ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች
አገራችንን ለአለፉት 27 ዓመታት ያሻውን በማድረግ በከፍተኛ አፈናና የጉልበት አገዛዝ ሲገዛ የነበረው ህወሃትና በሌሎች አክራሪ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ።
ህወሃት በገዥነት ዘመኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፈውን ሀብት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል ከትግራይ ውጭ ያለውን የአገራችንን ክፍል ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በየቀኑ የአገራችንን ፖለቲካ ከሚዳስሱ ባለሙያወች በበቂ ሁኔታ ከተረዳን ቆይተናል።
በዚህም ምክንያት አገራችንን ከተጋረጠባት ሴረኛ አደጋ ለመታደግ ከዚህ ቀደም በአሜሪካና አውሮፓ የምንገኝ በቁጥር 31 የምንሆን በሶፍት ዌርና ኢንፎርሜሽን ኮሚንኬሽን ሙያወች የተሰማራን Ethical Hackers የህወሓት ባለስልጣናትን እና አጋሮቻቸውን የኢሜይልና የሶሻል ሜዲያ አድራሻወች በመስበር የሚገኙ መረጃወችን ለተለያዩ አክቲቪስቶችና ሜዲያወች በመላክ ሴራዎቻቸውን ለሕዝብ እንዲጋለጥ ስናስደረግ ቆይተናል።
በዚህ የተደናገጠው የህወሃት ከፍተኛ አመራር የተፈጠረባቸውን ቀላል አደጋ ለመከላከል ባለመቻላቸው የዘርፉን ባለሙያወችን በተለይም መቐለ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንን ሲያማክሩ ከርመዋል።
ይሁንና ህወሃት ከደረሰበት ጥቃት በማገገም ከፍ ባለ ደረጃ የአገሪቱን ከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማትን በማጥቃት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትርምስ እንዲፈጠርና በዚህም አገራችን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንድትጓዝ አገር በማናወጥ ስራ ላይ ተጠምዷል።
ከሰሞኑም በራሱ በህወሃት ትዕዛዝ የአገሪቱ ፋይናንሽያል ሲስተም ላይ ጥቃት ሊደርስ ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ለተወሰኑ ደቂቃወች ኢንተርኔትን በማቋረጥ ያከሸፈ መሆኑ በመገናኛ ብዙሀን ተነግሯል።
ይህ የአገሪቱ ፋይናንሽያል ሲስተም ላይ የተነጣጠረ ጥቃት ከብልፅግና ፓርቲ ምስረታ ጋር ተያይዞ የፓርቲወቹ ውህደት ያልተዋጠላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር ለሚያደርጉት ቀጣይ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታወችን ለመፍጠር ታቅዶ የተፈፀመ ተግባር እንደሆነ ከፖለቲካ ባለሙያወች ለመረዳት ችለናል።
በመሆኑም 31 የምንሆን Ethical Hackers በአገራችን ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ፈጣን የኢኮኖሚና የንግድ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር የህወሃትንና አጋር ተባባሪወቹን አፍራሽ እንቅስቃሴ ለመግታት ከመረጃ መረብ እና ኢንፎርሜሽን ሲስተም ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሙያችን በሚፈቅደው መልኩ ከፍ ያለ እንቅስቃሴ ላይ በማድረግ እንገኛለን።
ከዚህ ቀደም እንዳልነው የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታና መጻኢ እድል ያሳሰበን ባለሙያወች ለሕዝባችን በአቅማችን የምናደርገው የሙያ ድጋፍ የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት አልያም ንቅናቄ በመደገፍ ሳይሆን ለስልጣን ሲሉ የምንወዳት አገራችንና ህዝባችንን ወደ ትርምስና ሽብር ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ቡድኖችን ሴራ በማክሸፍ ሰላማዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማስቻል መሆኑን ሕዝባችን እንዲያውቀው እናሳስባለን።
በአሜሪካና አውሮፓ የምንገኝ በሶፍትዌርና ኢንፎርሜሽን ኮሚንኬሽን ሙያ የተሰማራን 31 Ethical Hackers
Alem says
31 is a crowd. How do you manage
to hold together? You need to explain
what ‘ethical hacking’ is. Most of all,
You need to publish evidence of your
work for anyone to take you seriously.
Please tell us how so-called ‘digital woyane”
could operate from Mekelle disrupting
and disinforming while using the nation’s
Internet services?