ተዕለት ሕግ ማውጣትና ማፈረስ ባህርይ፤ ሕጋዊ አይደላችሁም ብሎ አንዳንዶቹን እንዳይወዳደሩ፤ ሌሎችን ደግሞ ሰርጎ በመግባት የሱ ተቀጥላዎች እንዲሆኑ እየኮለኮላቸው ነው። ይህ ሁሉ ድካሙ የሚያሳየው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ምን ያህል የኢትዮጵያን ሕዝብና ምርጫውን እንደሚፈራ ነው። ባለፈው ጊዜ ምርጫውን 99.6% አቸነፍኩ ያለ ፓርቲ፣ የሀገሪቱን ገንዘብ፣ መንግሥታዊ መዋቅርና የሰው ኃይል በሙሉ ለራሱ ምርጫ ያዋለ ፓርቲ፣ የምርጫ ቦርዱን በቁጥጥሩ ሥር ያደረገ ፓርቲ፣ ለምን ተወዳዳሪዎቹን እና ምርጫውን ይፈራዋል። ግልጽ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እምነት የለውም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ታጋዮች ደግሞ፤ አሁንም በሰላም መንገድ፤ ከመቼውም የበለጠ በመጠናከር፤ በገዥው ፓርቲ ፍላጎትና ሕገ-ደንብ ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ቆራጥነት ትግላቸውን ወደፊት ይገፉታል።

በሰላማዊ ትግል የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሥልጣኑን ወዶ አይለቅምና በትጥቅ ትግል እንዝመትበት ለሚሉት፤ ይሄ በር አይከፍትም። የትጥቅ ትግል የራሱ የሆነ ሁኔታዎች አሉት። ይልቁንም ያሁኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መደናበር፤ ምን ያህል የሰላማዊውን ትግል እንደሚፈራውና እንዳይካሄድ ያለ የሌለ ጉልበቱን እንደሚያፈስበት ያስረዳናል። ለምን ብንል፤ የሕዝብ ድጋፍ የሌለው ስለሆነ ነው። የሕዝቡ ድጋፍ ከታጋዮች ጋር ነው። የሕዝቡ ድጋፍ ከሰላማዊ ታጋዮች በሆነበት ቦታ፤ ሰላማዊ ትግሉ ያብባል። ያድጋል። ይጎለብታል። የይስሙላ ግደባዎች አያቆሙትም። ጊዜያዊ አጥሮች የሚያዘገዩት አጥሮቹን እስኪያፈርሳቸው ድረስ ብቻ ነው። ሰላማዊ ታጋይ ድርጅቶች በምርጫዎች መሳተፍ አለባቸው። የሚሳተፉት ምርጫውን በመጠቀም ለሕዝቡ መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ፣ ምርጫው ምን ያህል ውሸት እንደሆነ ለማሳየት፣ ለሕዝቡ የትግል ተሳትፎ በር ለማስፋትና ለማሳደግ እንጂ፣ የፓርላማ ወንበር አሟቂዎችን ቁጥር ለማብዛት አይደለም። ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚመራው በፓርላማው ሳይሆን፤ በጀርባው ባስቀመጠው የጉልበት መዋቅሩ ነው።

በዚህ አሁን በሙሉ ኃይሉ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ ትግል ያገኘነው ዋናው ትምህርት፤ ይህ ትግል፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት በማድረግ በኩል፤ የሚሳካው፤ መላ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት፤ በአንድ የትግል ማዕከል በሚመራ ትግል እንጂ፤ በተናጠል በሚደረግ ትግል አለመሆኑን ነው። መፍትሔ ለማምጣት በአንድነት መሰባሰብ፣ በአንድ ራዕይ መነሳትና መታገል ግድ መሆኑ ተስመረበት። ይህ እልል ያስብላል፤ ልንጠቀምበት ከቻልን።

በዚህ እየተደረገ ባለው ሰላማዊ ትግል፤ አንድ ዋና የኢትዮጵያዊያን ጠላት መኖሩን ተማርንበት። ትግሉ የሚያተኩረው የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣኑ ባለቤት ለማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋናው ጠላት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ብቻ ነው። ሥልጣኑ በኢትዮጵያ ሕዝብ እጅ እንዲሆን፤ መላ ታጋዮች ባንድነት መታገል ያለባቸው መሆኑን ሁላችን እናውቃለን። እንዳይሰባሰቡ እስካሁን ያገዳቸው ምንም ሆን ምንም፤ አሁን ካሉበት ወጥተው ወደ ስብስቡ እንዲቀርቡ መንገዱ ግልጽ፣ በሩ ክፍት ሆኗል።

የታጋዮች ወደ አንድ መጠቃለልና ከድርጅቶች ሕልውና ይልቅ የሀገር ጉዳይ ቅድሚያ ማግኘቱ፤ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊት ልብ እንደሚያንኳኳ ጥያቄ አያስፈልገውም። በሩጫ የመጀመሪያው አባል ለመሆን ግን የሚቀድመኝ እንዳይኖር ተዘጋጅቻለሁ። በርግጥ ብዙ እጅግ ብዙ ከኔ በፊት አባል ለመሆን እንደሚሽቀዳደሙ ጥርጥር የለኝም። ሁላችንም እልል እንበልና ለሩጫው እንዘጋጅ። እኔ ጫማዬን አጥልቄያለሁ። eske.meche@yahoo.com በሉ የዚህ ስብስብ ድርጅት አባል አብረን እንሁን።

አንዱዓለም ተፈራ

ተጨማሪ ጽሁፎችን በአቶ አንዱ ዓለም ተፈራ ብሎግ ላይ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule