
እ.አ.አ በገስት 17 ቀን2013 በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያውያን የፖለቲካና የሲቪክ ማህበር ወይም ኢ.ፕ.ኮ/EPCOU/ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰበሰቡ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ሲሆን የኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ/ኢ.ሕ.አ.ፓ/፤ የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት /ሞረሽ/ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አመራሮችና አባላት በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል።
ሰልፉኛው መነሻ ሃውፕት ቫክ /HAUPT WACHE/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ መፈክሮችንና በኢትዮጵያ ባንዲራዎች በማሸብረቅ ጉዞውን በተለያዩ የከተማው ክፍል በማድረግ ከሶስት ስአት የእግር ጉዞ በኋላ መድረሻውን ከተነሳበት ቦታ አድርጎል።
የሰልፉ ዓላማ
- ስልጣንን መከታ በማድረግ ከድሀው ህዝብ የዘረፉትንና በውጪ ባንኮች ያስቀመጡትን ገንዘብ በአስቸኳይ እንዲመልሱና ለህግ እንዲቀድቡ።
- በወያኔ እስር ቤት የሚሰቃዩ የፖለቲካ እስረኞች ጋዜጠኞች በአስቸኳይ ይፈቱ።
- የወያኔ ኢህአዴግ በሃይማኖት ጣልቃ ገብነቱን በአስቸኳይ ያንሳ የሙስሊም ወንድሞቻችን ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይመልስ።
- ሰማያዊ ፓርቲ ፤ አንድነትና ሌሎችም በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ሃይሎችን በሙሉ ልብና ሃይል የምንደግፍና የሚደርስባቸውን ወከባና እስር አጥብቀን እንቃወማለን!
የሚሉት ሲሆኑ ሰልፉም ከመጠናቀቁ በፊት በሲቨክ ማህበር ሊቀመንበር በአቶ በላይ ወንዳፍራሽ እና በሃይማኞት አባቶች ንግግር ተደርጎል። ተሳታፊው የዲሞክራሲ ስርዓት እውን እስከሚሆን ድረስ የሚያደርገውን ትግል አጥብቆ እንደሚቀጥል በአቋም መግለጫው ቁርጠኝነቱን ገልጾ ሰላማዊ ሰልፉ ተጠናቆል።
በየነ መስፍንና ተድላ ጌትነት
ጀርመን ፍራንክፈርት
Leave a Reply