ከሰናፍጭ ቅንጣት ባነሰችው አቅሜ በቤተ ክርስቲያናችንና በአገራችን ያለፉትን በንጽጽር ስመለከት፤ የሚሰማኝን በተደራረበ አካል እንደተፈጠረ ቀይ ሽንኩርት መሳይ ኢትዮጵያዊው ቅኔያችን ባቀረብኩት እጅግ በረካሁ ነበር:: ግን ይበልታ ማሰማት የሚችሉ የቤተ ክርስቲያኑቱ ልጆች አንገታቸውን የደፉበት ዘመን ስለሆነ ቅኔውን ትቼ ወደ አማረኛው ስነ ጽሑፍ እሻገራለሁ። የጦማሯ መነሻ በቪዲዮ የታየው የአቶ መለስ ግብአተ መሬት የተሸኘበት ፍትሐት ነው። ቤተክርስቲያችን ይህን አይነት የመሸኛ ፍትሐት የምታደርገው መመሪያዋን ፈጽመው ለሚሸኙ አማኞች ነው። በቦታው ላይ ተገኝተው ስነ ስርዓቱን የፈጸሙ ሰዎች ከኢ.ኦ.ተ. ቤተ ክርስቲያናችን መርሆ ውጭ መሆናቸውን ለመጠቆም ነው:: ሙሉውን አስነብበኝ
Leave a Reply