• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ

February 14, 2014 08:24 am by Editor 1 Comment

ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በ8-2-2014 በኖርዌ ኦስሎ በመገኘት ከኢትዮጵያዉያን የስደተኞች ማሕበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በኖርዌ ስለሚገኘው ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮዽያዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እና ይህ ጥገኝነት ጠያቂ በኖርዌ ምን ያህል ተቀባይነት አለው በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ9-2-2014 በሳውድ አረቢያ የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ለመርዳት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እኛ ስንሰቃይ አሜሪካ ዝም ብላ ይሆናል፣ እኛ ስንሰቃይ የአውሮፓ ሕብረት ምንም አላለ ይሆናል የኢትዮጵያ አምላክ ግን ከኛ ጋር ነው በሚል ልብ የሚንካ ነገር ተናግረዋል።

oslo 2በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ10-2-2014 በኖርዌ ጥገኝነት በጠየቁ ኢትዮዽያዊ ወገኖቻቸው ላይ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ እና ምን ያህል ጉዳያቸው እየታየ ነው የሚለውን በማንሳት ከLandinfo እና NOAS (norsk organisation for asylsøkere) ጋር በሰፊው ውይይት አርገዋል።

በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በሐገራችን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረገጣው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ገልፀው በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንም ይህንን አንባገነን ዘረኛ የወያኔ መንግስት ለመጣል በሚደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረጉ ስለሆነ እና ወያኔም ሰላዮቹን አሰማርቶ መረጃ እየሰበሰበ ስለሆነ ቢመለሱ አደጋ ይደርስባቸዋል በማለት ገልፀዉላቸዋል።

የመላው ኢትዮዽያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴም የዘረኛው ወያኔ መንግስት ተሰደን ባለንበትም ኖርዌ ሰላዮችን እየላከ መረጃ ይሰበስባል፣ ጉዳያችንም በሚገባ ስለማይታይ የጤና መታወክ እየደረሰብን ነዉ ከ2 ኔጌቲቭ በላይ አላችሁ እየተባለ ተገቢው የጤና ክትትልም አይደረግልንም በማለት ቅሬታቸውን ከገለፁ በኋላ የኑዋስ ተወካይ የሆኑት ጆን ኡላ በኖርዌ ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማሕበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ተገናኝተው በመነጋገር ጉዳዩ ለፍትህ ሚንስትር የሚቀርብበትን መንገድ ለማመቻቸት ኮሚቴውን ሌላ ስብሰባ እንደሚጠሩ በመግለጽ ስብሰባው አጠናቀዋል።

አቶ ኦባንግም የኖርዌ ቆይታቸውን ጨርሰዉ ተመልሰዋል።

የስደተኛ ማህበሩ ኮሚቴም አቶ ኦባንግ በየጊዜው ለሕዝባቸው መብት መጠበቅ የሚያድርጉትን ትግል በማድነቅ ምስጋና እና አድናቆት ቸረዋልl

ከኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Gach says

    February 28, 2014 09:53 am at 9:53 am

    ኦባንግ በጣም ጥሩ ነዉ ።ሁላችንም ከጎንህ ነን።ከተለያዩ ሀገራት ጋር የምታደርገዉ ዉይይት ጥሩ ነዉ ቀጥልበት።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule