
በሕይወት እያላችሁ…
ላለመዋደድ ተፋቅዳችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ…
ባንዲት ጉድጓድ ታድማችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ…
ምስጥና አፈር ላስማማችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ…
ማንም ምንም ላይለያችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ…
ተቃቅፋችሁ
የኋላ ኋላ ኋላ…
ላሸለባችሁ…
ለናንተ… ላምበሎቼ
ለጋሼ ኃይሌ ፊዳ
ለጋሼ ብርሃነ መስቀል ረዳ
እነሆኝ እላለሁ…
ይህን ያገር እዳ፡፡
(በአበራ ለማ)
“ጥሎ ማለፍ” ለተባለው የታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፌ መታሰቢያ ቋጥሬው የነበረ – 2003 ዓ.ም.
Leave a Reply