ሰሞኑን የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ አሰልጥኖ ጃዝ ባላቸው ቅልብ ነፍሰ ገዳዮቹ፣ በኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያና ማፈናቀል፣ የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በጽኑ ያወግዛል። ይህ አንዱን ነገድ በሌላው ነገድ ላይ በማስነሳት፣ አንደኛው ሌላውን ከክልሌ ውጣ ማለት የወያኔ የሥልጣን ዘመን ማራዘሚያና ኢትዮጵያን የማፈራረሻ ስልቱ እንደሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ሁሉ ዐውቆ ፣ወያኔ ሆን ብሎ ከሚያጠምደው የራስ በራስ መጠፋፋት ተግባር ራሱን ሊቆጥብ ይገባል ብለን እናምናለን።
ይህ ሰሞኑን ወያኔ ሆን ብሎ በሶማሌና በኦሮሞ ነገዶች መካከል የለኮሰው ብጥብጥ ፣ ከገጠመው ሕዝባዊ ቁጣና ተቃውሞ የሕዝቡን የትብብር እንቅስቃሴ ለማዳከምና ሕዝባዊ አመጹን በሚሻው መልኩ ለማጨናገፍ ፣ የትግሉን አቅጣጫ ለማሳትና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ያጠመደው ወጥመድ መሆኑን በግራ በቀኙ ያሉ የሁለቱ ነገድ አባሎች ሊያስተውሉት ይገባል። የኦሮሞና የሶማሊያ ነጎዶች ዘላለማዊ ሲሆኑ፣ የትግሬ ወያኔ አገዛዝ ጊዜአዊ ነው። ጠፊና ተለዋጭ ነው። ኦሮሞና ሶማሌ ለዘመናት አብረው የኖሩትን ያህል ወደፊትም ተፈጥሮ በአንድ መልከዐምድር አቆራኝቷቸዋልና ማንም ሊለያያቸው አይችልም። ይህን ወያኔ አስቦና አቅዶ በሁለቱ ነገዶች መካካል ከራሱ ፍጡር «የሶማሊያ ክልል» ርዕሰ መስተዳድር ነኝ፣ ከሚለው ግለሰብ በስተኋላ ሆኖ፣በኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን ላይ የወሰደው የግድያና የማፈናቀል ተግባር፣ እኛ ለራሳችን ነገድ ኅልውና እና መብት የምንታገል እና በእኛ ላይ በከፋ ሁኔታ ላለፉት 27 ዓመታት ሲፈጸምብን የኖርንና ያለን የዐማራው ልጆች፣ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በሌሎች ላይ ሲፈጸም ስናይ የዝሆን ጀሮ ይስጠኝ ልንል አይቻለንም። በመሆኑም በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ግድያ፣ ስቃይና ማፈናቀል በጥብቅ ከማውገዝ አልፈን፣ ኢትዮጵያ ማለት በውስጧ የሚኖሩ ነገድና ጎሳዎች አንድነት የፈጠሩት አገርና የነርሱ ማንነት መለያና መታወቂያ ናት፤ ይህ ማንነትና መታወቂያ ተጠናክሮና ዳብሮ ሊቀጥል ይገባል ከሚሉ ቡድኖችና ስብስቦች ጋር በመሆን፣ የወያኔን የመከፋፈል ሤራ ከማክሸፍ ማሻገር፣ ወያኔን ገፍትሮ ለመጣል ለሚደረገው ግብግብ፣የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነው። (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply