• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአዲስ አበባ ውሃ እስከ 20ቀናት ይጠፋል

March 16, 2014 11:44 pm by Editor 2 Comments

* “የውኃ ምርት ችግር የለብንም የኤሌክትሪክና የማሰራጨት እንጂ” የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን

የፌዴራል መንግሥት መቀመጫና የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ፣ ለሁለትና ሦስት ቀናት ይጠፋ የነበረው የውኃ ችግር እስከ 20 ቀናት እየጠፋ  መሆኑንና ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡

በተለይ ከሳሪስ እስከ ቃሊቲ፣ አየር ጤና፣ ወይራ ሠፈር፣ ለቡ፣ ጉለሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ፒያሳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ መርካቶ፣ የካ በተለያዩ ወረዳዎች አራት ኪሎ (አልፎ አልፎ) በአጠቃላይ በከተማው ከአምስት እስከ 20 ቀናት ውኃ ጠፍቶ እንደሚሰቃዩ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ አበበ የተባሉ የሳሪስ አቦ ማዞሪያ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጹት፣ የውኃ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ ያስገርማቸዋል፡፡ ቀን ቀን ይጠፋና እኩለ ሌሊት ይመጣላቸው በነበረው ውኃ ሲማረሩ፣ ይባስ ብሎ የመጥፋቱ ሁኔታ ወደ ሦስት፣ አራትና አምስት ቀናት አድጐ አሁን እስከ 20 ቀናት ውኃ እንደማያገኙ ጠቁመዋል፡፡ በመንገድ ግንባታ ምክንያት በሚል በተለይ ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2004 ዓ.ም. መጀመርያ ወር ድረስ በፈረቃ በሁለትና ሦስት ቀናት ቆይታ ያገኙት የነበረው ውኃ፣ መንገዱ ከተጠናቀቀ በኋላ ብሶበት ወደ ወር ሊቃረብ መድረሱንና አሁን ባለው ሁኔታ በቅርቡ ወር ሙሉ ላያገኙ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ከፍታ ባላቸው አካባቢዎች ውኃ ማዳረስ እንዳቃተው አምኖ ሲገልጽ የከረመ ቢሆንም አሁን ግን በለገዳዲ፣ ገፈርሳና አቃቂ ቃሊቲ የከርሰ ምድር ውኃ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችም ውኃ እያጡ በመሆኑ ‹‹ምን ተፈጠረ?›› የሚል ጥያቄ እየተፈጠረባቸው መሆኑን ወ/ሮ ስንታየሁ ገልጸዋል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ውኃና ኤሌክትሪክ  የሚጠፉበት ጊዜና ቀናት በመገናኛ ብዙኃን ይነገር እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮዋ፣ አሁን መንግሥት ሰልችቶት ይሁን አሳፍሮት ዝምታን መምረጡ እያሰጋቸው መሆኑን አክለዋል፡፡

ከመሀል አዲስ አበባ (ፒያሳ) ጀምሮ እስከ ዳር ከተማና አቀበት በሚባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ሁሉ እንደ ወ/ሮ ስንታየሁ ‹‹የውኃ ያለህ›› እያሉ ሲሆን፣ የውኃና ፍሳሽ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች፣ በክፍለ ከተማና እስከ ማዘጋጃ ድረስ እየሄዱ አቤት ቢሉም ምላሽ ሊያገኙ እንዳልቻሉ እየገለጹ ነው፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት የግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ፣ ውኃን በሚመለከት ያቀረቡትን ሪፖርት በተለይ በውኃ ችግር water lineውስጥ ያሉ ነዋሪዎች አምርረው እየተቃወሙ ነው፡፡ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሽሮ ሜዳ ነዋሪ እንደገለጹት፣ ‹‹እኛስ መጣች መጣች ብለን ሌሊቱን ስንሯሯጥ መኖሩን ለምደነዋል፡፡ የኛ ዕጣ ፈንታ የደረሳቸው የመሀል ከተማ ነዋሪዎች ግን ያሳዝኑኛል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ያዘንኩት የታደለ አገር በዘመናዊ መንገድ ማንኛውንም አቅርቦት እንደልቡ ሲቀርብለት፣ እኛ የውኃ ጥም ለማርካት ቦቴ መኪና እንደሚገዛልን እየተነገረን ነው፤›› በማለት የከንቲባውን ሪፖርት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውመዋል፡፡

አስተዳደሩ ትኩረት በመስጠት ከተንቀሳቀሰባቸው ተግባራት አንዱ የውኃ ምርትን መጨመር መሆኑን የገለጹት ከንቲባ ድሪባ፣ በአቃቂ ቃሊቲ 19 ጥልቅ ጉድጓዶች መቆፈራቸውንና 80 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ማምረት መቻሉን፣ በለገዳዲም 11 ጥልቅ ጉድጓዶች እየተቆፈሩ መሆኑን፣ ለገዳዲን በማስፋትና የድሬ ግድብን በማሻሻል የውኃ ማምረት አቅምን ወደ 195 ሺሕ ሜትር ኩብ ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ ወደ 260 ሺሕ ሜትር ኩብ የሚጠጋ ውኃ ማምረት የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑንና ሁሉም ሥራዎች ሲጠናቀቁ 610 ሺሕ ሜትር ኩብ የውኃ ምርት ከፍ እንደሚልም በሪፖርታቸው ከንቲባው አብራርተዋል፡፡

ነዋሪዎች ግን ሥራውና ዕቅዱ ወይም እንቅስቃሴው ከወረቀት ላይ እንደማያልፍ  በመግለጽ፣ የዕለት ጥማቸውን የሚያስታግሱበት መፍትሔ እንዲፈለግላቸው እየጠየቁ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ግን በነዋሪዎቹ አቤቱታና ሮሮ አይስማማም፡፡ ‹‹የውኃ ምርት እጥረት የለብንም፣ ችግራችን የሥርጭት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንገድ ግንባታዎችና በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መጥፋት ከፍተኛ ችግር እየፈጠረብን ነው፤›› ሲሉ የባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ የሥራ ሒደት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ከምሴ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለይቶ ማወቁንና ከፍተኛ ችግር አለባቸው የተባሉትን ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ጉለሌ፣ የካና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍላተ ከተማዎች ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች፣ ለተወሰኑት ጊዜያዊ የፕላስቲክ መስመር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቀበት ለሆኑት ደግሞ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ያሠራቸውን ታንከሮች እየተተከለ መሆኑን፣ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ደግሞ ጄኔሬተር እየተገዛና የፀሐይ ኃይል ለመጠቀም ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ (ሪፖርተር)

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. liku says

    March 17, 2014 07:28 am at 7:28 am

    It is really a shame to have water distribution problem in the capital city of Africa union head quarter And this a country which was boasting electric power distribution to neighboring countries

    Reply
  2. Tesfaye says

    March 17, 2014 12:27 pm at 12:27 pm

    It is now a month since we got clean water around Betel Hospital. Who will resign from his or her post because of this failure?? I know none!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule