ይህ ትችት የኔን ጽሑፍ በሚያስተናግዱ እንደሚለጠፍ ባውቅም፤ ለሌሎቹ ተቃዋሚ ድረገፆች በሙሉ ተልኳል። ቢያወጡት አስተማሪ ነው። ብዙዎቹ ግን እንደማያውጡት ጥርጣሬ አለኝ። ምክንያቱም የፖለቲካ መሪዎቻቸውና ድርጅቶቻቸውን ጨምሮ በዚህ ትችት ስለተካተቱ ወገንተኛነታቸው ከሉጓም በበለጠ ይስባቸዋል። ለማንኛወም ለታሪክ ልኬአለሁ።
አሁን ወደ ርዕሱ ልግባ። በትግርኛ በምንመስለው ምሳሌ ልጀምር፡ {ዝፀገባ ደራሁስ ምስ ፀኻድም ማሕበር ይኣትዋ} “የጠገቡ ዶሮዎች ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር ይገባሉ” ይባላል። ሁለቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች እውቅ ሯጮች ከጭልፊቶች ጋር ማሕበር መግባቱ ምርጫቸው አድርገው ይሆናል። የጭልፊቶቹ እና የዶሮዎቹ ማሕበር የሚቆየው ዕድሜ አብረን የምናየው ይሆናል።
ሰሞኑን በአጋጣሚ “ዩቱብ” ድረገጽ ላይ አንድ ማሕደር ለመፈተሽ ጎራ ስል ድንገት ያላሰብኩበትን እና አስደንጋጭ አስገራሚ ነገር በዓይኔ ተመለከትኩ። “ገንዘቤ ዲባባ እና ወርቅነሽ ደገፋ” በሰንደቃላማችን ላይ ያሳዩት ፖለቲካዊ ጋጠወጥነታቸውን በወቅቱ የተመለከቱ ዜጎች ጉዳዩን ለማሳወቅ ‘በዩቱብ’ ላይ ለጥፈውት ለካ ኖሯል። እኔ ኣላወቅኩም ነበር። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
ለጥይበሉ says
ይድረስ ለአቶ ጌታቸው ረዳ፣
እኔም እንደ እርስዎ ድንገት ድረ ገጽ ሳገላብጥይህን ጽሁፍዎን አገኘሁ እና የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ። እርስው የት እንደሚኖሩ አላውቅም ግን እነዚህ አትሌቶች የሚኖሩት አምባሻው የሌለበትን ባንዲራ መጠቀም በህግ በሚከለክል ሃገር ወስጥ ነው። አረረም መረረም ይህ መንግስት በህይወት እስካለ ድረስ ህግ ብሎ ያወጣን መታዘዝ ያሊያ ግን ከህግ አስፈጻሚ ተብዬዎቹ ጋር መላተም ይከተላ። ድንጋይ ደግሞ ድንጋይ ነው፣ ብትወድቅበትም ይጎዳሃል ቢወድቅብህም እንደዚያው። እነዚህ አትሌቶች ደግሞ ከሮጡ በኋል ተመልሰው የሚገቡበት ሃገር ያስፈልጋቸዋል። አጉል ጀብደኝነት የሚጠቅመው ማንን ይመስልዎታል?እንዳሉት ይህን በማድረግ አንገታቸውን ለቢላ ቢሰጡ ምን አልባት እርስዎን ደስ ይልዎት ይሆናል እነሱ ግን ደመ ከልብ የሚሆኡ ይመስለኛል። ለርስዎ ሰማዩ ቅርብ ነው ምክንይያቱም የወያኔ እጅ ከሚደርስበት ርቀት አይገኙምና። ስለዚህ ሌላውን መፈረጅ እንዲሁም ሌዋ መስዋዕትነት እንዲከፍልልዎት በፅኑ የሚመኙ ያስመስልብዎታል። ሌላው ቀርቶ በመሰላቸው መንገድ እየታገሉ ያሉት ላይ እንዳመጣልዎ ሲተፉ ማየቱ ያሳፍራል። ሌላው የሚገርመው ይቅርታ እንዲጠይቁ ማሳሰብዎት እና ካልሆነ ግን የሚወስዱት እርምጃ ነው። እነዚህ አትሌቶች በዚህም ሆን በሌላ በማናቸውም መንግስት ዘመን ስራቸው መሮጥ እና ሃገራቸውን እና ስማቸውን ማስጠራት ነው። ጊዜው ደርሶ አምባሻውን የሚፍቅ መንግስት ሲነሳ በነጻነት የፈለጉትን ሊያደርጉ ይችላሉ። እስከዛው ድረስ ግን ብልጥ እየበላ ያለቅሳል። ይሄ የእኔ ያልኩት ብቻ፣ ካለ እኔ ላገር የሚያስብ የለም የሚል አስተሳሰብዎትዝቅ እንጂ ከፍ ሊያደርግዎት አይችልም። በዚያ ላይ የሚሰብኩለት ዲሞክራሲ የፈለጉትን የመደገፍ መብት መሆን ይኖርበታል። ያለዚያ እንደ ወያኔ ልማት ከዲሞክራሲ ይቀድማል እንደሚለው ማለትዎ ሊሆን ይችላል። እርስዎ የመሰለዎትን እንዳመጣልዎ እንዳሉ ሁሉ እኔው የመሰለኝን ብያለሁ።
ቀና ቀናውን ያሳስበን።
ለጥይበሉ ነኝ
aradw says
It was customary in another world and in Ethiopian diaspora politics to use flag as a peaceful political expression. We have seen flag burning on TV and in different occasion. We have seen the diaspora group burning the TPLF flag and vice versa the TPLF group burning Ethiopian Flag. This might be very uncomfortable to the one who loves his flag, but is a common or as sometimes called here is USA freedom of Expression. It is very easy to judge the two ladies while leaving comfortably in California. My question to Ato Getachew is “what would you do if you are in their position?
We can say or you can say , they can pick and wear it as it done in this situation and expect TPLF jail. They are not courageous as Lelissa Feyssa. From the picture it seems they expected the current EPRDF flag which they want to wear and be safe when they go home. This is not a political expression of desecration of the Ethiopian Flag. Looking the video in my opinion what they did was drop the flag to be safe, when they go home and continue what they do best i.e continue running. Let us not take everything political, sometime people do things from fear or other reason but not political. You have your own judgement and this is mine.