የአፈና ግዜ አዋጁን ተከትሎ፤ የሕወሃቱ ፋና ብሮድካስቲንግ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያስተናገደው “የውይይት መድረክ” አዳዲስ ኩምክናዎችን ይዟል። ልደቱ አያሌውን በመሪ ተዋናይነት ያሳተፈውን ይህን አዲስ የበረከት ስምኦን ድራማ ብዙም ሰው አላየውም። ሕዝቡ ፋና ሚባል ነገር እንደሬት መርሮታል።
ገሚሶች ደግሞ በ”ቃና”ው “ጥቁር ፍቅር” ድራማ ተጠምደዋል። በዚህ ድራማ ልደቱ አያሌው መሪ ገጸ-ባህሪይ ተላብሶ ይተውን እንጂ እንደወትሮው ቀልብ ሊስብ አልቻለም። በኢትዮጵያ ታሪክ ወያኔ መድብለ ፖርቲን የፈቀደ ድርጅት እንደሆነ በሙሉ አፉ ሲናገር እሱ አላፈረም። ከሱ ይልቅ የተሸማቀቁት እነ በረከት እና ስብሃት ናቸው። በልባቸው አበስኩ ገበርኩ እያሉ … ጌታዎቹ ሃዘን ሲሰማቸው እሱ ያለቅሳል። በዚህ አቋሙ ከሶስተኛው መንገድ ወደ አንደኛው የተሸጋገረ ይመስላል ልደቱ። ለነገሩ እንጂ ለሱ መገለባበጥ አዲስ ጉዳይ አይደለም!
ልደቱ አያሌው ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት ወደ ልማታዊ ባለሃብት እንደገባ ነበር የምናውቀው – የሃብቱ ምንጩ ግልጽ ባይሆንም። እንደ ፕ/ር ኤፍሬም ይሳቅ የሕወሃት የመከራ ጊዜ ደራሽ እና አስተንፋሽ ለመሆን መጣሩ አይደንቅም። ሕዝባዊ አመጹን ማውገዙ ግን ከሃይለኛ ማእበል ጋር አላትሞታል። “ጥናታዊ ጽሁፍ” ያቀረበው የአስታራቂነትን ሚና ለመጫወት ከሆነም ማስታረቅ፣ የተበደለን ሕዝብ እየኮነኑ አይደለም። ህወሃት ሕዝብን በጅምላ ገድሏል። አንዴ የተገደለውን ሕዝብ ደግሞ መግደል ምን ይሉታል? መጨረሻውን ፈጣሪ ያሳምርለት።
የዚህ ውይይት አላማ ግልጽ ነው። ችግሩን ከመፍታት ይልቅ በግብጽ እና ሻእቢያ ላይ ጣት ማውጣቱ ያዋጣቸው አልመሰለም። ስለዚህ የተወጠረውን ለማስተንፈስ፣ የተለመደ አቅጣጫ ማስቀየስ፣ እና ሕዝብን ለማዘናጋት መሞከር ከመጣር አልተኙም። በውይይቱ የተገኙትም አይነት ብዙ ናቸው። ጉዳዩ የገባቸው፣ ጉዳዩ ያልገባቸው እና ግራ የገባቸው ሰዎች ተሳትፈዋል።
ሃይሌ ገብረስላሴ እና ሳምሶን ማሞ የነበረከት ደባ በደንብ ከገባቸው ተሳታፊዎች ዋነኞቹ ናቸው። የኢትዮጵያ ችግር በውይይቱ እጅግ ተጋንኖ እንደቀረበ በቀልድ እያዋዛ ተናገረ ሃይሌ። አንዴ ተኑሮ ለሚታለፍባት አለም እንዲህ አጎብዳጅ መሆን ለምን እንዳስፈለገ አይገባኝም። የማያልፍ ነገር የለም። ይህ ስርዓትም በእርግጠኝነት ያልፋል። እንደ ሃይሌ እና ቀነኒሳ ያሉ አድርባዮች ይህ ያከበራቸው ህዝብን ነገ እንዴት ቀና ብለው እንደሚመለከቱት ወደፊት የምናየው ይሆናል። በፈጣሪ አምሳል የተሰራን ሰው አትግደሉ ብሎ የመናገር ሞራል ከሌላቸው፣ ዝምታም እኮ መፍትሄ እንኳን ባይሆን አማራጭ ነበር። ዝምታ ወርቅ ነው። እነሱ ግን እንደበቀቀን ህወሃቶች የሚሉትን የ”መልካም መስተዳደር” አሲዮ ቤሌማ ደጋግመው ይዘፍኑልናል።
ሳምሶን ማሞ ሲናገር የክበበው ገዳን አዲስ ቀልድ ያስታውሳል።
በአሜሪካ ሃገር ዋይት ሃውስ በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” እያልክ ብትውል የሚነካህ የለም። ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተ መንግስት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል? ብሎ ነበር ክበበው ገዳ።
“እኔ አቶ በረከት ስምዖን ቢሮ ገብቼ እንደፈለኩ ተሳድቤ እወጣለሁ። ይህንን ያህል ነፃነት አለ።” ይለናል ይህ የስርዓቱ ተደጋፊ ሳምሶን ሞሞ። አዎ ይህ ሰው ይሳደባል። አቶ በረከትን ቢሮ ድረድ ሄዶ ተሳድቦ ቢሆን ኖሮ ግን 34 ጥርሶቹን አናያቸውም ነበር። ደፋሩ ሳምሶን ባለፈው ሳምንትም በዚሁ መድረክ ላይ ቀርቦ ሕዝብን በጅምላ ተሳድቧል። አቶ በረከትን ሊሳደብ እንደማይችል ግን ሕጻን ልጅም ይገምታል። የሚደንቀው ታዲያ በስድብ እና በመብት መካከል ያለውን ልዩነት እንኳን አጥርቶ የማያውቅ ይህ ሰው መድረኩን ይዞት ሲቀልድ ማየቱ ነው። እርግጥ ነው። ዝሆን ላይ የሚጮህ ሞኝ ውሻ ብቻ ነው። ሆድ ከፊት ለመሰለፍ አይፈራም ይሉ የለ አፍሪካውያን።
ሕዝብ መሬት ላይ ነው። እነሱ ሰማይ ላይ። መሬት ላይ የተኛ ግዜው እስኪያልፍ ሊረጋገጥ ይችላል። መሬት ላይ የተኛ እወድቃለሁ ብሎ አይሰጋም። ዛሬ ሰማይ ላይ ያሉት ግን እዚያው አይቀሩም። ነገ መውረዳቸው የተፈጥሮም ህግ ነው።
የመለስ ዜናዊ ልጅ ሰምሃል መለስ ግራ የተጋባች ተሳታፊ ትመስላለች። ግን አጠር ብላ የረዘመች መልእክት አላት። በህወሃት ውስጥ ያለውን የስልጣን ሽኩቻ ብቻ ሹክ ብላ አላለፈችም። ስልጣንችሁን ላለማስነካት ከምትንደፋደፉ ስልጣኑን ለኛ ስጡን ብላለች።
አባትዋ ከማለፉ በፊት ስለመተካካት ብዙ ተናግሮ ነበር። ሰምሃል ይህንኑ ቃል እንደ ፈጣሪ ቃል አምና ተቀብላለች። ይህ ብቻ አይደለም። የህወሃት ስልጣን እንደ ርስትና ጉልት በውርስ እየተላለፈ ይቆያል ተብሎም ተነግሯታል። ጸጉርዋን የሽፍታ አስመስላ ስልጣኑን ከነበረከት ለመቀበል ብዙ የጠበቀች ነው የሚመስለው። በዚያ ሰሞን ጠመንጃ ይዛ የቶክስ ልምምድ ስታደርግ የተነሳችው ፎቶም ተለቆ ነበር። ይህም በህወሃት መመዘኛ ከርክክብ ቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ መሆኑ ነው።
የመተካካት እና የቅብብሎሹ ወሬ ከአቶ መለስ ጋር ተቀብሮ በጥልቅ ተሃድሶ አዲስ ዜማ መተካቱን ግን ሰምሃል የሰማች አይመስልም። ይህች ወጣት ስብሰባው ላይ የተሳተፈችው የእናቷ አዜብ ጎላን ሃሜት ይዛ ነው የሚለው ንግግራቸው የሚያስኬድ ቢሆንም፤ መልእክትዋ ግን ግልጽ ነው። እስዋም ገና የለውጥ ሳይሆን የጥገና መፍትሄ ላይ ናት።
እንደ ሰምሃል ነገሮችን ሳያላምጡ እየዋጡ፣ ቅዠት ሁሉ ህልም መስሎ እየታያቸው፤ ሕወሃትን እንደ ንጉሳዊ ስርዓት ለማስቀጠል የሚፈልጉ ደፋሮች ጥቂት አይደሉም።
ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ኢንጅነር ይልቃል በዚህ ስብስብ የተሳተፉበት ምክንያት ግን አልገባኝም። ድራማውን ለማሟሟቅ ካልሆነ በስተቀር የእነሱ በዚያ መገኘት ፋይዳ አይታይም። እርግጥ ነው ሁላችንም ይህንን ውይይት እንድንመለከት ያደረገን የእነሱ መሳተፍ ነበር። ግና ከምርጫ ክርክር ግዜ የተናገሩትን ያህል እንኳን በዚህ ውይይት ሲናገሩ አልሰማንም። እነሱ እዚህ እያወሩ ባሉበት ቅጽበት አጋዚ ጦር በጠራራ ጸሃይ የቤት ለቤት ዘረፋ፣ አፈና እና አስገድዶ መድፈር ላይ ተሰማርቷል። ከውይይቱ በፊት – እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቅድመ ሁነታዎችን ማስቀመጥ ነበረባቸው።
ሕዝብ ጥገና ወይንም ተሃድሶ ሳይሆን ለውጥ ነው የፈለገው። ሕወሃት፣ የማይታደስ፣ የማይሻሻል፣ ከስህተት የማይማር እንደሆነ ብዙ ግዜ ነግረውናል። ጅምላ ግድያ እየፈጸመ ካለ ከዚህ ስርዓት ጋር ቁጭ ብለው ዲስኩር ማድረግ ምን ሊጠቅም እንደሚችል ከእኛ በላይ እነሱ ያውቁታል። ሕዝብ እና ሕወሃት የማይታረቅ ቅራኔ በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ እነሱ ራሳቸው የውይይት ግዜ አብቅቷል ሲሉ የሰማን መስሎኝ ነበር። በረከት ስምኦን እና ልደቱ “ብቃት ያለው ተቃዋሚ ልንፈጥር አልቻልንም” የሚሉን ይህንን እያስተዋሉ ይሆን?
አቦይ ስብሃት እንደተባለው ቀምቅመው መድረክ ላይ ይውጡ እንጂ፣ የሚናገሩት ሁሉ ቅኔ አዘል ነበር። ሰምና ወርቅ ያለው ቅኔ። “መረራ እና ይልቃል ጓደኛሞች ናቸው። የፖለቲካ ፓርቲ አይደሉም!” ያሉት ያለምክንያት አልነበረም። ያንን ሁሉ ተናግራችሁ ስታበቁ እዚህ በኛ ጉባኤ ላይ ምን ትሰራላችሁ? ማለታቸው ይመስላል። ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ ሕወሃት ለፍትህ እንጂ ለድርድር እና ለውይይት የሚቀርብ ስርዓት እንዳልሆነ ነው የቅኔው ወርቅ የሚጠቁመን። የህወሃት መክሠም እና መጥፋት ምኞታቸው መሆኑን የማብሰራቸው ቅኔ ግን ሰምም ሆነ ወርቅ የለውም።
ሽማግሌው ስብሃት ቀጠሉ “እናንተ ሕዝቡን አታውቁትም። እኛ እንኳን ግማሹን የኢትዮጵያ ሕዝብ አናውቀውም!” ብለው አረፉ። የማያውቁትን ሕዝብ ለ 25 አመት የሙጥኝ ይዘውት ኖሯል።
“ከፊትህ የሚጠብቅህን መንገድ ለማወቅ ተመላሾቹን ጠይቅ” ይላሉ ቻይናውያን። ላስተዋለው ትልቅ አባባል ነበር። ለተመክሮውም የደርግ ውድቀት ብቻ በቂ ነው። እነሱ ግን ከታገሉት ደርግ በመቶ እጥፍ ብሰው ተገኙ። ወትሮውን ቁጭ ያሉበት መጥበሻ ሲግል እንደማሽላ መፈንዳት ግድ ነውና እስከመጨረሻው እስትንፋሳቸው ይናገራሉ። እኛም እንደ ኮሶ እያንገሻገሸን የሚሉትን መስማቱን አልተውንም።
… በሚቀጥለው ጽሁፌ ስለ አፈና ግዜ አዋጁ እና ስለ አጋዚ አ የምለው አለኝ። እስከዚያው ቸር እንሰንብት።
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
በለው! says
“የውይይት መድረክ” አዳዲስ ኩምክናዎች:
1) የበረከት ስምኦን ድራማ “ገበሬው የእኛ ነው ከኢአዴግ ውጭ ማንም ለውጥ እንደማያመጣ ያውቃል ስለዚህ 80 ከመቶ ሕዝብ ተቃዋሚዎችን አይፈልግምና ቦታ የላቸሁም። አልተሳካም! አይሳካም! ሊባሉ ተጠርተውና ተሽቀዳድመው መድረክ መያዛቸው ለምን ይሆን? ለመሆኑ ይህን ተቃውሞ ያሰማው 20 ከመቶው የከተማ ውስጥ ነዋሪ ብቻ ነው? 20 ከመቶ የከተማ ነዋሪ የትውልዱ ሀረግ ገጠር አደለምን? 1983 በኢህአዴግ ተጠፍጥፈው ከተፈጠሩት ሀገርና ሕዝቦች ውጭ ትውልዱን የዘር ሀረግ፤ ታሪክና ሉዓላዊነት ያልነበራት ሀገር አድርጎ የማቅረብና ትውልድ የማሸበር አባዜን ለመሸፋፈንም ስለኢትዮጵያም ታላቅ ሀገርነት ለመግልጽ ሲቃትቱ ተደምጠዋል፡ግን ይህ ሁሉ ቱማታ አሁን ሀገሪቱ ከተዘፈቀችበት የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ፤ የጎጥና የዘርኝነት ምስቅልቅል የማዳን ሳይሆን የማባባስ ብስብስነት እንጂ ከሥህተቱ የተማረ ወይንም ለመማር የፈለገ በሳል ሥርዓት ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው። ለምን ? ሲተከል ተጣሟልና።
2) ልደቱ አያሌው ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት ወደ ልማታዊ ባለሃብት እንደገባ ነበር የምናውቀው – መታጠፍና መተጣጠፍ — ከተቃዋሚ አቋቋሚ (አጋር) ___ወደ ሶስተኛ አማራጭ ፓርቲ ከመጠላላት ፖለቲካ ወደ መደናነቅ ታማኝ ቦለጥቀኛ ከዚያማ ይህን የድሮ ‘ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ’ የአሁን ‘ ቦርቃቃው የኢህአዴግ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአልበላ አንጀታችው የመጽሐፍ ማራገፊያ ማደረጝ ከውስጥም ከውስጥም ቤተ ሙከራ ሆነው ተከልለውና ተከልክለው እንዲኖሩ እንደነዚህ ወዶ ገባ ቦለጥቀኞችን ከፊት ማቆም ኢህአዴግን ሳይበረዝና ሳይሸራረፍ ማስቀጠል ለመኖር የውዴታ ግዴታ ነው። “ዛሬ ያቀረብኩትን ጽሁፌን በጣም ወዳችሁታል ምክንያቱም ተቃዋሚውን በደንብ ስለተቸሁና ስለወቀስኩ (ስላጣጣለኩ) ይላል አቶ ልደቱ ታዲያ ኢህአዴግ አንተን ከአሜሪካ ድርስ እስክትመጣ ለምን ጠብቀ? ሌላ ሰው የለም? ሕዝቡስ ክደቱ አያሌው በዋዛ አለ?
3) በውይይቱ (ክርክሩ፤ድርድሩ፡ማስታረቁ ይሁን ማዋለቁ) የተገኙትም አይነተ ብዙ ናቸው።ታዋቂዎቸ እንጂ አዋቂዎች ለመሆናቸው ማስረጃና መረጃ የለም ግን ጉዳዩ የገባቸው፣ ጉዳዩ ያልገባቸው እና ግራ የገባቸው ሰዎች ነበሩ እንበል ከእነዚህም ‘ሃይሌ ገብረስላሴ እና ሳምሶን ማሞ….” በፈጣሪ አምሳል የተሰራን ሰው አትግደሉ ብሎ የመርናገር ሞራል ከሌላቸው፣ ዝምታም እኮ መፍትሄ እንኳን ባይሆን አማራጭ ነበር። ዝምታ ወርቅ ነው። እነሱ ግን እንደበቀቀን ህወሃቶች የሚሉትን የ”መልካም መስተዳደር” አሲዮ ቤሌማ ደጋግመው ይዘፍኑልናል። ”
4) እንደ ሰምሃል መለስ ዜናዊ ነገሮችን ሳያላምጡ እየዋጡ፣ ቅዠት ሁሉ ህልም መስሎ እየታያቸው፤ ሕወሃትን እንደ ንጉሳዊ ስርዓት ለማስቀጠል የሚፈልጉ ደፋሮች ጥቂት አይደሉም። ይሁንና ትናንት “መልስ ኖረ አልኖረ ፋጡማ (አዜብ) ኖረች አልኖረች ሥራዓት ዘርግተናል ያሉትን ስብሃት ነጋ ” እናነት አዛውንቶች ኖራችሁ አልኖራቸሁ ሥረዓቱ አለና እኛ ሳይበረዝና ሳይከለስ ትግራይን እንዱስትሪ መር ሀገሪቱን ሙስና መር ኢኮኖሚ ራዕይ እናስቀጥለዋለንና ንኩት ማለቷ አሁን ካለው ሕዝባዊ ወዠብ ያድናልን?
5) ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ኢንጅነር ይልቃል በዚህ ስብስብ የተሳተፉበት ምክንያት ግን አልገባኝም። ድራማውን ለማሟሟቅ ከልሆነ በስተቀር የእነሱ በዚያ መገኘት ፋይዳ አይታይም። መቼም እንዲህ ተባለ አሉ ከሚባል ሰምቼ መጣሁ ጥሩ ነው ጆሮአቸውን የበላቸውን ያህል በደንብ አድምጠዋል ምንግዜም አውራው ፓርቲ! ገዢው ፓርቲ! መንግስትና ኢህአዴግ! ከአጋር ፓርቲ የተረፈ በርጩማ በጥሩ አናጢ ይቀረጻል አሉ መድረክ ዳግማዊ ኢህአዴግ ይቀመጥበታል። ምሕዳሩ በነጭ ሰፍቶ ተጫዋቹን በቀይ ካርድ!!
6) አቦይ ስብሃት ነጋ እንደተባለው ቀምቅመው መድረክ ላይ ይውጡ እንጂ፣ “መረራ እና ይልቃል ጓደኛሞች ናቸው። የፖለቲካ ፓሪቲ አይደሉም!” “እናንተ ሕዝቡን አታውቁትም። እኛ እንኳን ግማሹን የኢትዮጵያ ሕዝብ አናውቀውም!” በመሠረቱ ከሞቅታም በላይ ምጥ መኖሩን ያሳያል 80 ከመቶ ገበሬ የደገፈው 100 ከመቶ ፓርላማ የተቆናጠጠ ቡድን የሚመራውን ሕዝብ ማንነት 40 ዓመት ካላወቀ ችግር አለ። በመሠረቱ አቶ ደበላ ዲኒሳ ለቀዳማዊ ኅይለስላሴ ከሥልጣን መልቀቅና ለደህንነታቸው ሲባል ከቤተ መንግስት ሲያስወጧቸው “አሁን ያላችሁትን ከውጭ የለቃቀማችሁትን ሁሉ አድምጠናል እኛም የቻልነውን የሰራን መስሎን ነበር የሕዝብ ፍቃድና ፍላጎት ከሆነ ይሁን ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለማታቁት ነው ይሁንላችሁ” ብለው ነበር ኮ/መንግስቱም ይህንኑ ንግግር ” ትናንት ነጠላውን መሬት አንጥፎ የሚሰግድላቸው ሰፊ ሕዝብ …ስቀለው! በለው! ግደለው! ” ሲል ሥሰማ ነግ በእኔ አልኩ ብለው ነበር ። ታዲያ ስብሃት ነጋ ትናንት የዕርዳታ ንፍሮ በድንኳን እየነፋ … ካኒቴራና ባርኔጣ እየሸቀለ…በጥቅማጥቅም የተያዘው ካድሬ… ልማታዊ ጋዜጠኛና እስፖርተኛ ኢህአዴግ ዙሪያውን ሲለበለብ ሲቃጠል “አይጥ ወልዳ ወልዳ አንድ መቶ ከአምሳ አንድ ልጅ ጠፋ ድፍጥ የሚያነሳ” ነግ በእኔ ማለታቸው አደለምን? አይደንቅም!
7) “ኢህአዴግ ዘላለማዊ ሆኜ እኖራለሁ አላለም እራሴን አጠፋለሁ እያለ ነው” እልል ይህ የከብት ጋጣ (ክልል) ሊጠፋ ነው? ይህ ለ80 ከመቶ ገበሬ 80 የፖለቲካ ፓርቲ ቀርቶ ሁለትና ሶስት ብቻ ሊሆን ነው? ሰው በሰውነቱ ተከብሮ እንዳሻው ተዘዋውሮ የፈለገውን ደግፎ ያልተመቸውን ተቃውሞ በብሔርና ፓርቲ ዕውቅና ሳይሆን በኢትዮጵያዊ ዜግነት በአእውቀትና ችሎታው ነጋዴ ሠራተኛና ነዋሪ ሊሆን ከሆነ ኢህአዴግ ከመጥፋት ዘግይቷል ያጥፋው ብለናል በለው! ብርታት ለተገፋውና አጥፊው ይሁን ።አራት ነጥብ።
merid woldeyes says
ያልካቸው አስተያየቶች ሁሉ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ዓላማና ግበ በሕወሓቶች ብቻ የሚታወቅ።ይኸውም ማደናገሪያ፥ውጥረቱን ማስተንፈሺያ እና በቀጣይ የሚደረገውን ለማሰብ ጊዜ መግዥያ ለማድረግ የተቀነባበረ ሲሆን፤ እንደ ልደቱ አይነቱ ደላላ በወያኔ ሕወሓት ላይ የተቀጣጠለውን እሳት ለማጥፉት በውሐ አፍሳሽነት ተገዝቶ የቀረበ መሆኑ ያስታውቃል። ዶር መረራና ኢንጂንየር ይልቃል ለምን በዚያ ድራማ ላይ መገኘት እንደፈለጉ አልገባኝም። እነርሱ በዚያ ስብሰባ ላይ እያሉ ወታደሩ በመላው አማራ እና ኦሮሞ ክልሎች ንፁሐን ዜጎችን ይጨፈጭፋል።እንዲያው የኛ ነገር 25ዓመት አብረናቸው ኖረን የደደቢት ልጆችን መሰሪነት አለማወቃችን ይገርመኛል
Tadesse says
I haven’t read any thing here of what Semhal Meles said,endinebelh becha new ende se’eluan yakemetkew/wei wedua hagerachen?
Sarrah says
You either don’t read Amharic or don’t want TPLF critiques
የመለስ ዜናዊ ልጅ ሰምሃል መለስ ግራ የተጋባች ተሳታፊ ትመስላለች። ግን አጠር ብላ የረዘመች መልእክት አላት። በህወሃት ውስጥ ያለውን የስልጣን ሽኩቻ ብቻ ሹክ ብላ አላለፈችም። ስልጣንችሁን ላለማስነካት ከምትንደፋደፉ ስልጣኑን ለኛ ስጡን ብላለች።
አባትዋ ከማለፉ በፊት ስለመተካካት ብዙ ተናግሮ ነበር። ሰምሃል ይህንኑ ቃል እንደ ፈጣሪ ቃል አምና ተቀብላለች። ይህ ብቻ አይደለም። የህወሃት ስልጣን እንደ ርስትና ጉልት በውርስ እየተላለፈ ይቆያል ተብሎም ተነግሯታል። ጸጉርዋን የሽፍታ አስመስላ ስልጣኑን ከነበረከት ለመቀበል ብዙ የጠበቀች ነው የሚመስለው። በዚያ ሰሞን ጠመንጃ ይዛ የቶክስ ልምምድ ስታደርግ የተነሳችው ፎቶም ተለቆ ነበር። ይህም በህወሃት መመዘኛ ከርክክብ ቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ መሆኑ ነው።
የመተካካት እና የቅብብሎሹ ወሬ ከአቶ መለስ ጋር ተቀብሮ በጥልቅ ተሃድሶ አዲስ ዜማ መተካቱን ግን ሰምሃል የሰማች አይመስልም። ይህች ወጣት ስብሰባው ላይ የተሳተፈችው የእናቷ አዜብ ጎላን ሃሜት ይዛ ነው የሚለው ንግግራቸው የሚያስኬድ ቢሆንም፤ መልእክትዋ ግን ግልጽ ነው። እስዋም ገና የለውጥ ሳይሆን የጥገና መፍትሄ ላይ ናት።
እንደ ሰምሃል ነገሮችን ሳያላምጡ እየዋጡ፣ ቅዠት ሁሉ ህልም መስሎ እየታያቸው፤ ሕወሃትን እንደ ንጉሳዊ ስርዓት ለማስቀጠል የሚፈልጉ ደፋሮች ጥቂት አይደሉም።
Lusif says
One important thing we all missed and do not mention is the resentment of the Ethiopian youth against the ruling party. Though there is difference between ruling party loyalists and members on one hand and the the oppressed ordinary youth on the other.
Young party members are not comfortable with the dictatorial behaviours and dicision making by the old TPLF central committee. They are heard saying that the oldies, through marriage, partnership in corruption and other means, have become to greedy to power and wealth. On top of that, all of them immersed themselves in political vices and have stopped being pragmatic,creative and inclusive. These young party members wants to grow and succeed through the political process by being positive, creative and inclusive.
The oldies never go away, instead they recycle themselves. So the opportunity is closed to the ambitious young politicians. One see resignations and frustrations
They young party members want to have peaceful transition by engaging all political groups to find a common ground by actively involving themselves in the process.
The other group is the oppressed, alienated and the marginalized mass of youth that wants total change by ending political domination.
Even though, there is some effort underway to bring these two groups to gether, it seems very weak.
All the resentments against the heedless, self righteous, bigoted oldies is so strong. I guess there is a light at the end of the other side. What we all have to do is remove the clogs, clear the way peacefully ( retirement is one option ), so that everybody can see the light.
zola says
የኢህአዴግ ዛሬም “ጥልቅ ተሀድሶ” – የልደቱ አያሌው የቅጥፈት
ነጋሪት
.ቅዳሜ ነሀሴ 1997 ዓ.ም ጠዋት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
መኖሪያ ቤት ደረስኩ። በአካል ስንገናኝ የመጀመሪያዬ ሲሆን ለግል
ጉዳዬ ነበር ያመራሁት። ማታ ያገኘሁትን መረጃ አስቀደምኩ።
በሸራተን ሆቴል ልደቱ አያሌው ከስብሀት ነጋ ጋር ለሶስት ሰአት
ገደማ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሲነጋገሩ ማምሽታቸውን ለፕ/ር
ነገርኳቸው። እሳቸውም ” መገናኘቱ ታዲያ ምን ችግር አለው?..እኔ
ለምሳሌ ከክንፈ ገ/መድህን ጋር እንገናኝ ነበር። ጥሩ ሰው ነው።
እንደዛ ሊሆን ይችላል” አሉኝ። ” በድብቅ መገናኘት በዚህ ጊዜ
ለምን አስፈለገ?..ያውም በምሽት..ስብሀትና ድርጅቱ ያቀዱት
ቢኖርስ?..” የእኔ ጥያቄ አዘል ምላሽ ነበር። ጉዳዩን ሳንቋጭ
በድንገት ኢንጂ. ሽመልስ መጡ። ፕ/ር መስፍን አስተዋወቁኝና
ሌላ ርእስ ቀጠልን።…ይህ በሆነ በሳምንቱ ልደቱ በቅንጅት
ውህደት ዙሪያ ማህተም አላሳርፍም ብሎ ሸሸ። ኢንጂ. ሽመልስ
ያሉበት ሶስት የሽማግሌ አካል ልደቱን ለማወያየት ሲያመራ
አስቀድሞ ያነሳው ቅድመ ሁኔታ አስገራሚ ነበር። ” እዚህ
የምንወያየውም ሆነ እኔን የተመለከተ ጉዳይ በኢትኦጵ ጋዜጣ
የሚወጣ ከሆነ ሁሉንም ነገር ይፈርሳል” አለ ልደቱ።
ሽማግሌዎቹም ” እኛ የምናወራው ስለቅንጅት ፓርቲ ጉዳይ እንጂ
ጋዜጣ አይደለም። ጋዜጣውን ይህን ፃፍ..ያንን አትፃፍ ..የማለት
ስልጣኑም፣ መብቱም የለንም” ይላሉ። ልደቱ ቀበል አድርጎ
“ጋዜጣውን ፕ/ር መስፍን እንደሚያዙት አውቃለሁ” አለ። ..ልደቱ
ምክንያት ይደርድር እንጂ ዋናው አላማው በስብሀት በኩል
የተሰጠውን “ተልእኮ” ማሳካት ነበር። …የቅንጅትን ውህደት
አሰናከለ። ..በኢዴፓ ውስጥ በአባልነት ከነበሩትና በምርጫ
ያልተወዳደሩትን ጨምሮ የሰበሰበው ልደቱ እንዲህ አላቸው፤ ”
ወያኔ በቅርቡ የእስር ዘመቻ ይከፍታል። ስለዚህ ለአውሮፓ
ህብረትና ለአሜሪካ ሪፖርት ማድረግ እንዲያመቸን ሁላችሁም
ሁለት..ሁለት ጉርድ ፎቶ ተነስታችሁ አምጡ” አለ። አሁን ኑሮውን
በአውሮፓ ያደረገው ወጣቱ ምሁር አለማየሁ በልደቱ እምነት
ከነበራቸው አንዱ ሲሆን ሲናገርም ” .ጥቅምት 22 ቀን 98 ዓ.ም
አዲስ አበባ ከባድ ተቃውሞ ተነሳ። ምሽት ላይ መንግስት ይፈለጋሉ
ያላቸውን የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች በፎቶ አስደግፎ በቲቪ
ሲያቀርብ እኔና ጓዶቼ ለልደቱ የሰጠነው ፎቶ ተለጥፎ ስመለከት
ደነገጥኩ። በማግስቱ ሄጄ ማእከላዊ እጄን ሰጠሁ። ስለልደቱ
መናገር አይደለም ማሰብ አልፈልግም” ብሎኛል ከእስር
እንደተፈታ። ..ልደቱ ወደ ፓርላማ ..ሌሎች ወደእስር ቤት ተጋዙ።
በመቶዎች ተገደሉ፣ ተሰደዱ። ለዚህ “ውለታ”ው ከባለሀብቱ ብቻ 6
ሚሊዮን ተሸጎጠለት። ከኢህአዴግ ደግሞ ከለንደን ትምህርት ቤት
ክፍያ አሁን እስከሚገነባው ትልቅ ሆቴል በሚሊዮን ተንበሸበሸ።
..የልደቱ አያሌው የጀርባ ታሪክ ይህ ብቻ አይደለም..ከፅላት እስከ
ልደታ ፍ/ቤት፣ ከመአድ ቢሮ እስከ ፕ/ር አስራት ግድያ
ተዋናይነት..የነበረውን ሚና ጋዜጠኛ ሴሳይ አጌና ጠይቁት።
..ኢህአዴግ ዛሬም “ጥልቅ ተሀድሶ” የሚለው የቅጥፈት ነጋሪት
ለመሆኑ ልደቱን ይዞ መውጣቱ ነው!!!!
( አርአያ ተ/ማርያም)