• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አስደሳቹ የብሔራዊ ቡድን ውጤትና ቅሌት

October 31, 2012 08:30 am by Editor 2 Comments

ባሳለፍናቸው ሳምንታት  እሁድ ዕለት አንበሳው የብሔራዊ ቡድናችን ያደረገው ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ትንቅንቅ በጣም አጓጊና አስደሳች እንደነበር አይተነዋል።  ጀግናው ብሔራዊ ቡድናችን የሱዳን አቻውን  ሁለት- ለዐልቦ  በሆነ ውጤት በዝረራ አሸንፎ እነሆ ከሰላሳ አንድ አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ እንድናልፍና  ልክ  አረንጓዴ ጎርፍ ተብለው የሚጠሩት አትሌቶቻችን ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገን እንድናውለበልብ እንዳደረጉን ሁሉ ዛሬም ብሔራዊ ቡድናችን አፍሪካ ላይ ለጊዜውም ቢሆን መሀሉ ላይ የሰይጣን አምልኮት ምልክት ያለበትን ባለኮከቡን አረንጓዴ ፥ ቢጫና ፥ ቀዩን ሠንደቅ ዓላማችንን እንድናውለበልብ አድርገውልናል፡፡ ምስጋና ይግባቸው ለዋልያዎቹ።

ይህን ድል አቶ መለስ በህይወት ኖረው ቢያዩት ደስ ይለኝ ነበር። የሚሉትን ለመስማት፡፡ ግን አፈር ይክበዳቸውና የሉም። ሀገራችን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ እንደሚጠብቃት ብዙ ምልክቶችን አሳይቶናል። ለዚህም ለአብነት ያህል፦ አዲስ አመት መግቢያ ግድም ዘረኛውንና አምባ ገነኑን፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት ደንታ የሌለውን፥ ህዝቡን በዘር የከፋፈለውን ፥ አረመኔ መሪ መለስ ዜናዊንና ቋሚ የሲኖዶስን ህግ ጥሶ በአጉራዘለልነት  በራሱ ፈቃድ የሾማቸውን ጭፍራውን አባ ጳውሎስን ጨምሮ ከምድረ ገዕ እንዲጠፉ አድርጓቸዋል። ሎሚ ተራ ፥ ተራ ነውና ሌሎቹንም ተራ በተራ  እንደሚጠርጋቸው አልጠራጠርም፡፡ በቅርብ የምናየው ይሆናል ።

ለሃያ አንድ ዓመታት ግራ – ሸቅብ ብለው በሃገሪቷ ላይ የጨበጠትን መዳፋቸውን አዲሱ አመት አስፈልቅቆ ጠላቶቿን ስለቀነሰላት  አዚማቸው ከሽፎ ፣ ብሄራዊ ቡድናችን ብቻ ሳይሆን ፥ የወጣት ቡድኑም ሆነ ፥ የሴቶቹ ሉሲ የእግር ኳስ ቡድን ጭምር ኢትዮጵያን ወክለው በአፍሪቃ ውድድሮች ውስጥ ዘንድሮ እንዲካተቱ አምላክ ፈቅዷል ፡፡

በቅድሚያ ግን ለስፖርት ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ስፖርት አፍቃሪ ህዝብ  በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ ። መጨረሻውንም እንዲያሳምርልን እየተመኘሁ ፣ አንድ ቅር ወደተሰኘሁበት ጉዳይ ላይ ግን በቀጥታ ላምራ ፡፡ ድሉን ያስጨበጡን ዋልያዎቻችንና  የወቅቱ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝን ጨምሮ፣  ለጋዜጠኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግን እጅግ አስተዛዛቢ ነበር ፡፡ እማን ላይ ቆመሽ ማንን ታሚያለሽ ሆኖባቸው እንደሆነም ልቦናዬ ጠንቅቆ ያውቃል ፡፡  ልማታዊ እስፖርተኝነትና የካድሬ ሥራ ሆኖባቸው ተጫዋቾቻን ፣ አቶ መለስ በህይወት ዘመናቸው የኢትዮጵያ የግር ኳስ ቡድን ላይ የተዛበቱትን በመርሳት መታሰቢያነቱ ለአቶ መለስ ይሁንልን ማለታቸው ግን አንጀቴን  ነው ያቃጠለው ።

መሬት ይቅለላቸውና ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ እንኳንም በዚህ ዘመን  ያልኖሩ ፡፡ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ኳስ ተጨዋች አይብቀልብሽ ብለው አገሪቷን ይረግሟት ነበር ፡፡  አቶ መለስ በአንድ ወቅት ስለ ብሔራዊ ቡድናችን ተጠይቀው የመለሱትን መልስ ላስታውሳችሁ ፡፡ በዚያን ወቅት  አቶ መለስ የጦር ኃይላችንን ወደ ሶማሌ ለማዝመት ደፋ ቀና የሚሉበት ወቅት ነበር ፡፡ አንድ ጋዜጠኛ ፦ ወደ ሶማሌ ተልኮ የሄደውን የኢትዮጵያ ወታደር እንደከዚህ በፊቱ አሜሪካዊ ወታደር  ሬሳውን በመኪና ሲጎትቱት  የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያይ ምን የሚልዎት ይመስሎታል ? ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ  የመለሱት መልስ ፦ ለጦርነት የሚሄደው እኮ ጀግናው የኢሕአዴግ ሠራዊት እንጂ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን አይደለም በማለት አሳዝነውናል።

በሌላ ወቅት ደግሞ ብሔራዊ ቡድናችን ከሀገር ውጪ ሊጫወት ሄዶ በሙሉ ተጫዋቾቹ ሳይመለሱ ቀሩ ተብለው ሲጠየቁ ፦ መንገዱን ጨርቅ ያርግላቸው ይህ እኔን አያሳስበኝም ፡፡ እኔን የሚያሳስበኝ አንድ ገበሬ ቢጠፋ ነው ብለው መልሰዋል።  እንደውም ስታዲየሙን ቢለቁልን ማዳበሪያ ፋብሪካ እንከፍትበታለን በማለትም ጭምር በብሄራዊው ቡድን ላይ ተዛብተውበታል ፡፡  ታዲያ እንግዲህ ጎበዝ ለዚሁ በብሔራዊ ቡድናችን ላይ በሞራሉ የተረማመደበትንና በቡድኑ አናት ላይ ቀለበት መንገድ የሰራበትን መሪ ነው መታሰቢያነቱ ለሱ ይሁን ብለውአሰልጣኝና ተጨዋቾች ያስደመሙን።

ማን ያውቃል ! ከእጅ አይሻል ዶማ እንዲሉ አቶ ሀይለማሪያምና ጭፍሮቻቸውም አስገድደዋቸው ይሆናል ስፖርተኞቻችን ልማታዊ ስፖርተኞች የሆኑብን ፡፡ እንደኔ እንደኔ ግን መታሰቢያነቱ ለአቶ ይድነቃቸው ተሰማና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪ በሙሉ ቢሆን በጣም ደስ ይለኝ ነበር ግና አልሆነም ። እንግዲህ ገዢው የኢሕአዴግ ፓርቲ ሲገረሰስና ሙሉ ለሙሉ ከስልጣን ሲወገድ የብሔራዊ ቡድናችን ዝናና ክብረ ሞገስ ልክ እንደ ሶስተኛው የአፍሪቃ ዋንጫ ጀግንነታችን መመለሱ አይቀርም ፡፡ ጅምሩንም በዚህ አዲስ አመት አይተናልና ፡፡ ለአለም ዋንጫም አገራችን እንደምትደርስ አንጠራጠርም ፡፡  ያኔ ታዲያ ማስታወሻነቱ ለማን ይሆን ? ቸር እንሰንብት ።

ውድቀት ለወያኔና ጭፍሮቹ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!
ዳዊት አበበ / ኦስሎ ኖርዌይ

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Comments

  1. elias bekele says

    November 1, 2012 01:50 am at 1:50 am

    bertu

    Reply
  2. እስከመቼ says

    November 1, 2012 11:40 pm at 11:40 pm

    ወንድሜ ዳዊት አበበ ከኖርዌይ፤
    ጥሩ ብለሃል።
    የእግር ኳስ ቡድናችን ባደረገው ጉዞ የተሰማን ደስታና ያሳየነው ፍንደቃ፤ የአንድነት ምንነታችን መግለጫ ነው። አንድነታችን የተደበቀ፣ የማይታይ፣ የተሰረዘ፣ ወይንም የጠፋ አይደለም። አንድነታችን በውስጣችን ያለ ሀቅ ነው። ብቅ የሚለው ሲፈተን ነው። የእግር ኳስ ቡድናችን ለረጂም ዘመን ርቆት ከነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ድግስ መግባቱ፤ ሁላችንንም ቀሰቅሰን። አንድነን ብለን ዓይናችንን አፈጠጥን። ጠላት መጣ ሲባል፤ ያለ የሌለውን መሳሪያ አንግቦ፤ ካገኘው ኢትዮጵያዊ ጋር ባንድነት ተሠልፎ፤ ሀገሩን ለመከላከል እንደሚነሳው ሁሉ፤ አንድነን ብለን ተነሳን። በአንድነታችን ኮራን። ፈነደቅን። ዘርዓይ ድረስን፣ አቡነ ጴጥሮስን፣ በላይ ዘለቀን፣ ባልቻ አባ ነፍሶን፣ ገብርዬን፣ ሽብሬ ደሳለኝን፣ እቴጌ ጣይቱን፣ ዘርዓያቆብን፣ አበበ በቂላን፣ ፋጡማ ሮባን፣ አቢቹን፣ የኛ ብለን ባቀፍነው እጆቻችን፤ የአባይን ወንዝ፣ የአዋሽን ወንዝ፣ የራስ ደጀንን ተራራ፣ የአክሱምን ሀውልት፣ የላሊበላን ገዳም፣ ሶደሬን፣ ኦሞን፣ የኛ እንዳልነው ሁሉ፤ ኮራንባቸው፤ የኛ ብለን አቀፍናቸው። ምንም እንኳ ማስታወሻነቱን ያሉት ባለሥልጣናት ለፈለጉት ቢሠጡትም፤ ማስታወሻነቱ እስከዛሬ በእግር ኳስ ታሪካችን አስተዋፅዖዋቸው ከፍ ላሉት ለይድነቃቸው ተሰማ፣ ለነመንግሥቱ ወርቁ መሆኑን ነጋሪ አንፈልግም። የተለጠፈው ማስታወሻ ይቀረፋል።
    ወደፊት የበለጠ እንጠብቃለን
    የወደፊታችን ያማረ ነው
    ወያኔን አያካትትምና
    እስከመቼ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule