• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል – ቁጥር 01

June 3, 2013 06:16 am by Editor Leave a Comment

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ካለምንም እንከን ተጠናቀቀ። አምባገነን መለስ ዜናዊ ከግንቦት 8 ቀን 1997 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሽብርተኛ ህጎቹ እና ተግባሮቹ የገነባው የፍርሃት ፖለቲካ ህንጻ ፈረሰ። በዚኹ እለት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ማዕከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስኮች መፈጸም አለባቸው የሚላቸውን እርማቶች በንግግሮች እና በመፈክሮች በአደባባይ አስታወቀ። እነሱም ከሞላ ጎደል እንደሚከተለው ሊቀርቡ ይችላሉ፥ “መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም፣ ነፃነት እንሻለን፤ ፍትህ እንሻለን፤ አንለያይም፤ የህሊና፣ የሃይማኖት እና ሌሎች ፖለቲከኛ እስረኞች ይፈቱ፤ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች ይመለሱ፤ በአገራችን ሰላም አጣን፤ ልማት እያሉ ሙስና ሰሩ፤ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል፤ ህዝብ ማፈናቀል የዘር ማጥራት ወንጀል ነው፤ ህገ-መንግስት ይከበር፤ የሽብር፣ የነፃ ፕሬስ እና የሲቪክ ድርጅቶች ህጎች ይከለሱ ወይንም ይሰረዙ፤ ኢቲቪ ሌባ፣ ኢቲቪ ውሸት፣ ኢቲቪ ሽብር” የሚሉት ነበሩ።

መንግስት ለተጠየቀው ጥያቄዎች አዎንታዊ መልሶች መስጠት ይጠበቅበታል። ሁሉም ነገር በእጁ እና በደጁ ስለሆነ አዎንታዊ መልስ ለመስጠት የሚያስቸግረው ምንም ነገር የለም። ዛሬ ብድግ ብሎ “እስከ ዛሬ ድረስ ለፈጸምኩት ጭቆና ይቅርታ ይደረግልኝ። የዜጎችን ነፃነት ከዛሬ ጀምሮ አከብራለሁ። እስረኞችን ነገ እፈታለሁ። በኢትዮጵያ በነፃ ፕሬስ ላይ የጫንኩትን ጭቆና ከዛሬ ጀምሮ አንስቻለሁ። ኢ.ቲቪ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአንድ ወር ውስጥ ከመንግስት ፖለቲካ ነፃ ሆነው እንዲደራጁ አደርጋለሁ። ህዝብ ማፈናቀል በኢትዮጵያ ዳግም አልፈጽምም። የተፈናቀሉትም ካሳ ተከፍሏቸው እና ህጋዊ ዋስትና ተስጥቷቸው ወደቀድሞ ኑሮዋቸው እንዲመለሱ በአንድ ወር ውስጥ እፈጽማለሁ። አፈናቃዮችን ፍርድ ቤት አቀርባለሁ። ሁሉም በሙስና የሚታሙ ባለስልጣኖች አዜብ መስፍን ሳትቀር ክትትል እንዲደርግባቸው አደርጋለሁ። አንድን ሙሰኛ ከሌላ ሙሰኛ ሳላበላልጥ ሁሉም ሙሰኞች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አደርጋለሁ። በዚህም በዚያም እያልኩ በየውሩ ከደሞዛችሁ እምቆርጠውን ከዚህ ወር ጀምሮ በማቆም የኑሮ ውድነት ያጎበጠው ትከሻችሁ እንዲያገግም አደርጋለሁ። ህገ-መንግስት አከብራለሁ።”

በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን መንግስት ከፍ ብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ከፊሉን ያህል በማድረግ እንኳን ከአምባገነንነት ወደ ተሻለ የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ (Political Power Shift) ሊያደርግ ይችላል። ይኽን በማድረግ የነፃነት እና የዲሞክራሲ አድማሶች እንዲሰፋ ያደርጋል። በምላሹ የህዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል። የህዝብ ድጋፍ ማግኘት ማለት ደግሞ የፖለቲካ ድጋፍ ማገኘት ማለት ነው። እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ መንግስት ከተቃዋሚ ዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር የፖለቲካ ስልጣን ሽግሽግ ያደርጋል ማለት ነው። ይኽን በማድረግ መንግስት የሚያጣው ነገር ቢኖር አምባገነንነትን ብቻ ነው። ምርጫው የእርሱ ነው። በታሪክ ግን አምባገነኖች ካልተገደዱ በስተቀር በፈቃዳቸው የፖለቲካ ስልጣን ሽግሽግ ያደረጉበት ጊዜ ስለመኖሩ ተጽፎ ያየሁት መረጃ የለኝም።

መንግስት ከፍ ብለው ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ካልሰጠ በአምባገነንነት መቀጠል መርጧል ማለት ነው። እሱም ቢሆን ችግር አይሆንም ለዲሞክራሲ ሰራዊት። የዲሞክራሲ ሰራዊት በሰላማዊ ትግሉ የዲሞክራሲ ማዕከሉን መሰረት እና አቅም ያጎለምሳል። ይኽን ማድረግ እንደሚቻል ታሪክ ትመሰክራለች። ይሁን እንጂ መንግስት አምባገነንነትን ከመረጠ ስትራተጂካዊ የፖለቲካ ስህተት መፈጸሙን ልብ ሊል ይገባል። ነፃ ምክር ነው!

ሲጠቃለል፥ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ሁለት የፖለቲካ ማዕከሎች እንዳሉ እና በመካከላቸው ሰላማዊ ትግል እንደሚካሄድ አሳይታናለች። የዲሞክራሲ ኃይሎች የሚያደርጉት የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ (Political Power Shift) ትግል በስልጣን ላይ ከሚገኘው አምባገነን መንግስት አንፃር የፖለቲካ መሰረታቸውን እና አቅማቸውን ሳያቋርጥ ሽቅብ ማሳደግ አለበት። በውጤቱም የፖለቲካ ኃይል ደረጃቸው ቀስ በቀስ ከበታችነት ወደ አቻነት ከዚያም ወደ በላይነት ደረጃ ይጓዛል። የበላይነት ደረጃ መያዝ ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግ ማለት ነው። መንገዱ ደግሞ ምርጫ ወይንም ግብጽ ሊሆን ይችላል።

የፖለቲካ ኃይል ሽግሽግ ትግል ሌላ ቁልፍ የሰላማዊ ትግል ጽንሰ አሳብ ነው። አፈጻጸሙን በስፋት ማወቅ ጠቃሚ ነው የተሳካ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ። የሽግሽግ ትግልንም ከበካዮች (Contaminants) መጠበቅ ያስፈልጋል።

ግርማ ሞገስ
ግርማ ሞገስ

Goolgule/ጎልጉል በፌስ ቡካችሁም (https://www.facebook.com/goolgule16) ላይ በማቅረባችሁ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። አሁንም ቀጥሉበት። ዘሃበሻም እንደዚሁ። የረጅም ጊዜ የሰላማዊ ትግል ጉዋደኛዬ አብርሃ (ኢትዮሚዲያ) ምስጋናዬን ተቀበለኝ። እንዲሁም ቋጠሮ፣ ኢትዮጵያ ዛሬ፣ አቡጊዳ፣ አሲምባ፣ ECADFORM እና ያላየሁዋችሁ ድረገጾች በሙሉ ለምትለግሱኝ ትብብር ምስጋናዬ ገደብ የለውም። ትግሉ የጋራ ቢሆንም!

(girmamoges1@gmail.com)

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule