ዋይ ! ዋይ ! (በሙሾ ዜማ ይውጡት)
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ንዋይ ሞተ አሉ በቁሙ
ንዋይ ሞተ አሉ በቁሙ
ጨለመችበት ዓለሙ (2)
ንዋይ በንቁላል ተመታ
ንዋይ በንቁላል ተመታ
ሊዘፍን መጥቶ በማታ (2x)
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ምን ይላት ይሆን ለሚስቱ
ምን ይላት ይሆን ለሚስቱ
በንቁላል ገምቶ ደረቱ (2)
ጀግናው ፈረሰ ለሆዱ
ጀግናው ፈረሰ ለሆዱ
እንደ አሜሪካን ልማዱ (2)
ኡ ውይ … ( ረገዳ )
ኡ ውይ …
ኡ ውይ …
ዋይ ! ዋይ !
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
በጨፈረበት መሬት
በጨፈረበት መሬት
ተቀበለበት ውርደት (2)
ጥላው ሄዳለች በፊትም ሚስቱ
ጥላው ሄዳለች በፊትም ሚስቱ
ለወለደችው ይብላኝ ለናቱ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ምነው ምነው ምነው ምነው ንዋይ (በለዘብታ የድምጽ አወጣጥ)
ምነው በደሙ ላይ
መሮጥህ ለንዋይ
ምነው በደሙ ላይ
ህዝቡ ሲጨፈጨፍ
እንደቅጠል ሲረግፍ
ምነው አንተ ንዋይ
ምነው በደሙ ላይ
ቀና በል ጥላሁን
ተመልከት ጉድህን
ምነው በደሙ ላይ
ንዋይ አዋረደው፣
የሙያ ክብርህን
ዋይ! ዋይ! (ሞቅ ባለ የዝላይ ረገዳ)
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
እናትህ እንደዚህ መከራዋን ስታይ
ምነው አንተ ንዋይ
እህትህ እንደዚህ መከራዋን ስታይ
ምነው አንተ ንዋይ
አባትህ እንደዚህ እስር ቤት ሲዋረድ
ምነው አንተ ለሆድ
ወንድምህ እንደዚህ እስር ቤት ሲዋረድ
ምነው አንተ ለሆድ
ምነው በደሙ ላይ
ምነው አንተ ንዋይ
ዋይ! ዋይ! (ሞቅ ባለ የዝላይ ረገዳ)
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ዋይ! ዋይ!
ንዋይ
ማሳሰቢያ
ይህን ግጥም በመጠቀም በድምጽ ሙሾ ማውረድ ተፈቅዷል።
dereje says
ይህ እጅግ ደስ የሚል፣ የሚያስለቅስ ፣አንጀት የሚበላ፣ የሚያስቅ የሚያዝናና፣ የለቅሶ ግጥም ነው። ይህን አይቶ ንዋይ ደበበም ለገጣሚው ጥሩ ሽልማት ሸልሞ እራሱ ንዋይ በነጠላ ዜማ የሚለቀው ይመስለኛል። ገጣሚውን ግን አንድ ነግር ታዘብኩህ። የዚህ አይነት የሙሾ ችሎታ እያለህ ምነው ለክቡር ጠ,ሚ መለስ ዜናዊ ሳትገጥምላቸው። ወለላዬ ያኔ ትልቅ ዕድል አመለጠህ። ለእቶ መለስ በዚህ ችሎታህ ሙሾ ብታውርድላቸው ኢህአዲግም እኮ ኮኮብ ሙሾ አውጪ ብሎ ይሸልምህ ነበር። እናም ወለላዬ አደራህን ለሌሎቹም መንታ ምላሥ ዘፋኝ ነን ባዮችም የዚህ አይነት የሙሾ ትብብር አትንፈጋቸው።
biruke says
THE SMART
biruke says
AND ANOTHER ONE PLISE