• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የህዝብ ደም የፖለቲካ ፀበል አይደለም!

June 15, 2016 02:04 am by Editor 4 Comments

ዱሮ እረኞች በነበርንበት ጊዜ ታላላቆቻችን ይሰበሰቡና እኛን ታናናሾቻቸውንን ጠርተው እርስ በርሳችን ትግል እንድንጋጠምና አሸናፊውም ከዛ ቀን ጀምሮ ላሸናፊው አለቃና አዛዥ እንዲሆን ያደርጉት ነበር፤ ውድድሩ አንዳንድ ጊዜ ከዚህም የከፋ መልክ ነበረው። ተወዳዳሪዎች መደባደሚያ ዥልጥ (የዛፍ ግንጣይ ማለት ነው) ይሰጣቸውና ጎረምሶቹ በተሰበሰቡበት እንዲደባደቡ ይደረጋል። ተጋጣሚዎቹም በፍርሃትና ባልሸነፍም እልህ ከአይንና ጥርስ በቀር አካል ሳይመርጡ ይናረታሉ። ጎረምሶቹ (ባካባቢው አጠራር ውርጋጦቹ) በሳቅ እየተንፈራፈሩ ትርኢቱን በደስታ ይመለከታሉ። ተጋጣሚ ታዳጊዎች ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ስሜት እርስ በእርሳቸው ክፉኛ ይጨፋጨፋሉ። እጅግ የሚያሳዝን ትእይንት ነው። በመጨረሻም አቅም ያነሰውን ተጋጣሚ አሸናፊው፥ እመን፥ እያለ ያለርኽራኼ ይቀጠቅጠዋል። ተሸናፊውም ዱላ እያለቀሰ፥ በቃ አመኛለሁ፥ ይላል። ከዛ ቀን ጀምሮ ጉልቤው በተሸናፊው ላይ አዛዥ ይሆናል።

ብዙውን ጊዜ በታላላቆቻቸው አስገዳጅነት የሚደባደቡት ታዳጊዎች በጣም የሚዋደዱ ባልንጀሮች ስለሆኑ ከግጥሚያው በኋላ፥ ያጣሉን እኮ እነርሱ ናቸው። እኔ አንተን ልመታህና ልጣላህ አልፈልግም፥ ይባባላሉ። ወዲያውም ዘመኑ ያዝመራ ወቅት ከሆነ ባተር ወይም በስንዴ እንኩቶ ይታረቃሉ። “እንኩቶ” ያተሩ ወይም የስንዴው እሸት ከተነቀለ በኋላ ከዱር በሚሰበሰብ ማገዶ ዛፍ ስር በሚላማ እሳት እሸቱን ከነቁሪንባው ወይም እንቡጡንና ተክሉ ከነፍሬው እንደምንጣሮ በማያያዝ እንዲበስል በማድረግ እየታሸ የሚበላ ጣእሙ ደስ የሚል የእሸት ቆሎ ነው። በዝግጅቱ ሂደት እረኞች ግማሹ እሸት፤ ግማሹ ማገዶ ቀሪው ደግሞ እሳት በማምጣት የሚሳተፉበት የህብረት ስራ ነው። ታዲያ በጎረምሶች አስገዳጅነት የተደባደቡም ሆነ በሌላ ምክንያት የተኳረፉ እረኞች የሚታረቁት በዚህ አጋጣሚ ነው። በታላላቆቻቸው ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ሳይፈልጉ የተቀያየሙት ባልንጀሮችና አብሮአደጎች በእንኩቶ ዙሪያ ታድመው ፍቅራቸውን ያድሳሉ። ቀድሞውንም የተጣሉት ተገደው እንጂ በእርግጥም ጠላትነት በውስጣቸው አድሮና ሊጎዳዱ አስበው አልነበረምና ሌሎች በሸረቡት ሴራ ወንድማማችነታቸው እንዲፈርስ አይፈቅዱም።

የረኝነት ዘመኔን ክፉና ደግ ትውስታ የቀሰቀሰብኝ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሽፍታ መንግስታት ሰሞኑን መደለቅ የጀመሩት የጦርነት ከበሮ ድምፅ ነው። እነዚህ መንግስት ተብዬ ቡድኖች በየግላቸው ስውር አጀንዳና ጠባብ የቡድን ጥቅም ወንድማማቹን የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ ዳግም ደም ሊያቃቡ ቡራ ከረዩ ሲሉ በመስማት እረፍት የሚነሳ ብቻ ሳይሆን ህሊና የሚያደማ ክፉ ድርጊtት ነው። ይህ በደምና ባጥንት የተሳሰረና ምኑም ከምኑ የማይለያይ ህዝብ በፊት በደርግ በኋላ ደግሞ በነዚሁ ያዲስ አበባና ያስመራ ጉደኛ ቡድኖች ደም እንዲፋሰስ መደረጉ ሳያንስ አሁን ደግሞ ለሌላ ዙር የእርስ በእርስ እልቂት ሲያዘጋጁት ማየት በእጅጉ ያንገበግባል። ከጦርነትና አፈና ውጪ ህልውና የሌላቸው ቡድኖች ዛሬም ከዛ ሁሉ መከራ በኋላ እንኳን በናፍቆት የሚተያየውን ህዝብ ለየግል የፖለቲካ ግባቸው ጭዳ ሊያደርጉት ራሱ በከፈለው ግብር የሸመቱትን ጠመንጃ እያጎረሱ ነው። ይህን እኩይ ተግባር ማንኛውም ወገን በቸልተኝነት ሊመለከተው ጨርሶ አይገባም። እናም ለሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ ወገናዊ ጥሪ አለኝ።

ወንድማማች ለሆንከው የኢትዮጵያና ኤርትራ ሰራዊት!

ዱሮም ቢሆን በወንድምህ ላይ ክንድህን ክንድህን የምታነሳበት በቂ ምክንያት አልነበረህም። አለቆችህ በፈጠሩት ያገር ተደፈረ ማጭበርበሪያ ጩኸት ያለአግባብ ተላልቀሃል። በከንቱ በዚያ አሳዛኝና ከንቱ ጦርነት ያለቁትን ከ70000 በላይ ወንድምና እህቶችህን አስብ። ካሳዛኙ የሰው ህይወትና ንብረት ኪሳራ ሌላ የተገኘ ምንን አይነት ትርፍ እንዳልነበረ አስታውስ። እናም በወንድምህ ላይ ክንድህን አታንሳ። ያለፈው ስህተት ሳይታረም ሌላ የታሪክ ስህተት እንዲፈፀም ተባባሪ አትሁን። በዘረኞችና የስልጣን ጥመኞች ሴራ ለሩብ ዘመን ተለያይቶ የነበረው ወንድማማች ህዝብ ለዘለአለም ተቆራርጦ እንዲቀር ባዲስ መልክ ለተወጠነው ሸር ስኬት መሳሪያ አትሁን።

የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በያለህበት!

የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ እንዲለያይ እንዳልተፈጠረ ልብህ ያውቀዋል። እስካሁን የተካሄዱት ጦርነቶች የገዢዎች እንጂ የህዝብ ጦርነቶች እንዳልነበሩም አሳምረህ ታውቀዋለህ። የእስከዛሬ ግጭቶች ገዢ ቡድኖች ስውር ስሌት የተፈጠሩ እንጂ የህዝብ ቁርሾዎች እንዳልነበሩ ገኻድ ነው። ከዛ ሁሉ እልቂት በኋላ እንኳን ሁለቱ ህዝቦች ቂም ሳይዙ በየአጋጣሚው ለመቀራረብና ለመፈቃቀድ ሲጥሩ መመልከት በልባቸው ተዳፍኖ ላለው ፍቅር ማሳያ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። በመሆኑም በገዢዎች ሴራና የተሳሳተ ፖሊሲ የተበላሸውን ህንኙነት ጠግኖ አዲስ የግንኙነት ታሪክ ለመገንባት ጥረት በሚደረግበት ባሁኑ ወቅት በህዝብ ደም የሚያተርፉ ቡድኖች በጠነሰሱት አዲስ ሰይጣናዊ እቅድ ህዝብ ዳግም ደም ሲፋሰስ በዝምታ መመልከት አይኖርብህም።

ለህዝብ ደም ደንታ የሌላቸው እነዚህ ጦረኛ መንግስታት በሰላም አደባባይ ያጡትን የፖለቲካ ትርፍ በጦር ሜዳ ለመሸመት የሚያደርጉትን ሸብረብ ማስቆም አለብህ። በውስጥና ውጪ ያለኸው ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ሁሉ እነዚህን የጥፋት መንግስታት በቃችሁ ልትላቸው ይገባል። አሁን ለፍቅር እንጂ ለጦርነት የተዘጋጀ ልብ የለንም ሊባሉ ይገባል። እናም በተገኘውአጋጣሚ ሁሉ ይህን አዲስ የጥፋት ጦርነት ዝግጅት ማስቆም አለብህ። ገዢዎች እንዲያተርፉ ህዝብ መክሰር የለበትም። ህዝብ ለህዝብ ፍቅር እንጂ ለቡድኖች ደህንነት የሚከፍለው መስዋእትነት ሊኖር አይገባም። ትርጉም በሌለው ጦርነት የማገዷቸው ታዳጊ ልጆች ሀዘን ሳይወጣልህ ዳግም የምትከፍለው የደም ግብር ሊኖር አይገባም።

በመሆኑም ወንድማማች በሆነው ህዝብ ላይ የፈጸሙት የታሪክ ነውር ሳያሳፍራቸው ዳግም የመዘዙትን  የጥፋት ሰይፍ ወደአፎቱ እንዲመልሱ መገደድ አለባቸው። በሁለቱ ህዝቦች ጠንካራ ትግል ጥፋቱ ባስቸኳይ መቆም አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቸልተኝነት አጥፊ ቡድኖቹ በጀመሩት የጥፋት መንገድ ገፍተው ዳግመኛ ንፁሃን እንዲያልቁ የምንፈቅድ ከሆነ ግን እንደ ቡድን ሳይሆን እንደህዝብ ታላቅ ስህተት በድጋሚ እንዲፈፀም መስማማታችን ስለሆነ ለትውልድ የሚዘልቅ ፀፀት አትርፈን የምናልፍ መሆናችንን ልብ ልንል ይገባል።

የህዝብ አምላክ ወንድማማች ህዝቦችን ይጠብቅ!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. eunetu says

    June 16, 2016 04:28 am at 4:28 am

    ለአቶ ህሩይ፡
    ባሉበት

    ሰማያዊ /እውነተኛው/ ሰላም ይብዛልዎ!

    ከጽሁፉ /የሁለቱ ወንድማማቾች/ ዋና መልእክት ባሻገር ያንን የገጠር የእረኝነት ውበት በትክክለኛው የአማርኛ አገላለጽ በማቅረብዎ ልዩ የሆነ ትዝታየን ነው የቀሰቀሱት። የእራሱን ስር መሰረት/አስተዳደግ/ በራሱ ተማምኖ ከመግለጽ ይልቅ በአብዛኛው እራሱን ከሚደብቅ ሕዝብ መካከል በትናንት ማንነቱ የማያፍርና በራሱ የሚተማመን እንደ እርስዎ ያለ ግልጽና እውነተኛ ሰው ማየቴን እንደ ልዩ መታደል ነው የቆጠርኩት። ኧረ ብዙልን!የቦሌ ልጆች መስሎ ለመታየት የአማርኛ ንግግራቸውን ለመቀየር ሲሉ ከናፍራቸውን የሚያጣምሙ ሰዎች አሉና፤ በራስ ማንነት ያለመተማመን በሽታ!!!

    ፈጣሪ በገጠርና በከተማ በተለያየ አቅምና ችሎታ ከእየነገዱ ሁላችንንም ውብ አድርጎ የሠራን መሆናችንን የማናውቅ ከሆነ በልዩነት/በበላይና በበታችነት/ስሜት ተሞልተን ወደ ማይጠቅም ከንቱ ውድድር ውስጥ መግባትና በመካከላችን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ለመግባት እንገደዳለን፤ እርስዎ የፈሩት ‘የሁለቱ’ ሕዝቦች ጉዳይም በጽሁፍዎ ከጠቀሱት የመሪዎች ችግር እንዳለ ሆኖ ማንነትን ያለማዎቅም ላለመስማማታችን ተጨማሪ በሽታችን ነው። መድሃኒቱ ደግሞ እያንዳንዳችን ውብና ጠቃሚ ሆነን እንደተሠራን ማዎቅና አመኖ መቀበል ነው።

    ማንነቱን የማያውቅ ሰው የሚሠራውንም ሥራ አያውቅም!
    እረኛ ነበርኩ ብሎ ስለትናንትና ማንነቱ
    የሚያወራ ምሑር እንዲህ መገኘቱ
    ጥሩ ምሳሌነት ነው ለእኔ በእውነቱ
    ያልሆነውን ነን፤
    የሆነውን አይደለንም ማለቱ
    መሆን ነውና የከንቱ ከንቱ
    እንንቃ ሳይመሽ በጠዋቱ
    እንደገና ሳይመጣ ጦርነቱ
    በእነዚህ ሕዝቦች በሁለቱ???

    እውነቱ ይነገር ነኝ
    ከአለሁበት
    ዐ

    Reply
  2. tesfai habte says

    June 18, 2016 09:04 am at 9:04 am

    እና ወደ ኢትዮጵያ ሂደን ተዋግተን ኣናውቅም። ሁሌ ውግያውን የሚመጣው ከጎሮቤት ኢትዮጵያ ነው። ለኣመሪካኖችና ለማስደሰትና ዶላርን ለማግኘት ሲባል ሁሉ ግዜ ኢትዮጵያን ለጎሮቤት ኣገራች ለሱማል፡ ለሰዳን፡ ለኬንያ፡ ታስቸግራለች። የኢትዮጵያ ህዝብ ለኣመሪካ ኢንተረስት ለመፈጸም ሲባል የኢትዮጵያ ልቾች ለመስዋእትነት ይደረጋሉ።

    Reply
    • tesfai habte says

      June 19, 2016 10:19 am at 10:19 am

      የኢትዮጵያ መሪዎች ለዶላር ሲሉ፡ በደርግ ግዜ ሰውን ፈላሽ እያሉ ለኢስራኤልን ይሸጡ ነበር። በሃጸይ ሃይለ ስላሴ ግዜም ከምዕራቡ ኣገሮች ዶላር ለማግኘት የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ኮርያ እና ኮንጎ ኣገሮች ዘመተ። ዛሬም ወደ ደቡብ ሱዳን ሶማል ኣገሮች ሄደዋል። የኣሁኑ ብኣንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች እንደመግደል፡ ወያኔዎች ብኣንድ በኩል ሌላ ብሄሮች ለማጥፋት ሲሆን፡ በሌላ በኩል ደግማ ዶላርን ለማግኘት ነው። ባለፈው ሳምንት በኤርትራ የተፈጸመው ጥቃት፡ ብኣመሬካን የተደገፈ ዶላር ለማግኘት ነው። ይህ ዶላር ከባንክ ብኢትዮጵያ ስም ሲወጣ የኣማሪካ ማፍያዊች ግን 75 በሞቶ እዛው ለኣመሪካ ፖሎቲከኞች አንደ ጉርሻ ይሰጣል። ሻእብያዎች (ህዝባዊ) ግን ለኢትዮጵያ ተብሎ በትሪሌን የሚቆጥረ ብረታ ብረት የተገዛ እየማረከ ነው። ሄሊኮፕተርን ጭምር። በኤርትራ መሬት ከኢትዮጵያ የተማረክ ታንኮች እና መድፍ መሬቱ ኣጨናንቀዋል። sanction ፋይዳ የሌለው በዚህ ምክንያት ነው።

      Reply
  3. gud says

    June 19, 2016 06:48 pm at 6:48 pm

    No amount of cry ,call or propoganda support will save Shabia from what is planned against it !

    Call shabian members in Asmara

    Run ,run for your cheap life ,…run

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule