• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች

September 22, 2013 05:15 am by Editor Leave a Comment

ክፍል አንድ

የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል። ሰለዚኽ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪው እና ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቱ ሲድኒ ታይ (Sidney Tai) ከቻይንኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተረጎመው። የእንግሊዘኛ ትርጉሙን “በማጭበርበር መግዛት” (“Rule by Tricks”) የሚል ርዕስ ሰጠው እና ሰላማዊ ቅጣቶች (Nonviolent Sanctions) በሚል ርዕስ የአልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም በሚያትማት ጋዜጣ ላይ አሳተመው ሲድኒ ታይ (Sidney Tai)። የዝንጀሮዎቹ ቅጣት ሰላማዊ ቅጣት እንደነበር እና የዝንጀሮዎቹ ጌታ ቅጣት ግን የኃይል ቅጣት (Violent Sanction) እንደነበር ወደፊት ከቦታው ስንደርስ እናስተውላለን። በቅርብ ደግሞ ጂን ሻርፕ (Gene Sharp) የተባለው ሌላው የዘመናችን የሰላማዊ ትግል ተመራማሪ እና በካምብሪጅ ዩንቨርስቲ መምህር ይኽን አጭር ታሪክ ከአምባገነን ወደ ዲሞክራሲ በሚለው መጽሐፉ ገጽ 17-18 ላይ ሰላማዊ ትብብር የመንፈግ ትግል (Nonviolent Non-cooperation Struggle) የሚለውን የሰላማዊ ትግል ጽንሰ አሳብ ለማብራራት ተጠቅሞበታል። የዚህ ጽሑፍ ግብ በዚህ አጭር ታሪክ አንባቢዎች እየተዝናኑ እንዲመራመሩ ማድረግ ነው። ይኽ ምርምር በቅርብ ለንባብ ለማቀርበው ጽሑፍ መሰረት ይጥላል የሚል እምነት አለኝ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

ክፍል ሁለት፡

በክፍል አንድ እንዳነበብነው የዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ ተርቦ ከመሞቱ በፊት የሚቀልቡት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ነበሩት። የፖለቲካ ኃይል ምንጮቹ መድረቅ ተርቦ እንዲሞት አድርገውታል። እንደ ዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ መንግስትም የፖለቲካ ኃይል ምንጮች አሉት። የአንድ መንግስት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ከሞላ ጎደል የሚከተሉትን ያካትታል። (1) መንግስት ከህዝብ የሚያገኘው የገዢነት ክብር፣ ህጋዊነት፣ (2) መንግስት ከቢሮክራሲው (ከመንግስት ሰራተኞች) የሚያገኘው ትብብር መጠን፣ (3) መንግስት ከሙያተኞች የሚያገኘው የቴክኖሎጂ ክህሎት እና ፕላን የማቀድ፣ የማስተዳደር እና የመሳሰለው ዕውቀት ትብብር፣ (4) የመንግስት የአገር ኢኮኖሚ (የተፈጥሮ ሃብት፣ የገንዘብ፣ የኢንዱስትሪ፣ የእርሻ፣ የንግድ፣ የትራንስፖርት፣ የኮምኒኬሽን) ባለቤትነት፣ (5) በመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙ መሪዎች በሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም ወይንም በጎሳ ማንነታቸው የሚያገኙት የተወሰነ ህዝብ ክፍል ድጋፍ፣ (6) በመጨቆኛ እና በመቅጫ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ፖሊስ፣ ደህንነት እና የጦር ኃይል ለመንግስት የሚለግሰው ትብብር። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule