• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ያዳቆነ ሰይጣን

October 28, 2016 02:50 am by Editor 2 Comments

ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም የሚል ነባር ተረት አለ። መልእክቱም ግልፅ ነው። በአንድ አጋጣሚ ክፉ አባዜ የተፀናወተው  ሰው ያው ክፉ አባዜው ለከፋ አደጋ ሳይዳርገው አይቀርም ማለት ነው። የብሂሉ ትርጉም ገብቶኝ ካልሆነ የምታውቁ አርሙኝ። እኔ ግን በጥላቻ ታሪክ የታጨቀ ኮሮጆ  አንጠልጥለው የሚዞሩና ህዝብን  እርስ በርስ በማጋጨት ደዌ የተለከፉ አንዳንድ የዖሮሞ ተቃዋሚና የመብት ተከራካሪነን ባይ ግለሰቦችን ይገልፅልኝ እንደሆነ ብዬ  የተጠቀምኩበት ምሳሌ ነው።

ሰሞኑን ከሎንዶን አካባቢ አንድ ጉድ ሰምቼ ጆሮዬን እስከማምነው ድረስ የፈጀብኝ ጊዜ ቀላል አልነበረም። በእውነቱ በቀላሉ የሚታመን ወሬ አልነበረም። ለነገሩ አሁን አለም ያወቀው ፀሃይ የሞቀው እውነት ሆኖ ሀቀኛ ኢትዮጵያውያን ዖሮሞዎችን ብቻ ሳይሆን መላ ህዝብ ጭምር አንገት ያስደፋ እውነት ስለሆነ ወሬ ልለው አልችልም። አዎ ከጥቂት ቀናት በፊት በሎንዶን በዖሮምኛ በተካሄደው ጉባኤ ኢትዮጵያ ካልፈረሰች ዖሮሞ ሰላም አይሆንም መባሉ ወሬ ሳይሆን እውነት ነው። እናም ጆሮዬ ያላመነውን መርዶ ልቤ እያለቀሰ ሰማው። ሀዘኔም ዝም እንድል አላስቻለኝምና የሆዴን መናገር ፈለግሁ።

አላማዬ ወሬ ማሞቅና እንደሃሳቡ አራማጆች በህዝብ አንድነት ላይ እሳት በመለኮስ የነርሱን ስህተት መድገም አይደለም። አላማዬ

  1. በሎንዶኑ የዖሮሞ ተቃዋሚዎችና የመብት ተከራካሪዎች ጉባኤ ላይ የተረጨው በታኝ መርዝ የደም አንድነቱን ባደባባይ በማረጋገጥ ገዢና አስገዢዎቹ የገመዱትን የጥላቻ አሽክላ በጣጥሶ ቃልኪዳኑን ያደሰው ህዝብ በነዚህ ከፋፋይ ግለሰቦች ንግግር እንዳይደናገጥ ለማሳሰብ
  2. ችኩል የዳያስፖራ ፖለቲከኞች የዖሮሞ ህዝብ እናትነቷን ሳይጠራጠር ያለስስት ህይወቱን ገብሮ በክብሯ ያቆያትን ሀገሩን ኢትዮጵያ በእናትነቷ ኮርቶ በክብር የሚኖርባት የዲሞክራሲና ፍትህ ምድር እንድትሆን የሚታገሉና ሲታገሉ የኖሩ አያሌ ሀቀኛ የዖሮሞ ፖለቲከኞችና በሳል ምሁራን መኖራቸውን በመዘንጋት የሃገር ማፍረስ ሟርት የዖሮሞዎች ሁሉ ወካይ ሃሳብ አድርጎ እንዳይመለከቱት ለማስጠንቀቅ
  3. በአንድ የጋራ ሀገር ወንዝና ጅረት በፈሰሰው የዖሮሞና አማራ  ወንድማማችና እህትማማቾች ደም ዳግም ውህደት በተረጋገጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ተፈጥሯዊ አንድነት አይናቸው ደም የለበሰ ጥቂት የዖሮሞ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋች ነን ባዮች የዖሮሞ ህዝብ ከወገኖቹ ጋር በክብር የሚኖርባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አድሶ ሊሰራት እንደማእበል እየተመመ ስለሆነ እርማቸውን እንዲያወጡ ለማርዳት ነው።

ስለጉባኤው

የዖሮሞ ህግ ባለሞያዎች ማህበር በይፋ የተናገረው የሎንዶኑ የዖሮሞ ድርግቶች ጉባኤ አላማ ክፉ አልነበረም። ሊቀመንበሩ ለኢሳት ከሰጡት ቃለምልልስ እንደሰማነው የዖሮሞ ድርጅቶች ብቻ የተሳተፉበት ጉባኤ አላማ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በማጥበብ አንድ አይነት አቋም ላይ ለመድረስ ነበር። በእኔ አስተያየት የዖሮሞ ህዝብ ፍላጎት አንድ ሆኖ ሳለ እንወክለዋለን የሚሉት የዖሮሞ ድርጅቶች ተፃራሪና ምናልባትም ለህዝቡ ባእድ የሆኑ አመለካከቶችን የሚያራምዱ ሆነው መገኘታቸው ጠቃሚ ስለማይሆን ተወያይቶና ተከራክሮ አንድ የሚያስማማአመለካከት ላይ ለመድረስ መጣር ተገቢ ነው። በእርግጥም ከሌሎች አጋር የፖለቲካ ድርጅቶች  ጋር ለማበርና ለመተባበር ይበጃል፤ ይመቻልም። እናም እዚህ ላይ ባዘጋጆቹ ላይ የማየው ጥፋት የለም።

ነገር ግን በጉባኤው አዘገጃጀትና ባዘጋጆቹ አመለካከት ረገድ ቢያንስ ሁለት ጉልህ ጉድለቶችን መመልከት ይቻላል። በመጀመሪያ  ደረጃ በጉባኤው የሚቀርቡ ፅሁፎች ይዘታቸው የሚመራበት ደንብና ፖሊሲ ወይም መመዘኛ የነበረው አይመስልም። እንዲያ ቢሆን ኖሮ መንፈሳቸው በዖሮሞ ህዝብ ፍቅር የተቃኘ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ጥላቻ የተመረዘ ግለሰቦች ህዝብ በማንም ፈቃድ ሳይሆን ፈጣሪው ባመላከተው ቅን መንፈስ ተነስቶ በደሙ እንደገና እየገነባ ያለውን አንድነት ላይ ውሃ የሚቸልስ መርዝ ሊረጩ እድል ባላገኙ ነበር።

በሌላ በኩል የዖሮሞ ህግ ባለሞያዎች ማህበር ሊቀመንበርና የጉባኤው ዝግጅት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ወየሳ የምንኖረው በዲሞክራሲ ሀገር ስለሆነ ተሳታፊዎች የፈለጉትን መናገር መብታቸው ነው ያሉት ትክክለኛ ግንዛቤ አይመስለኝም። መብት ገደብ አለው። ማንም ሰው የትም ይኑር የት በዲሞክራሲ መብት ሰበብ ሌሎችን የሚጎዳ ድርጊት ሊፈፅም አይፈቀድለትም። ተናጋሪዎቹ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን በሚል ድንፋታ በከንቱ ስሜት ተከታዮቻቸውን ማስጨብጨባቸው በየትኛው ያለማቀፍ ሰነድ የሚደገፍ መብት ወይም ነፃነት እንደሆነ የዖሮሞ ህግ ባለሞያዎች ማህበር በእርግጠኝነት ሊነግረን የሚችል አይመስለኝም። እኔ እንኳን የሰማሁት ማንም ሰው እጁን መዘርጋት የሚችለው የሌላውን አፍንጫ እስካልነካ ድረስ ነው ሲባል እንጂ ነጻነት ድንበር የለውም ሲባል አይደለም። መብት አለን ብለን ውስጣችን ያለውን የሃሳብ ቆሻሻ ሁሉ በየስፍራው እንደፋ ዘንድ ቢፈቀድ ኖሮማ  በዚች ምድር ላይ ከነችግራችንም ቢሆን መኖር ባልቻልን ነበር። እናም በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ዖሮምያን እንገናባለን ሲሉ በድፍረትና  በስሜት  ሲያጓሩ የተሰሙት የሟርት ፖለቲከኞች እንዲያ ማለታቸው መብታቸው ነው መባሉ ከህግ ባለሞያ የሚጠበቅ ሆኖ አላገኘሁትም።

ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያን በማፍረስ የዖሮሞን ህዝብ ጥቅም እናስከብራለን እያሉ በሙቀት ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ የዋሉት ጥቂት ተናጋሪዎች ንግግራቸው ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ትተን ካለንበት ተጨባጭ  ሁኔታ አንፃር ብቻ እንኳን ብንመዝነው የግለሰቦቹ ንግግር መቀራረብና መተሳሰብን፤ መፈቃቀድና መተማመንን የሚበክል ክፉ እቅድ ሆኖ እናገኘዋለን።

መፍትሄ

ሌሎች የፍቅርና የህብረት ሃይሎች፣ ሀቀኛና  በሳል የዖሮሞ ምሁራንንና ታማኝ ዖሮሞ ኢትዮጵያውያን ጭምር ይህን ዘረኛና መራዥ አመለካከት በማውገዝና እጅ ለእጅ በመያያዝ  ህዝብ የጀመረውን የፍቅር ጉዞ በፅናት ማስቀጠል፤

በፈጠራ ታሪክ የተደረተ የታሪክ ቡትቶ በመጎተት ኢትዮፕያ የምትባል  ሀገር እንድትፈርስ ሌት ተቀን ዖሮሞና ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲቆራረጥ ዘወትር የሰይጣን ህልም ሲያልሙ የሚውሉትን ያልበሰሉ  ግልፍተኛ ፖለቲከኞችን ወደጎን  በመተው የዖሮሞ ህዝ ጭቆና በማስወገድ ለሁሉም  የምትመች ኢትዮፕያን  ለመመስረት ለሚታገሉ ሀቀኛ የዖሮሞ አዋቂና በሳል  ፖለቲከኞች ያለማመንታት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ መስጠት፤

ከሃቀኛ የዖሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር የተጀመረውን ህብረት ማጠናከርና ኢትዮጵያን ከጭንቅ ለማውጣት መተባበር እጅግ አስፈላጊ ነው።

በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ዖሮምያንና ስልጣን  ለምታልሙ፤

ኢትዮጵያ ካልፈረሰች የዖሮሞ ህዝብ ሰላም አያገኝም የሚል የሟርት ፖለቲካ ለምታራምዱ መልእክት አለኝ። ምኞት መቼም መልካም ይሁን ደግ መላካዊ ይሁን ሰይጣናዊ አይከለከልም። በደጉ የዖሮሞ ህዝብና በሃቀኛ የዖሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን ጉያ ተደብቃችሁ በዖሮሞ ስም የዖሮሞን ቤት ሲፈርስ ማየት ታስቡ ይሆናል ግን መቼም ቢሆን ይህ ክፉ ህልም እውን እንደማይሆንላችሁ ስነግራችሁ እንደናንተ በምኞት ብቻ ሳይሆን በማስረጃ ነው።

 በኢትዮጵያ ህዝብ ደም የተሰራጨውን የዖሮሞ ደም አንጥሮ ለማውጣት ጥበብ የላችሁም። በእናንተ ውስጥ ያለውን የኢትዮጵያን ደም ከጠላችሁት ግን ራሳችሁን ማጥፋት የሚከለከላችሁ የለም። የኢትዮጵያን  ህዝ የደም አንድነትማ  ህዝብ ሲመሰክር ብቻ ሳይሆን እዚያው በጋራ ምድሩና ሸንተረሩ  ላይ ተቀላቅሎ ሲፈስ በቁማችሁ አይታችኋል። እንግዲህ የዖሮሞ ህዝብ የጋራ ቤቱን በጋራ እንደገና ሊሰራ እንጂ እንደምኞታችሁ ከወገኑ ላይነጠል ወስኖ በፍቅር እየተመመ ነውና እግዚአብሄር ያጽናችሁ። ያዳቆነው ሰይጣን ሳላቀስ አለቅም ካለ ምን ይባላል? ቸር ያሰማን!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. AKLILU says

    October 29, 2016 01:21 pm at 1:21 pm

    Great! thank you

    Reply
  2. Mulugeta Andargie aaaaa says

    October 31, 2016 02:54 am at 2:54 am

    ክልል በክልሉ!ዘር ሃረግ እዳማራ እንደትግሬ
    በቋንቋችን ተናግረን:ሳንፈራ ሳንከለከል በጥሬ
    ጎምርቶ ልናየው እንፈልጋለን ዛሬ!
    ታዲያ! ያዲያ! ማንም እምየ ቢል
    ወይ ኣባየ:እኩል ካልሆን ቢያነጥስ ቢስል
    ላንዱ ጨለማ: ንጋት!
    ለሌላው ጭምልቅ ያለክረምት
    እንዲም ሆኖ ላይዘራበት
    ጭቅይት! ጭቅይት! ብቻ ጭቅይት!
    የሃምሌ ዝናም እንኳን ኧረ ኣይሉት
    በባቡር የተጫነ እኩልነት!
    ከልካዩ እኮ ተቀምቶጧል!ተወዝቷል! ከኛው ቤት!
    “እንዲህ ኣድርጉ!” ሊል ይፈልጋል ደርሶ እደዘበት!
    ወይድ!ንሳ! ንሳ! ንሳ!
    ደርሶ ኣትሁኑብን አንበሳ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule