• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሮመዳን ዋዜማ እና ሮመዳን በሳውዲ

July 9, 2013 02:19 am by Editor Leave a Comment

እንኳንስ ለኔ ቢጤ አፍላ የጎልማሳነት እድሜውን በሳውዲ እየገፋ ላለ ላንድ ሰሞን ጉብኝት ሳውዲን የመጎብኘት እድልን ላገኘ የሮመዳን ወር የጾምና የጸሎት ወር ልዩና የማይረሳ ትዝታ ይቋጠርበታል፡፡ በሮመዳን ዋዜማ የገበያ ጥድፊያramadan 1 የተለመደ ነው፡፡ ጾሙን ለመያዝ የሚያስችሉ የምግብ ፍጆታና ቁሳቁሶችን ዋዜማ መገለጫ ሆኖ ከአመት አመት የሚስተናገድ ቀልብን ሳቢ ትዕይንት ነውና በዛሬው የማለዳ ወጋወጌ ስለ ሮመዳን ዋዜማ ከማውቀው ጥቂቱን ላካፍላችሁ ወድጃለሁ ! የፈቀዳችሁ ተከተሉኝ. . .

. . . ጾም ሲፈታ ለሚቀርበው የጾም መፍቻ ተምርና ጣፋጭ መጠጦች ጨምሮ የምግብ ማዕዱን ramadan 3ለማድመቅ ታላቅ ቅናሽን በሚያደርጉት ትላልቅ የገበያ አዳራሾች የሚደረገው ግብይት ደምቆ የሚስተዋለው በሮመዳን ዋዜማ ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ ለአረቦች ነዳጅ ለሰጠ ፈጣሪ ምስጋና ይግባውና የዘመኑ ቴክኖሎጂ የወለዳቸው የተለያዩ የባውዛ መብራቶችና የሌዘርramadan 2 አንጸባራቂ ብርሃኖች አውራ መንገዶችንና የህዝብ መዝናኛ ቦታወችን የማድመቁ ሃላፊነት የሳውዲ መንግስት ሃላፊነቱን ሲወጣ የሚታየው የሮመዳንን በአል ለመቀበል ሽር ጉድ የሚባልበት አጋጣሚም ይህ የዋዜማ ወቅት ነው ! በሮመዳን ጂዳ እጹብ ድንቅ የሚታይባት ሙሽራ ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም !

በሮመዳን ሰውም ቸር ነው ! . . . በየመንገዱ ሲያልፍ ሲያገድም ሰላም ሳይባባል አይተላለፍም፡፡ በተለይ በጾሙ ወቅት ለአንድየ ሰላምታ ” አውቀዋለሁ ፣ አላውቀውም” የሚባል ነገር አይሰራም፡፡ ፈገግ ብሎ በሰላምታ ከመጨባበጥ ባለፈ አብሮ እንዳደገ ትከሻ ለትከሻ ሰላምታ መለዋወጥ የተለመደ የሮመዳን ወር ልዩ ህበረ ቀለማዊ ውበት ነው፡፡ ቀን ላይ ሁሉም ምግብ ቤቶችና ሻሂ ቤቶች ዝግ ናቸው፡፡ ከረፋዱ ጀምሮ ቢሮዋቸውን የሚከፍቱት በአብዛኛው ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ትሥሥር ያላቸው ጽህፈት ቤቶች ፤ ለሮመዳን ፍጆታ ምግብ መጠጥ ምኑ ምናምኑን የሚያቀርቡት ፋብሪካዎችና ከዚሁ ጋር ተዛማጅ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሱቆች ብቻ ናቸው፡፡ ቀኑ ወደ ማታ የተቀየረ ይመስላል፡፡  ጾሙ ከተፈታ በኋላ ምሽት ላይ ምግብ ሲበላ እንደ ሃገራችን ሰው በቅርቡ ያለውን ይጋብዛል “ፈደል” ይሉታል ! “እባክህ እንብላ !” እንደ ማለት ነው፡፡ እንብላ ብሎ አንዱ አንዱን ሲሸማግል ማየት የተለመደ ነው !

ጅዳ በምትደምቅበት ወቅት በሮመዳን ሁሉም ነገር የሚሆነው ማታ ነው፡፡ ታዲያ ማታ ይህ ሁሉ ሲሆን ቀን ላይ ጥድፊያ አይታይም፡፡ አውላላውን ጥርጊያ መንገድ ሞልተው የሚርመሰመሱት ሚጢጢዎችም ሆኑ ትላልቅ የቅንጦት መኪኖችም አልፎ አልፎ ውር ውር ከማለት ባለፈ ብዙ አይታዩም፡፡ ከተማዋ የተወረረች ትመስላለች፡፡ ቀን ላይ ሃይማኖቱ ምንም ይሁን ምን እንደ ሲጋራውና እንደ ምግቡ ሁሉ ውሃ መጠጣት እንኳ አይፈቀድለትም፡፡ “መምኑእ” ነው ክልክል ! በሳውዲ ! በሮመዳን ጾም ዋዜማ የሚፈልገውን ሁሉ እቤቱ ከዋውኖ መውጣት ግድ ይላል ! የስሞኑ ናላን ሰብሮ የሚገባው የጅዳን ሃሩር ጸሃይና የቀይ ባህር ወበቅ አይጣል ነው! . . .ዛሬ በዋዜማው ያለሁት ከመካ 80 ኪሌ ሜትር የቅርብ ርቀት በምትገኘው በወደብ ከተማዋ በጅዳ ነው! አምና ይህን ሰአት ድግሞ ከልጆቸ ጋር የሮመዳንን ዋዜማ የመጨረሻ ቀን የተቀበልኳት ኮረብታማ እናramadan kareem ረባዳ በሆነችው ከተማ ጣይፍ ላይ ሆኘ መካን ቁልቁል እያየኋት ነው ! . . . በቀጣይ አመታት የት እንደምሆንም ብቻ ሳይሆነ እኖር አልኑር፣ የሚያውቀው አንድየ ብቻ ነው!

በዘንድሮው ሮመዳን ቅዱሳኑ መካና መዲና እንደለመዱት ከመላ አለም ለጸሎት የሚመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናን ሙሉ በሙሉ አይስተናገድባቸውም ። ምክንያት አለው ፣ታላቁ የካእባ እና የመዲና ቅዱሳን ቦታዎችን ለማስፋፋት ፣ ከአመት እስከ አመት ተንቦርቅቆ ውሎ የሚያድረውን የበርሃ ሃሩር ወደ ኤሌትሪክ ሃይል ለመቀየር ፣ ትላልቅ ማረፊያ ሆቴሎች ለመገንባት እና ቅዱሳኑን ቦታዎች በፈጣን ዘመናዊ ባቡር ለማገናኘት በቢሊዮኖች የሚቆጠር መዋዕለ ንዋይ ተመድቧል። ከግንባታው ጋር መጨናነቅ እንዳይፈጠር የጸሎተኞች ቁጥር እንዲቀንስ መደረጉን የሳውዲ መንግስት አስታውቋል። በዚህ መሰረት ከሃገር ውስጥ የጸሎተኞች ኮታ በ50 እጅ የቀነሰ ሲሆን የውጭ ምዕመናን ኮታ በ20 እጅ እንዲቀንስ ተደርጓል ! ግንባታው ሲጠናቀቅም የመካና መዲና የቅዱስ ቦታዎች የማስተናገድ አቅም በእጥፍ ድርብ እንደሚጨምር በዋዜማው ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ለሮመዳኑ ዋዜማ የማለዳ ወጌ ግብአት ሆነውኛል!

እንኳን ለሮመዳን የጾምና የጸሎት ወር በሰላም አደረሳችሁ !

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule