• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሪያድ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች “አሸባሪ” መባላቸው ተቃውሞ አስነሳ

May 12, 2014 12:52 am by Editor Leave a Comment

በቅርቡ በሪያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተከበረውን የአባይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግደብ 3ኛ አመት  ክብረ በዓል አሰመልክቶ ኤምባሲው በጠራው ስብሰባ ላይ  ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዳይገኙ  በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ባስተላለፉት ቀጭን ትዕዛዝ አዛውንቱ በአሸባሪነት ተፈርጀው በአሉን እንዳይታደሙ መታገዳቸው ሪያድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፈተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።

በተለይ ሰሞኑን  ውስጥ ወስጡን ሲነገር የነበረው የአምባሳደሩ መሃመድ ሃሰን ነውረኝነት ተግባር አርብ ሜይ 9 2014 ምሸት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ውስጥ ለአንድ ኢትዮጵያዊ በተዘጋጀ የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ አንድ የሃይማኖት አባት ሪያድ ከተማ ውስጥ መኖር ከጀመሩ 35 አመታትን እንዳስቆጠሩ በማውሳት በሪያድ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ በተለያዩ ግዜያት ከሚፈራረቁ መንግስታት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር በተለያዩ የሃገር ጉዳዮች ከኤንባሲው ጎን ቆመው ህዝብን በማስተባበር በሰላም እና በፍቀር እየሰሩ ማሳለፋቸውን ጠቅሰው ዛሬ በማን አለብኝነት የሚከተሉትን የተሳሳተ አቅጣጫ እንዲያርሙ የሚመክሯቸውን ሁሉ በጠላትነት በሚፈርጁ ስረአት አልበኛ የመግስት ሹማምንቶች ኤምባሲያችን እየተመራ በፀረሰላም እና በአሸባሪነት መፈረጃችን በህግ ደረጃ አነጋጋሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የስም ስያሜው የተለመደ እና ለታላላቅ ኢትዮጵያውያን እየተሰጠ የሚገኝ የኢትዮጵያውያን መለያ በመሆኑ ልንኮራበት እንጂ ልንሸማቀቅ እና ልናፍርበት አይገባም በለው እምባ እየተናነቃቸው ባሰሙት ንግግር በተሰብሳቢው የድጋፍ ጭብጨባ የአዳራሹ ድባብ ተለውጦ መዋሉን  ለማወቅ ተችሏል።

saudi 13የዛሬውን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለጨቆኞች መልዕክታችንን በግልጽ የምናስተላለፍበት መልካም  አጋጣሚ በመሆኑ ፈጣሪን ልናመስግነው የገባል በማለት የመናገር እደል አግኝተው ተቃውሞቸውን ማሰማት የጀመሩ  አንድ በዕድሜ የገፉ የሃገር ሽማግሌ በአምባሳደር እርምጃ የተሰማቸውን ቅሬታ ሲገልጹ ለህዳሴው ግድብ 20 ሺህ ሪያል (1 መቶ ሺህ ብር) የቦንድ ግዢ መፈጸማቸውን ጠቅሰው ወዳጅ እና ጠላቶቻቸውን መለየት በተሳናቸው የመንግስት ተወካዮች ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የተሰጣቸው ስም ተችሮኝ ሰንደቃላማችን የተሰቀለበት ግቢ እንዳልገባ መታገዴ መንግስት በተለያዩ ሃገራት የሚልካቸውን ሹማምንቶች የአምባሳደርነት ብቃት ትዝብት ውስጥ የከተተው ብቻ ሳይሆን የኮሚኒቲውን ንብረት ለግል ለመቆጣጠር አምባሳደሩ በማን አላበኝነት በግሉ የወሰደው እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸው ህዝብን በአሸባሪነት ፈርጆ በብሄር እና በሃይማኖት በማተራመስ  ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ እንዳይሆኑ በንጹሃን ላይ የሚለጥፍው የአሸባሪነት ውንጀላ በፍጹም ህጋዊ መስረት እና ምክንያት  የሌለው መሆኑን በተጨባጭ አረጋግጫለሁ ብለዋል።

አንዳንድ የልማት ማህበር ስራ አመራር አባላት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን የተቀንባበረውን ስረአት አልበኝነት ለማስፈፀም  በህዳሴው ግድብ 3ኛ አመት  ከበረ በአል ላይ የሚገኙ እና የማይገኙ ኢትዮጵያውያን ስም ዘርዘር በማውጣት ንጹሃን ኢትዮጵያውያንን በአሸባሪነት በማፈርጅ ተግባር ላይ ተስማርተው የልማት አጋር የሆነውን ህዝብ   እየለዩ የጥሪ ወረቀት በማዘጋጀት ሲያከፋፍሉ እንደነበር  ከውስጥ አውቂ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል። ይህ በእንዲህ  እንዳለ በአማራ ልማት ማህበር በኩል  በአሉን እንዲታደሙ የጥሪ ደብዳቤ ደርሷቸው  የነበሩ በሪያድ ነዋሪዎች ዘንድ  የተጣላን በማስታረቅ የተራበን በማብላት የታረዘን በማልበስ በአጠቃ ላይ  በሰው ሃገር የቤት ኪራይ ላጣ ገንዘብ በመለገስ እና ማህበረሰቡን በማስተባበር እርዳታ እንዲዋጣ በማድረግ የሚታወቁ እንደነ ፊት አውራሪ አሊ ሙሃመድ (አሊ ደሴ) አይነቱን  የህገር ሽማግሌ እና መስል ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች የበአሉ ተሳታፊ  እንዳይሆኑ መታገዳቸውን ተከትሎ  የህዝብ አገልጋይ ነን እያልን  ስለልማት እንዴት መናገር ያስችለናል በሚል አንዳንድ የአማራ ልማት ማህበር  አመራር አባላቶች በአምባሳደሩ ላይ ቅሬታ ማሰማታቸውን ለማወቅ  ተችሏል።

የሰሞኑንን እርምጃ  በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መስራች  እንደነበሩ የሚነገር ላቸውን  የኮሚኒቲው አንጋፋ አባላት እና ደጋፊዎች ወደ ኮሚኒቲው ቀጥር ግቢ እንዳይደርሱ እየተደረገ ያለው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን የሚናገሩ ምንጮች ሪያድ ከተማ ውስጥ ተደረገ በተባለው የአባይ ግድብ 3ኛ አመት በዓል ላይ እንዳይገኙ  የታገዱ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪነት በመፈረጃቸው በህዝብ ዘንድ የቀሰቀሰው ቁጣ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሊያመራ እንደሚችል አክለው ገልጸዋል።saudi 12

አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በሪያድ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ከወገኖቻቸው ይልቅ ለጥቂት የዓረብ ሃብታሞች የሚያጎበድዱ በቅርቡ መፉሃው ውስጥ በተነሳው ሁከት  የዜጎቻቸውን ክቡር ያስደፈሩ ለንዋይ ያደሩ አምባሳደር መሆናቸው ይታወቃል። አምባሳስደር መሃመድ ሃሰን የሃገሪቷን በሄራዊ ክበር ከሚፈታተኑ የተለያዩ ህገወጥ የሃዋላ ነጋዴ የአስሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶች ጋር የጥቀም ግንኙነት ፈጥረው በኢትዮጵያውያኑ ህይወት ዶላር ሲሰበስቡ የከረሙ በወገኖቻቸው ሬሳ ገንዘብ የሚበሉ ጨካኝ ሰው መሆናቸው በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሪያድ ነዋሪ ይነገራል።

ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎችን በአሸባሪነት በፈረጀው አወዛጋቢው የአባይ ግደብ 3ኛ አመት ክብረ በአል ዙሪያ አርብ ሚይ 09 ምሸት ኢትዮጵያኑ ያሰሙትን ተቃውሞ  አስመልክቶ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር ማብራሪያ እንዲሰጡኝ በስልክ ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም።

ይህ ሥዕላዊ መግለጫ በዓሉን ለመታደም የመጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ኮሚኒቲ ግቢ እንዳይገቡ ታግደው ጥቂቶች የህዳሴውን ግደብ 3ኛ አመት ክብረ በዓል ሲያደርጉ  የሚያሳይ ነው!

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule