• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስአበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

April 14, 2014 11:09 am by Editor Leave a Comment

አዲስ አበባ፡– ሰማያዊ ፓርቲ “የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!”› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Blue Advert April 12ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ያደረገውን ጨምሮ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ባደረገበት ወቅት የኑሮ ውድነት፣ የእምነት ጣልቃ ገብነት፣ ሉዓላዊነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀልና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎችን አንስቶ የነበረ ቢሆንም ጥያቄዎቹ ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ የህዝብ ግንኙነቱ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ በእስልምና እና ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት፣ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና አሁንም ድረስ ተባብሰው መቀጠላቸው ሰላማዊ ሰልፉን በመጥራት ህዝቡ እነዚህን የተነጠቁ መብቶች እንዲያስመለስ ማስተባበርና ማታገል የግድ በማለቱ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ለገዥው ፓርቲ ስልጣን እንጅ ለህዝብ አገልግሎት የማይጨነቁት ተቋማት ስራቸውን በሚገባ ባለመስራትቸው ህዝብ ለከፈለው ክፍያ የሚገባውን አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑም ሌላኛው ሰላማዊ የሰልፉ ምክንያት መሆኑን ተገልጹዋል፡፡ በተለይ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮሚኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ህዝብን እያማረሩ መቀጠላቸው መፍትሄ ስለሚያስፈልገው የሰላማዊ ሰልፉን አስፈላጊነት እንዲሚያጎላው ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

ምንም እንኳ “የህዝብ መብት መነጠቅና የአግልግሎቶች እጦት ሰላማዊ ሰልፉን ወቅታዊ ቢያደርገውም የሰማያዊ ፓርቲ በአመት ውስጥ ከያዛቸው ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ህዝብ የተቀማቸውን መብቶች ማስመለስ መሆኑንና ይህም በተደጋጋሚ በተለያዩ ሚዲያዎች መገለጹን” አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ እሁድ ሚያዚያ 19 ከቀኑ 4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ካሳንቺስ ከሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት እስከ ጃን ሜዳ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን ጃን ሜዳ የተመረጠበት ምክንያትም መብቱን የተነጠቀውና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በሚገባ ማግኘት ያልቻለው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ጥያቄዎቹን እንዲያነሳ ሰፊ ቦታ በማስፈለጉ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየ ክፍለ ከተማው የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው ‹‹በሀይል የተቀሙትን መብቶችን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያውና እያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ በማድረግ አገራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ (ምንጭ: – ነገረ ኢትዮጵያ)

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule