• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እሰራት ምላሽ አይሆንም

March 23, 2014 02:10 am by Editor Leave a Comment

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት መጋቢት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ዓመት አራተኛ መደበኛ ስብሰባው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ በተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ ፖሊስና ፍርድ ቤት በመተባበር የፈጸሙትን ሕገ መንግስት የጣሰ ተግባር፣ እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት በደረሳቸው ግብዣ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓም ምሽት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፈያ በተገኙት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላይ ራሳቸውን ከህግ በላይ ያደረጉ የደህንነት ኋይሎች የፈጸሙትን አሳፋሪና ሕገ ወጥ ተግባር በመመርመር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡

  1. የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ የተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በሩጫው ከተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚለዩት የነጻነትን ቀን ሊያከብሩ በተገኙበት ቦታ ስለ ነጻነት፣ስለ ፍትህ፣ስለዴሞክራሲ፣ስለ ሰብአዊ መብት ወዘተ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማታቸው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 29/2 «ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው» ተብሎ የተደነገገውን ከምንም ያልቆጠረውና ሕጉን ሳይሆን ጠመንጃውን ተማምኖ፣ የሙያውን ሥነ ምግባር ሳይሆን የአለቆቹን ትዕዛዝ አክብሮ እንደሚሰራ በተግባሩ ያረጋገጠው ፖሊስ እነዚህን የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣቶች አፍሶ ሲያስር አንዳችም ህጋዊ ምክንያት አልነበረውም፣ የፖሊስ ሕገ ወጥ ተግባር በዚህ ሳያቆም የታሰሩ የትግል አጋሮቻቸው የሚገኙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱ የፓርቲው አመራር አባላትንም አሰረ፡፡ ዋስትና ለማስከልከል አይደለም ለክስ የሚያበቃ ምንም ምክንያት ሳይኖረው ለፍ/ቤት ምርመራየን አልጨረስኩም የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አባላቱ ለአስር ቀናት በጣቢያ እስር እንዲጉላሉ በማድረግ ሕግን ለማስከበር ሳይሆን የፖለቲከኞችን ፍላጎት ለማስፈጸም የቆመ መሆኑን በተግባር አረጋግጠ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህንን ሕገ መንግሥቱን በግልጽ የጣሰ የፖሊስ ተግባር በጽኑ እያወገዘ፣ፖሊስ የግለሰቦች ሥልጣን ጠባቂ ሳይሆን ሕግ አስከባሪ መሆኑን በተግባር እንዲያሳይ ይጠይቃል፡፡
  2. የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19/4 «የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም ህግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡» ተብሎ የተደነገገውንእንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምር ፍርድ ቤቱ ለህግ የበላይነት የሚሰራና  በመተላለፍ ታሳሪዎቹን የዋስትና መብት ከልክሎ ለሁለት ግዜ ለፖሊስ የግዜ ቀጠሮ የፈቀደው ፍርድ ቤት፣ የእኔ ሥልጣን አይደለም መደበኛ ፍርድ ቤት አቅርቡዋቸው በማለት ካሰናበት በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለክስ አይበቃም ተብሎ በአቃቤ ሕግ ውድቅ የተደረገበት ፖሊስ መልሶ እዛው ፍርድ ቤት ሲያቀርባቸው እያንዳንዳቸው 1300 ብርና የሰው ዋስ በጣምራ ለፍትህ መከበር የቆመ አለመሆኑን በተግባር ያረጋገጠበትን ይህን ተግባር እያወገዘ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79/2 «በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው» እንዲሁም በአንቀጽ 79/3 ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፣ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም »ተብሎ የተደነገገው በተግባር እንዲገለጽ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
  3. የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ የሚያደርሳቸውን አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ አሟልተው ሻንጣቸው አውሮፕላን ላይ ካስጫኑ በኋላ ፓስፖርታቸው በደህንንት ኋይሎች ተቀዶ ጉዞአቸው እንዲስተጓጎል ተደርጓል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህን ሕገ ወጥ ብቻ ሳይሆን እጅግ አሳፋሪ የሆነና የደህንነት ክፍሉን ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱንም ስም የሚያጎድፍ ተግባር በጽኑ እያወገዘ ድርጊቱን በፈጸሙት ማን አለብኝ ባዮች ላይ ከሕግ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ የሚያሳይ ሕጋዊ ርምጃ አንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡ 4–መንግሥት ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄ እስራት አፈናና ማስፈራራት ምላሽ እንደማይሆን ከታሪክ በመማር ለዜጎች የመብት ጥያቄ ትክክለኛውን ምላሽ እንዲሰጥና ትግሉ ሰላማዊ፣ ዓላማው ሕዝባዊ ግቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ ከሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጥፋት እጁን እንዲያነሳ አጥበቀን እንጠይቃለን፡፡

መጋቢት 14/2006 ዓም አዲስ አበባ

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule