• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ክንፉ ምን ነካህ?

May 16, 2017 09:43 am by Editor Leave a Comment

ቴዲ በክርስቶስ ተቦርነም በጲላጦስ እንዲት ይመሰላሉ?

ምሳሌያዊ አነጋገሮች ተረቶቻች፣ የታላላቅ ሰዎች አባባሎች መጽሐፍትና ገጠመኞች እየተጠቀሱ ንግግር መክፈቻም ሆነ የጽሁፍ መነሻ መሆን በፊትም የነበረ አሁንም የቀጠለ የተለመደ ነገር ነው።  እንደዚሁም የክርስቶስ ቃል የሀዋርያት ትንቢት ምሳሌና ተግሳፅም እንደቦታው አስፈላጊነት የሚጠቀስበት ጊዜ አለ። ይህም የሚሆነው ትምህርት ለመስጠት የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ እንደአስፈላጊነቱም ጊዜውና  የተፈጸመውን ድርጊት ለማስተማር ነው።  በሰርግ ጊዜ ጌታ በሰርግ ቦታ ተገኝቶ ባዶዎቹን  እንስራዎች በጣፋጭ ወይን ሞላቸው ተብሎ ትምህርት እንደሚሰጠው።

አንተም  ለጽሁፍህ መነሻ ያደረከው  ቃል በማትዮስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፩.  ሰፍሮ ይገኛል።  ቃሉም እንደሚያስረዳው እየሱስ በዛን ጊዜ ይሁዳ አሳልፎ ስጥቶት ሽማግለዎችና የካህናት አለቆች ተማክረው ሊገድሉት  ለክስ የሚሆናቸውን ቃል  ከአፉ ለመስማት ይፈልጉ ስለነበር ዝምታ መረጠ። ገዥውም በጠየቀው ጊዜ አንተ አልክ የሚል መልስ የሰጠው  ለዚህ ነው።  

ሁኔታው   እንዲህ  ሆኖ እያለ ተቦርነ ቴዲን ተቸው ብሎ ይሄን ቃል  መጠቀም ተገቢ አልነበረም። ተያያዥነትም የለውም  ግድየለም   አላዋቂነት ነው ብለን እንዳናልፍ ለአረፍተ ነገሩ መጠቅለያ ያደረከው ሰማይን ያለ ምሰሶ ያቆመው ክርስቶስ “ጥፋ” የምትል ቃል ብቻ ከአንደበቱ ቢያወጣ ኖሮ ፒላጦስ አይደለም መላው ቂሳር ክምድረ-ገጽ በጠፉ ነበር። ያልከው ቃል ደግሞ ለስህተትህ ሌላ ማጠናከሪያ ሆኖ ይታያል  ለመሆኑ በውቅቱ ስንት ቄሳሮች ናቸው ያሉት ከአውግስጥስ  ቄሳር ውጪ ሌላ ቄሳር አልነበረም ቄሳሮች በየተራ የሚተኩ ንጉሶች ነበሩ።  ምናልባት የሚጠፉት አይሁዳውያንና ፈሪሳውያውያን ጣፊዎችና የካህን አለቆችንን ማለትህ ይሆን? ደግሞስ እንደጠቀስከው ምሳሌ ቴዲ ጥፋ ቢል ተቦርነና መሰሎቹ ይጠፋሉ ማለት ነው። በምን ሀይሉ ነው የሚያጠፋቸው መጥፊያቸውስ የት ነው? ማንንም ማድነቅ ይቻላል ቴዲም መደነቅ የሚገባው ነው ግን አድናቆትህ ግን ልክ ይኑረው።

 ጽሁፍህ ብዙ ስህተቶች የታጨቁበት በመሆኑ አንተ ካልከው  ቃል ሳልወጣ ወደ ሌላው ልለፍ፤ ”ታዋቂዎች በአዋቂዎች ላይ የሚቀልዱበት ይህ የገሃዱ አለም እውነታ ግብረ-ገብ ወደ ግብግብ በተቀየረበት በዚህ ዘመን ባሰበት እንጂ አልጠፋም። ጥንት አንቺ-ትብሽ ፣አንተ-ትብስ ይባል የነበረው ብሂል አሁን በ”አንቺ ብስብስ አንተ ብስብስ” ተቀይሯል ሲል አንዱ አጫወተኝ። ከቶውንም ስድብን እንደ ስንቅ በከረጢት ቋጥረው በሚጓዙበት የፌስ ቡክ ዘመን መስመር የመልቀቁ ነገር አዲስ ሊሆን አይችልም።  “አንተ አልክ?” ብሎ ማለፍ ምን ይጎዳል?” ያልከው ደግሞ ይበልጥ ያስገርማል አዋቂው ቴዲ ታዋቂው ደግሞ ተቦርነ መሆኑ ነው ወይ? ለመታውቅ ከሆነ ቴዲ ከተቦርነ በላይ ታዋቂ ነው በእውቀት ከሆነ ሁለቱን ያወዳደርካቸው በምን ላይ ተመርኩዘህ ነው? ቴዲ  ከየትኛው ዪኒቨርስቲ ተመርቆ ነው የዘፈን የግጥምና የዜማ ማውጣት ድግሪውን የተቀበለው ተቦርነ ፈተና ወድቆ ነው ማለት ነው ጋዜጠኛ የሆነው የማይገናኙ ነገሮችን አብረህ አትሰር ሰው አጫወተኝ ብለህ ያቀረብከው እንቶ ፈንቶ ከተነሳህበት ጉዳይ ጋር እንኳን ዝምድና ሊኖረው ይቅርና ትውውቅም የለው። ስው የተናገረው ሁሉ አይጻፍም እኮ ወዳጄ ሰብሰብ ኮምጨጭ በል።

ከዚህ ጽሁፍህ ዝቅ ስል ደግሞ በንግሊዞች አፍ የተናገሩት ተርጉመህ አቅርበሃል ይሄስ ቢሆን ምን ያስፈልጋል፤ “ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍቷል” ምን አመጣው? ፌስ ቡክም ቢሆን  ለብቻው መተቸት የሚገባው ሊኖር ይችላል፤ እዚህ ጋ ደንጉረህ አብረህ መፍጨት ምን ያስፈልጋል? የምጨምረው ነበረኝ ትቼህ ዝቅ ልበል።

የከተፋ ወግ ከመግባቴ በፊት ትለናለህ፤ ከተፋ ምንን ቃል ይወክላል? የምትጽፈው እኮ ስለትልቅ ጉዳይ ነው፤ ትላልቅ አንባቢዎችም ፊት የሚቀርብ እኮ ነው። እና እነዚህ ሰዎች ከተፋ ወቀጣን የሚወዱልህ ይመስልሃል? መጽሃፍ ቅዱስ አዋቂ ነኝ ብለህ  አራዳነትን በቋንቋ ሽፋን ተላብሰህ ዱርዬ መሆን አብረው አይሄዱምና፤ አንዱን ያዝ ወይ መንፈሳዊነቱን ወይ ዱርዬነቱን ምረጥ። “እኔ ማለት ምችለው ቴድሮስ ካሳሁን / ቴዲ አፍሮ / ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የጠፋውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የመለሰ ልብ አስታራቂ ልጅ ነው።” ብለህ የጠቀስካትም ትዝብት ላይ ጥላሃለች። ሃይሌን  ስታበሻቅጡት እንዳልከለማችሁ  ዛሬ ስለቴዲ ይችን ተናገረና ያ ሁሉ ውርጅብኝን አወራረደ ማለት ነው። እግዚዎ!

እንዳልከው የዘፈንን ሙያ ለመተቸት አቅም ስለሌለኝ እዛው ውስጥ ገብቼ አልቦራጨቅም። ይህ ማለት ግን ምንም አልናገርም ማለት አይደለም። ተቦርነንም እንደሰማነው ቴዲ የይርጋ ዱባለን ዘፈን በዘፈኖቹ መሀል እንደተካተተ ተናገረ እንጂ ሌላ ያለው ነገር የለም። በርግጥ ቴዲና ተቦርነ ወይም አንተና ተቦርነ ወይም ሌላ ሰበብ የምትፈላለጉበት ነገር ከሌለ በቀር ይሄን ሁሉ ውርጅብኝ የሚያስወርድ ጽሁፍ መጻፍ የሚያስፈልግህም አልነበረም። ያንን ሁሉ ተረትና ምሳሌ በዚ ጽሁፍ ምን አዘረገፈህ? ቆጥበህ ለሌላ ጽሁፍ ብታውለው አይሻልም ነበር?! አንድ ሽህ ዝንብ … ሽሩባ ልትሰራ ሄዳ … አሽቃባጭ እና ጥሩምባ ነፊ ምናምን ለምን አስፈለገ?

ጽሁፍህን ወደ ታች እያነበብኩ  በወረድኩ ቁጥር፤ “ወይ ጉድ!” እያልኩ ነው የተጓዝኩት። ተቦርነ ኢሳትን ምርኩዝ አድርጎ ምናምን ያልከውም ሌላው አስገራሚ ነገር ነው። ተቦርነ በኢሳት ሬድዮ መደበኛውን ዝግጅት አለው። በዛ ዝግጅቱ ላይ ቴዲንና ስራውን በተመለከተ እንደ ጋዜጠኛ መጠነኛ ገለጻ አደረገ እንጂ ኢሳትን ተመክቶ ምን ነገር ፈጠረ? ስለ  ቴዲ ለመናገር  የሚሰራበትን ቦታ ትቶ ወደ ሌላ ሬድዮ ጣቢያ መሄድ ነበረበት ወይ? ወይስ ከኢሳት ዝግጅት መልቀቅ  ያስፈልገው ነበር? አንተም ተቦርነን የተቸህበትን ጽሁፍና ምስል፤ እንዲሁም የድምጽ ቅንብር ባንተው ገጽ ላይ አውጥተህ ለጥፈህ የለም እንዴ?  ድረ ገጽ ስላለህ በዛ ተመክተህ ወይም አመቺ ስለሆነልህ ነው የጻፍከው ልትባል ነው? የምታቀርበው ነገር ሁሉ  ፍጹም ያልተያያዘ  ስለሆነ እየሰለቸኝ ነው፤ አላስችል ብሎኝ እንጂ ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ልተውህ  ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ተናጋሪ ጠፍቶ ስህተትህ ላይ ወድቀህ እንዳትቀር ስለሰጋሁ የግድ መናገር ኖረብኝ።

ተቦርነ አለ ብለህ ወደ አሰፈርከው ደግሞ እንሂድ “በቴዎድሮስ ካሳሁን አዲሱ ኢትዮጵያ የሚዚቃ አልበም ውስጥ የአንጋፋውን የባህል ድምጻዊ የይርጋ ዱባለን ጎንደር የተሰኘ ስራ ጨምሮ 14 ያህል የሙዚቃ ስራዎች ተካትተዋል።” አለፍ ብለህም ደግሞ  “ከአንጋፋው ይርጋ ዱባለ ጎንደር የተሰኘው ስራ ውጭ ሌሎች አስራ ሶስት የሙዚቃ ስራዎች ግጥም እና ዜማ ድርሰቶች የድምጻዊ  የቴዎድሮስ ካሳሁን ናቸው።” ብሏል ትለናለህ  ይሄን ማለቱ ምኑ ነው ጥፋቱ  በርግጥም ዘፈኑ ይመሳሰላል ባህላዊ ዘፈኖች ደግሞ ብዙውን ጊዜ ይወረራረሳሉም ይመሳሰላሉም ያን ተባለና ቴዲ ምኑ ተነክቶ ነው አንተን ቡራ ከረዩ  ያሰኘህ። ወዳጄ ሆይ! መለስ ብለህ የጻፍከውን ቃኝ አሳፋሪም አስነዋሪም ነው።  የሽያጭ ሰልፍም ከቴዲ አወዳደረ ብለህ የተቆጣህ መሰለኝ፤ ተቦርነ የጠቀሳቸው ተወዳጆቹና አንጋፎቹ  ዘፋኞን  በጊዜው ይብዛም ይነስም እንደ ቴዲ ይሁን አይሁንም ያሳተሙትን የሙዚቃ ካሴት በሰልፍ ሸጠው ነበር መባሉ ቴዲን ያንኳሰሰው እንዴት አድርጎ ነው? ህዝብ ናቀ ያልከውስ በምን መልኩ ነው? ህዝብ የናቀው የዚህን መልስ ካንተው በስተቀር ማንም ሊናገረው አይችልምና ላንተው ልተወው።

ወደ ማገባደጃህ ግድም ደግሞ አንድ ያላወቅነው ቁርሾ እርስ በርሳችሁ እንዳለ የሚገልጽ  አባባል ይታያል። ይሄን እርስ በርስ ፍቱ እንጂ ህዝብን ከታችሁ ልታንጫጩ አትሞክሩ። ቆዳ ሲወደድ … የሚለው የጽሁፍህ የመዝጊያ መጀመሪያ አለቦታው የተወተፈ ነው። እጅህን ከቴዲ አንሳ! የሚለውን ማሳረጊያህ ደግሞ ከላይ የጠቀስከውን የመጽሀፍ ቃል አጠናክረህ  ለመናገር የፈለክ አስመስሎሃል። ተቦርነ እጁን ከቴዲ ላይ የማያነሳ ከሆነ ያችን አስፈሪዋን ጥፋ የምትል ቃል ቴዲ ያወጣትና ተቦርነና መስሎቹ ተለቃቅመው እንደሚጠፉ ማስጠንቀቂያ መናገርህ መሰለኝ።

በዚህ በፍጹም በፍጹም አትስጋ ቴዲ ተቦርነን ግፋ ይለው እንደሆን እንጂ ጥፋ ሊለው እንደማደፍር እወቅ። እንኳን በአንድ ቃል በአንድ ሽህ ቃላትም እንደማያጠፋው ያውቃል። ምክንያቱም እንዳተ ምሳሌያዊ አባባል ቴዲም እየሱስ ተቦርነም ጺላጦስ አይደሉምና ሊጠፋፉ አይችሉም።

አቤቱ አምላክ ሆይ! … ክንፉ ባለማወቅ ላደረገው ይቅር በለው! ልቦናና ማስተዋልም ስጠው! – አሜን!!

ዲበኩሉ ቤተ ማርያም (dibekulubm@gmail.com)


የክንፉ ምላሽ

ውድ ዲበኩሉ፣

ለጽሁፌ የላክከውን ምላሽ ፖስት አድርጌዋለሁ። ከፈጣሪ ምህረትን ስለጠየቅክልኝ እና የተሰማህን ሁሉ በጨዋ መልክ ስለጻፍከውም አመሰግናለው። አስተያየትህን በእውነተኛ ስምህ ብትጽፈው ደግሞ የበለጠ ጥሩ ይሆን ነበር። የራስን ስም ደብቆ የሌላውን እያነሱ ማፍረጥ ባይለመድ ጥሩ ይመስለኛል። መተማመንም ይኖር ነበር።

ለግንዛቤ ይሆንህ ዘንድ –  ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ – በቴዲ ላይ ከሶስት አቅጣጫ ሰዎች መነሳታቸው ነው።   አንደኛው  የወያኔ ሰዎች፣ በሁለተኛ ረድፍ ጃዋራውያን ሲሆኑ በሶስተኛ ደረጃ  ደግሞ እንደ ተወልደ ያሉ – ወገን የምንላቸው ሰዎች – በመነሳታቸው ነው። በደንብ ከተመለከትከው ጽሁፉ ያተኮረውም በተወልደ ላይ ብቻ ሳይሆን በነዚህ ሶስት ቡድኖች ዙርያ ነው። በየማህበራዊ ገጾች፣  በዚህ ብላቴና ላይ እየወረደ የነበረው ናዳ ቀላል አልነበረም። እኔ ልጻፈው እንጂ፣ እጅግ ብዙ ሰዎች መናደዳቸውን እና እያጉረመረሙ እንደነበሩ አንተም ልትገነዘበው ይገባሃል። ለዚህም ይመስላል  እስካሁን ከጻጸፍኳቸው መጣጥፎች ሁሉ እንደዚህኛው ጽሁፌ ብዙ አስተያየቶች አለገኘሁም። ያንተን የሚመስሉ ጽሁፎችን በየፎረሙ እየተደጋገሙ ተለጥፈው አይተናቸዋል። ወገን ብለን የምናምነው ማንም ሰው ያለ አግባብ ሲዘመትበት እንደማደርገው ነው ያደረግኩት እንጂ – ፈጽሞ የግል ጉዳይ አይደለም።

ነገር የሚገባው በምሳሌ ነውና እኔም አስተያየቴን በዚያ መንገድ  ጻፍኩ።  አንተ ምሳሌያዊ አነጋገሩን በጥሬው ተርጉመህ ከአንድ ግለሰብ ጋር  ብቻ ለማያያዝ መሞከርህ ፍጹም ስህተት ነው።

ክንፉ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule